የፋሲል ከነማው አጥቂ ሙጂብ ቃሲም ወደ አልጄሪያው ታላቅ ክለብ ጂ ኤስ ካቢሌ የሚያደርገው ዝውውር ከተስተጓጎለ በኋላ ከፋሲልና በተጨዋቹ መሃል ሌላ አለመግባባት ተከስቷል።
የአልጄሪያው ክለብ ሙጂብን በሙከራ እንጂ በቀጥታ አላስፈርምም በማለቱ ዝውውሩ የከሸፈ ሲሆን ተጨዋቹ ወደሀገር ውስጥ ክለቦች ፊቱን ማዞሩ ከክለቡ ጋር ልዩነት ውስጥ የከተተው ሆኗል።
ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ ግን ፋሲል የሚጠብቅበትን 1.5 ሚሊዮን ብር መልሶ መልቀቂያውን የወሰደው ሙጂብ ከሰበታ ከተማና ከደሬዳዋ ከተማ አንዳቸውን ለመቀላቀል ያደረገው ሙከራ ፌዴሬሽኑ ውድቅ አድርጎታል። ያም ሆኖ እድሉ ከተገኘ ለማስፈረም ወልቂጤ ከተማም የክለቦቹ ሙጂብን የማስፈረም ሩጫን ሶስትዮሽ አድርገውታል።
ፋሲል ከነማዎች መልቂያውን ለሙጂብ ቢሰጡም የውጪው ዝውውር ካልተሳካ ለሌላ የሀገር ውስጥ ክለብ መጫወት እንደማይችል ቅድመ ፊርማ ከተጨዋቹ ጋር ከተፈራረሙ በኋላ ተጨዋቹና ስራ አስኪያጁ ውሉን ለኢትዮዽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ማስገባታቸው ታውቋል።
በካሜሩን የሰነበቱትና ጉዳዩንለመዳኘት የተጠበቁት ዋናጸሃፊው አቶ ባህሩ ጥላሁን በተለይ ለሀትሪክ በሰጡት መግለጫ ” ክለቡና ተጨዋቹ ውል በቀደዱበት ውል ማፍረሻ ላይ በተጨዋቹና በክለቡ የውስጥ ስምረነት መሰረት ለመለያየት መስማማታቸውን ይገልጻል የውስጥ ስምምነታቸው ደግሞ ፌዴሬሽን ያስገቡት ሌላ ደብዳቤ ነው ደብዳቤው ደግሞ የውጪ ጉዞው ካልተሳካ ለፋሲል ከነማ ተመልሶ እንደሚጫወት ተስማምተው የፈረሙበት በመሆኑ የትኛውም ክለብ ለመዘዋወር ፍቃድ አያገኝም በዚህም ደብዳቤ ስምምነት መሰረት ሙጂብ ቃሲም ከፋሲል ከነማ ውጪ ወደየትም ክለብ መዛወር አይችልም” ሲሉ የፌዴሬሽኑን ውሳኔ ይፋ አድርገዋል።
ዋና ጸሃፊው እንደሚሉት “ብቸኛ የሙጂብ እድሉ ክለቡና ተጨዋቹ መስማማታቸውንና ክለቡ ዝውውር ቢያደርግ እንደማይቃወም ፌዴሬሽን በመምጣት ከገለጸ ብቻ ነው” ሲሉ ጠንከር ያለ ምላሽ ሰጥተዋል።
አሁን ብቸኛ እድል ሙጂብ ቃሲምና ወኪሉ ሳምሶን ነስሮ ከፋሲል ከነማ ጋር የሚያደርጉት ሰላማዊ ድርድር ብቻ ሆኗል።
አስተያየት ይስጡ