መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አዳማ ከተማ የሶስት ተጫዋቾችን ዝዉዉር አጠናቋል !!
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግአዳማ ከተማዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

አዳማ ከተማ የሶስት ተጫዋቾችን ዝዉዉር አጠናቋል !!

አጋራ
አጋራ

ከአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ቅጥር በኋላ ወደ ዝዉዉር ፊታቸዉን በማዞር የተለያዩ አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ የሚገኙት አዳማ ከተማዎች ተጨማሪ የሶስት ተጫዋቾችን ዝዉዉር አገባደዋል።

የዉድድር አመቱን በወልቂጤ ከተማ ተጫዉቶ ማሳለፍ የቻለዉ የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ጀማል ጣሰዉ ከክለቡ ወልቂጤ ከተማ ጋር ከተለያየ በኋላ በዛሬዉ ዕለት ወደ አዳማ ከተማ በሁለት አመት የስምምነት ዉል ማምራቱ ዕርግጥ ሆኖአል።

ሌላኛዉ የክለቡ ፈራሚ ደግሞ ረዘም ላሉ አመታት ከተጫወተበት ሲዳማ ቡና ጋር በትላንትናው ዕለት በስምምነት የተለያየዉ የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ዮሴፍ ዮሀንስ ሲሆን ተጫዋቹ ከሲዳማ ቡና ጋር በተለያየበት ማግስት ወደ አዳማ ከተማ በማምራት በዛሬው ዕለት ፊርማውን አኑሯል።

ሶስተኛዉ ፈራሚ ደግሞ በሀዋሳ ከተማ ቤት ረዘም ላሉ አመታት በወጥ ብቃት መጫወት የቻለዉ የግራ መስመር ተከላካዩ ደስታ ዮሀንስ መሆኑ ታዉቋል። በተጨማሪም በትላንትናው ዕለት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአሰልጣኝ ዉበቱ አባቱ አማካኝነት ጥሪ ከደረሳቸው 28 ተጫዋቾች መካከል አንዱ እንደሆነ ይታወቃል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...