መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሙጂብ ቃሲምና ፋሲል ከነማ በይፋ ተለያዩ
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግየዝውውር ዜናዎችፋሲል ከነማ

ሙጂብ ቃሲምና ፋሲል ከነማ በይፋ ተለያዩ

አጋራ
አጋራ

ፋሲል ከነማ ለዝውውሩ ያቀረበው ጥያቄ ምላሽን ማግኘቱን ተከትሎ ከአጥቂው ሙጂብ ቃሲም ጋር በይፋ ተለያይቷል።

ሙጂብ ከፋሲል ከነማ ጋር ቀሪ የአንድ አመት ውል ያለው እንደሆነና የተገኘው እድል ከክለብም አልፎ ለሀገር ትልቅ ትርፍ ያለው በመሆኑ ዝውውሩ የክለቡን ጥቅም ባልነካ መልኩ እንደሚፈጸምና ለመጨረሻ ውሳኔ ዛሬ ከወኪሉ ጋር ቀጠሮ መያዙን ስራ አስኪያጁ አቶ አቢዮት ብርሃኑ መናገራቸው በትናንትናው እለት መረጃውን ማድረሳችን አይዘነጋም ። ፋሲል ከነማ ለዝውውሩ ያቀረበው የመልቀቂያ ወረቀት በክለቡ በኩል ይኹንታ በማግኘቱ ከክለቡ ጋር በይፋ መለያየቱ እውን ሆኗል።

በቀጣይ ተጨዋቹ ወደ አልጄሪያ ውጤታማ ክለብ ጂ ኤስ ካባሊ የሚያደርገው ጉዞ ብቻ የሚጠበቅ መሆኑን ወኪሉ ሳምሶን ነስሮ ተናግሯል። የክለቡ የደጋፊ ማህበርም ለእስከዛሬው ግልጋሎቱ በማመስገን በስጦታ ሸኝተውታል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ኢትዮጵያ መድህንኢትዮጵያ ንግድ ባንክዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ኢትዮጵያ መድን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 3-1 በማሸነፍ የአምስተኛውን ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ በድል አጠናቀቀ!

በአቤኔዘር አበበ ኢትዮጵያ መድን በድል የአምስተኛውን ሳምንት ጨዋታ አጠናቀቀ! በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ...

ባህርዳር ከተማዜናዎችየጨዋታ ዘገባፋሲል ከነማ

ፋሲል ከነማና ባህርዳር ከተማ ነጥብ ተጋሩ!

በአቤኔዘር አበበ በአማራ ደርቢ ፋሲል ከነማና ባህርዳር ከተማ ነጥብ ተጋሩ! በሁለቱ የአማራ...

ሀላባ ከተማዜናዎችየጨዋታ ዘገባፋሲል ከነማ

ሀላባ ከተማና ፋሲል ከነማ 1ለ1 በሆነ ውጤት ተለያዩ።

በአቤኔዘር አበበ ሀላባ ከተማና ፋሲል ከነማ ነጥብ ተጋሩ! በሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...