መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ የቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ክለቡን ለፊፋ ሊከስ መሆኑ ተሰምቷል!!
ቅዱስ ጊዮርጊስቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎች

የቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ክለቡን ለፊፋ ሊከስ መሆኑ ተሰምቷል!!

አጋራ
አጋራ

ደቡብ አፍሪካዊዉ የቀድሞ የፈረሰኞቹ አሰልጣኝ ማሂር ዳቪድስ የቀድሞ ክለቡን ቅዱስ ጊዮርጊስ ለፊፋ ሊከስ እንደሆ የአሰልጣኙ ወኪል ራስተም ሳይመንስ ገልጿል።

ከጥቅም 2012 ዓ.ም አንስቶ ክለቡን ማሰልጠን የጀመረው አሰልጣኝ ማሂር ከስድስት ወራት ቆይታ በኋላ ከአራት ወር በፊት በወርሀ መጋቢት ከክለቡ መሰናበቱ ይታወሳል።

ከክለቡ ከተሰናበተ በኋላ ወደ ሀገሩ በማምራት አሁን ላይ ማሪዝበርግ ዩናይትድ የተባለውን ክለብ በምክትል አሰልጣኝነት በማሰልጠን ላይ የሚገኙዉ ማሂር ዳቪድስ የቀድሞ ክለቡ ቅዱስ ጊየርጊስ እስከ አሁን ድረስ የሁለት ወር ከግማሽ ክፍያ እንዳልፈፀመለት ተናግሯል። በተደጋጋሚ የክለቡ ሰዎች ቃል ቢገቡለትም ቃላቸዉን ጠብቀው ክፍያዉን ሊፈፅሙ ባለመቻላቸው ምክንያት እና ጉዳዩን በተመለከተ ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ደብዳቤ ብንልክም ይፋዊ የሆነ ምላሽ ከፌዴሬሽኑ ሊሰጠን ባለመቻሉ ጉዳዩን ወደ ፊፉ በመዉሰድ ክስ ሊመሰርቱ መሆናቸውን ወኪሉ ራስተም ሳይመንስ ለሀትሪክ ስፖርት ገልጿል ።  በጉዳዩ ዙሪያ የቅዱስ ጊዮርጊስ አመራሮችን ለመጠየቅ ያደረገነው ጥረት ለግዜው አልተሳካም።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...