መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ “ፋሲል ከነማን የምንፋለምበት ጨዋታ ብዙም አይከብደንም፤ ማሸነፋችንም አይቀርም” አቡበከር ናስር /ኢት.ቡና/
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግኢትዮጵያ ቡናዜናዎች

“ፋሲል ከነማን የምንፋለምበት ጨዋታ ብዙም አይከብደንም፤ ማሸነፋችንም አይቀርም” አቡበከር ናስር /ኢት.ቡና/

አጋራ
አጋራ

ተጠባቂው ፍልሚያ
(ቅዳሜ 4፡ዐዐ)
ኢትዮጵያ ቡና ከፋሲል ከነማ
አቡበከር ናስር ከሙጂብ ቃሲም

ኢትዮጵያ ቡና ከፋሲል ከነማ የሚያደርጉት የዛሬው ቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮና የብዙዎቹን ትኩረት ስቧል፤ ሁለቱ ቡድኖች ካላቸው ጥንካሬ አኳያም ግጥሚያው በከፍተኛ ጉጉትም ተጠብቋል፡፡

በባህርዳር ኢንተርናሽል ስታድየም የሚደረገው የሁለቱ ቡድኖች የዛሬ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ካሸነፈ የነጥብ ልዩነቱን በማስፋት የውድድር መሪነቱን ይበልጥ የሚያጠናክርበት ሲሆን ይህን ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና በአሸናፊነት ከተወጣ ደግሞ ከመሪው ቡድን ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ስለሚያጠብ ለሻምፒዮናነት የሚኖረውን ፉክክር የበለጠ እያጧጧፈ እንዲሄድ ያደርገዋል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና ከፋሲል ከነማ ዛሬ ከ4 ሰዓት ጀምሮ ስለሚያካሄዱት ጨዋታ ለየቡድኖቻቸው ጥሩ እንቅስቃሴ ከሚያሳዩት ተጨዋቾች መካከል ሁለቱን ማለትም ለኢትዮጵያ ቡና በአጥቂ መስመር ላይ በመጫወት 19 ግቦችን ያስቆጠረውንና የኮከብ ግብ አግቢነቱንም እየመራ የሚገኘውን አቡበከር ናስርንና የፋሲል ከነማውን ሀብታሙ ተከስተን /ጎላ/ የሀትሪክ ስፖርት አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ አናግሯቸው ለየጥያቄዎቹ በቂ ምላሽን ሊሰጡ ችለዋል፤ ተከታተሏቸው፡፡

ሀትሪክ፡- ኢትዮጵያ ቡና የቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ መሪውን ፋሲል ከነማን በዛሬው ዕለት ይፋለማል፤ ጨዋታው ምን መልክ ይኖረዋል? ማንስ አሸናፊ ይሆናል?

አቡበከር፡- ከፋሲል ከነማ ጋር የምናደርገው የዛሬው ጨዋታ በሁለታችንም ቡድኖች መካከል ጥሩ ፉክክር የሚታይበት ሲሆን ይህን ጨዋታም ለማሸነፍ ነው ወደሜዳ የምንገባው፤ ከግጥሚያውም የድል ውጤት ስለሚያስፈልገን ሶስት ነጥብን ከእነሱ ላይ እንወስዳለን፡፡

ሀትሪክ፡- ቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ላይ ሶስት ጊዜ ሀትሪክ ሰርተሃል፤ ባለፉት 24 የውድድር ዓመታት ላይም ይህን ሀትሪክ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በመስራት ብቸኛም ተጨዋች ሆነሃል፤ ይሄን ታውቃለህ?

አቡበከር፡- በፍፁም፤ እኔ የማውቀው በተጨዋችነት ዘመኑ ከዚህ ቀደም ሁለት ጊዜ ሀትሪክ ሰርቶ ከነበረው ዮርዳኖስ አባይ ጋር አሁን ለሶስተኛ ጊዜ አደረግኩት እንጂ ለሁለተኛ ጊዜ ሀትሪክ በሰራሁበት ወቅት ከእሱ ጋር ለመስተካከል ስለመቻሌ ብቻ ነው፡፡

ሀትሪክ፡- አሁን ታዲያ ሀትሪክን ለሶስተኛ ጊዜ በመስራትህና ብቸኛውም ተጨዋች በመሆንህ በውስጥህ ምን አይነት ስሜት ነው ያደረብህ?

አቡበከር፡- በዚህ ዙሪያ አይደለም ለሶስተኛ ጊዜ ሀትሪክ ሰርቼ መውጣቴ ይቅርና ለሁለተኛም ጊዜ ሀትሪክ በሰራሁበት ወቅት ስሜ ከቀድሞው ድንቅ አጥቂ ዮርዳኖስ አባይ እኩል በመጠራቱ በጣም ነበር ደስ ያለኝ፤ ሪከርዱን ለብቻዬ ስጨብጠው ደግሞ የበለጠም ነው ልደስት የቻልኩት፡፡

ሀትሪክ፡- ሶስተኛ ሀትሪክህን ሳይጨምር በቅርብ ጊዜ ለሁለት ጊዜ ሀትሪክ በመስራትህ አንተን ከዮርዳኖስ አባይ ጋር ስምህ እንዲጠራ ያደረገ ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር፤ ግን እኮ ታፈሰ ተስፋዬም ለኢትዮጵያ ቡና ሲጫወት በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለሁለት ጊዜ ከሀትሪክ ግቦች በላይ አራት እና አምስት ግቦችን አስቆጥሮ ብቸኛ ተጨዋችም የሆነበት ሁኔታ አለ?

አቡበከር፡- ይሄ የሚገርም ነው፤ ታፈሰ ተስፋዬ በአንድ ዓመት ውስጥ በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ላይ አራት እና አምስት ግቦችን ካስቆጠረ የግብ ድምሩ ውጤት 9 ይደርሳል፤ በሁለት ጨዋታዎች ላይ ግቦቹን ስላስቆጠረ እንጂ በሶስት ጨዋታዎች ላይ ሶስት ሶስት ግቦችን አስቆጥሮ ቢሆን ኖሮ እሱም እንደ እኔው ሶስት ጊዜ ሀትሪክ የሰራ ተጨዋች ተብሎ ይመዘገብለትም ነበር፤ ያም ሆኖ ግን ታፈሰ በሁለት ጨዋታዎች ላይ አራት እና አምስት ግቦችን አስቆጥሮ መውጣቱን ስሰማ ለእሱ ከፍ ያለ አድናቆት እንዲኖረኝም አድርጓል፡፡

ሀትሪክ፡- አቡበከርስ እንደ ታፈሰ ተስፋዬ በአንድ ጨዋታ ላይ መቼ ይሆን ከሀትሪክ በላይ ግብን የሚያስቆጥረው?

አቡበከር፡- ይሄ ፈጣሪ ያለው ቀን ይሆናል፤ ከዚህ በኋላ 11 ቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች አሉን፤ በአንድ ጨዋታም ከሶስት ግቦች በላይ የማስቆጠር ፍላጎቱና እልሙ አለኝ፤ ያኔም የዮርዳኖስን ሪከርድ እንደተጋራሁት እና እንደሰበርኩት ሁሉ የታፈሰንም ሪከርድ የማልጋራበት ምንም ምክንያት የለም”፡፡

ሀትሪክ፡- በኢትዮጵያ ቡና ውስጥ ያለህን ስኬታማነት በመመልከት የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡናና የኢትዮ-ኤሌክትሪክ ድንቅ ተጨዋች ዮርዳኖስ አባይ አድናቆቱን ገልፆልሃል፤ በዚህ ዙሪያ ምን አልክ?
አቡበከር፡- ዮርዳኖስ አባይ የእውነት ደውሎ ጭምር ነው ያበረታታኝ፤ በርታ ከዚህ የበለጠ ደረጃም ላይ ትደርሳለህም ነው ያለኝ፤ ከእሱ ውጪም ሌሎች በርካታ የቀድሞም ሆኑ የአሁን ጊዜ እግር ኳስ ተጨዋቾች ከእነሱ ውጪም የቡድናችን ደጋፊዎችና ሌሎች ስፖርት አፍቃሪዎችም ለችሎታዬ ክብርና አድናቆትን ሰጥተውኝ እያሞገሱኝና እያበረታቱኝ ይገኛልና በዚሁ አጋጣሚ ሳላመሰግናቸው አላልፍም፡፡

ሀትሪክ፡- አቡበከር ናስር ቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ አይመጥነውም፤ ወደ ውጪ ወጥቶ ሊጫወት ይገባዋልም የሚሉ እየበዙ መጥተዋል፤ ይሄን ስትሰማ ምን አልክ?

አቡበከር፡- ይህን ለእኔ ችሎታ ካላቸው ከፍተኛ አድናቆት የተነሳ አሉ እንጂ በዛ ደረጃ የሚገለፁ ብዙ ተጨዋቾች ናቸው ሀገራችን ውስጥ እየታዩ የሚገኙት፤ የእውነቴን ነው አሁን ቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉን በሜዳ ላይ ተገኝተንም ሆነ በዲ.ኤስ.ቲቪ ተመልክተን ወደ ውጪ በመውጣት መጫወት የምንችል ልጆች በየክለቡ ውስጥ አለን፤ የዕድል አለመመቻቸት ብቻም ነው ወጥተን እንዳንጫወት ያደረግንና በቀጣይ ጊዜው ላይ ግን ብዙ ተጨዋቾቻችንን በውጪ ሀገር ሊጎች ላይ መመልከታችን አይቀርም፡፡

ሀትሪክ፡- በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ከእናንተ ውጪ ምርጥ ቡድንን ተመልክተሃል?

አቡበከር፡- አዎን፤ ያ ቡድንም ወልቂጤ ከተማ ይባላል፤ እነሱ በሰሞኑ ጨዋታ እኛን ስለፈተኑን ሳይሆን የመጀመሪያው ዙር ላይም የነበራቸውን ብቃት በሚገባ ተመልክቼ ነበርና ስለ ጥሩ እና አስገራሚ ስለሆነው ቡድናቸው መመስከርን እፈልጋለውኝ፡፡

ሀትሪክ፡- ወልቂጤ ከተማን በሁለተኛው ዙር የመክፈቻ ጨዋታ አሸንፋችኋል፤ ለቡና ውጤቱ አይገባውም ነበር የሚሉ አሉ?

አቡበከር፡- ያ ሊባል የቻለው እነሱ የጎል እድሎችን ሊፈጥሩ ስለቻሉ ነው፤ እኛም እኮ ጨዋታውን 2-0 ከመራን በኋላ ሶስተኛ ግብ ሊሆን የሚችል እድል አግኝተን በእኔ ላይ በተፈፀመ ጥፋት የእነሱ ተጨዋች መውጣት ሲገባው በቀይ ካርድ እንዳይወጣ የተደረገበት ሁኔታ አለና ያ ተጨዋች ከሜዳ ቢወጣ ሌላ ግብ ልናስቆጥር የምንችልበት እድሉ ስለሚኖረን ይህን ሳይ ለእኛ ውጤቱ ይገባናል ነው የምለው፡፡

ሀትሪክ፡- ወልቂጤን ያሸነፋችሁበት ውጤት ጣፋጭ ድል ነው?

አቡበከር፡- በጣም፤ ምክንያቱም እኛ ቡናማዎቹ ለሻምፒዮናነት ከመጫወታችን አንፃር ያ ውጤት ያስፈልገን ነበርና ጠንካራ ቡድን ደግሞ ተፈትኖ ሲያሸንፍ የሚሰጠው ከፍተኛም ደስታም አለና የእውነትም ጣፋጭ ድልን ነው ልንጎናፀፍ የቻልነው፡፡

ሀትሪክ፡- ኢትዮጵያ ቡና ቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉን በምን ውጤት ያጠናቅቃል?

አቡበከር፡- የሊግ ውድድሩ ገና በርካታ ጨዋታዎች የሚቀሩት ነው፤ ሻምፒዮናው ክለብም በዚህ ሰዓት የሚወሰንም አይደለምና ቀጣይ በሚኖሩን በርካታ ጨዋታዎች እያንዳንዱን ግጥሚያ በማሸነፍ የውድድር ዘመኑ ባለድል መሆንን ነው የምንፈልገው፡፡

ሀትሪክ፡- ከሬድዋን ወንድምህ ጋር አብረህ በአንድ ቡድን ውስጥ እየተጫወትክ ነው፤ ስለ እሱ ምን አልክ?

አቡበከር፡- በኢትዮጵያ ቡና ተጨዋችነቱ አሁን ላይ የመጫወት እድሉን እያገኘም ነውና እንደ ሌሎች ተጨዋቾች አቅሙን በደንብ አድርጎ አውጥቶ በመጫወት የተሻለ ተጨዋችነቱን ሊያሳይ ይገባዋል፤ ጥሩ ደረጃ ላይ ለመድረስም በርትቶ ሊሰራም ይገባል፡፡

ሀትሪክ፡- ኢትዮጵያ ቡና ውስጥ አሁን ላይ ምን የተለየ ነገር አለ?

አቡበከር፡- በጣም ደስ የሚል መንፈስን ነው እየተመከትን የምንገኘው፤ በተለይ ደግሞ ቡድናችን እንደ ቤተሰብም ለመተያየት መቻሉም ጥሩ ውጤትን እንድናመጣ እያደረገን ይገኛል፡፡

ሀትሪክ፡- ቃለ-ምልልሳችንን ልናጠቃልል ነው በምን እንቋጨው?

አቡበከር፡- ከፋሲል ከነማ ጋር የምናደርገውን ጨዋታ ለማሸነፍ ነው ወደ ሜዳ የምንገባው፤ የእኛ ቡድን ለሁሉም ቡድኖችም እኩል ግምት በመስጠትም ነው የሚታወቀው፤ ይሄ በመሆኑም በዛሬው ጨዋታ ለእኛ ሶስት ነጥብ የግድ ስለሚያስፈልገን ይህን ድል እናሳካለን፤ በቡድናችን ውጤት ማምጣት ላይም ሙሉ እምነቱ ነው ያለኝ፤ ከዛ በተረፈ በቡና ቆይታዬ በርካታ ግቦችን እንዳስቆጥር እየረዱኝ ላሉት ጓደኞቼና ለአሰልጣኜ እንደዚሁም ለኮቺንግ ስታፋችን ምስጋናን ማቅረብም እፈልጋለው፡፡

“ኢትዮጵያ ቡና በምርጥ አቋም ላይ የሚገኝና ጥሩ ቡድን ቢሆንም በነገው ፍልሚያ እጃቸውን ይሰጡናል” ሀብታሙ ተከስተ /ፋሲል ከነማ/

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...