መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሰልጣኝ ዘማርያም ወ/ጊዮርጊስ ድሬዳዋ ከተማን ለማሰልጠን ተስማማ
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችድሬዳዋ ከተማ

አሰልጣኝ ዘማርያም ወ/ጊዮርጊስ ድሬዳዋ ከተማን ለማሰልጠን ተስማማ

አጋራ
አጋራ

 

የፕሪሚየር ሊጉ አድማቂ መሰናበቱ
እርግጥ የሆነ ይመስላል

ድሬዳዋ ከተማ ውጤታማ አለመሆኑን ተከትሎ የክለቡ ቦርድ አሰልጣኝ ፍሰሃ ጥዑመ ልሳን ተሰናብቶ አሰልጣኝ ዘማርያም ወ/ጊዮርጊስ እንዲተካ ወሰነ።

ከድሬ ታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ የአሰልጣኝ ዘማርያም ቅጥር ይፋ ያልተደረገው ክለቡ ለአሰልጣኝ ፍሰሃ የሰጠው ሶስተኛ ደብዳቤ ሶስት ቀን ስላልሞላው ነው። አሰልጣኙ ለባህርዳሩ የ5 ሳምንት ጨዋታ ከቡድኑ ጋር ባህርዳር እያለ ክለቡ ለውይይት ወደ ድሬዳዋ እንዲመለስ ያዘዘው ሲሆን ነገ በክለቡ አመራሮች የስንብቱ ዜና እንደሚነገረው ይጠበቃል።

ነገር ግን አሰልጣኝ ፍሰሃ ጥዑመልሳን ከሃትሪክ ጋር በነበረው ቆይታ የክለቡ ቦርድ የተወሰኑ ጨዋታዎችን እንደሚያዩት ቃል እንደገቡለትና ወድ ድሬዳዋ ተመልሶ ከአመራሮቹ ጋር እንደሚወያይ በነበረው ጥሩ ያልሆነ ውጤት አንድ ጊዜ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንደደረሰው ገልጿል።
ክለቡ በ24 ወይም በ48 ሰአት ውስጥ ከአሰልጣኝ ዘማርያም ጋር እስከ ሰኔ 30/2014 ድረስ የሚያቆየውን ውል ይፈራረማል ተብሎ ይጠበቃል።በባህር ዳር ስታዲየም የሚካሄደው ውድድር የካቲት 12/2013 የሚቀጥል ሲሆን በቀጣዩ ሳምንት 12ኛ ጨዋታ ላይ ድሬዳዋ ከተማ አራፊ በመሆኑ አሰልጣኝ ዘማርያም አዲሱን ቡድኑን በደንብ እንዲመለከት እድል ይሰጠዋል ተብሎ ይገመታል።

ከጨዋታ በፊትና በኋላ በሚሰጣቸው አነጋጋሪ አስተያየት ትኩረት የሳበው አሰልጣኝ ፍሰሃ ጥዑመ ልሳን ከአሰልጣኝ ሰምዖን አባይ እጅ ድሬዳዋን ተረክቦ በሊጉ ባደረጋቸው 11 ጨዋታዎች 10 ነጥብና 5 የግብ ዕዳ ይዞ ወራጅ ቀጠና 11ኛ ደረጃ ላይ መገኘቱ ለስንብቱ ትልቁ ምክንያት መሆኑ ታውቋል።

የተሰናባቹ አሰልጣኝ ፍሰሃ ጥዑመልሳን
አነጋጋሪ አስተያየቶች….

“የአዲስ አበባ ስታዲየም አንግል በዘፈቀደ የተሰራ ነው፤ በርካታ ኳሶች የተመለሱብን በዚህ ምክንያት ነው”

—- —-

…ከጨዋታ በፊት.…

“የጅማ ስታዲየም ሜዳው ምርጥ መሆኑን ተናግሬያለሁ”

….በጨዋታው ከተሸነፉ በኋላ….

“የሜዳውን አስቸጋሪነት ለተጨዋቾቼ
ነግሬያቸዋለሁ”

——- ——

በወልቂጤ ከተማ ከተሸነፉ በኋላ…..

“ሜዳው የእግር ኳስ ሜዳ አይመስልም የወልቂጤ ተጨዋቾች በሜዳው ላይ እየወደቁ ሜዳውን ሪፈራል ሆስፒታል እድርገውታል”

እኚህን አነጋጋሪ አሰልጣኝ ከዛሬ ጀምሮ በባህርዳር ስታዲየም ከቡድናቸው ጋር እንደማናያቸው ተረጋግጧል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...