መነሻ ገጽ ሀዲያ ሆሳዕና “ሀድያ ሆሳዕና ይቆማል ብላችሁ አታስቡ፤ ቡድናችን ልክ እንደ ዝናብ መጥረጊያ ነው እየተንቀሳቀሰ የሚጫወተው”ሱሌይማን ሀሚድ /ሀድያ ሆሳዕና/
ሀዲያ ሆሳዕናቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎች

“ሀድያ ሆሳዕና ይቆማል ብላችሁ አታስቡ፤ ቡድናችን ልክ እንደ ዝናብ መጥረጊያ ነው እየተንቀሳቀሰ የሚጫወተው”ሱሌይማን ሀሚድ /ሀድያ ሆሳዕና/

አጋራ
አጋራ

 

ሀድያ ሆሳዕና ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉን በመቶ ፐርሰንት ያለ መሸነፍ ሪከርድ እየመራ ይገኛል።
ሀድያ በሊጉ ባደረጋቸው አራት ጨዋታዎች አራቱንም በማሸነፍ ብቸኛው ክለብ ሲሆን የዚህ ቡድን ጉዞ የት ድረስ ሊሆን ይችላል በሚለው ጉዳይ ብዙዎች እየተነጋገሩበት ይገኛል።
የሀድያ ሆሳህናን የሊግ ጉዞ አዳማ ከተማን ስላሸነፉበት ጨዋታ ቡድናቸው የት ድረስ እንደሚጓዝ እና ሌላን ተጨማሪ ጥያቄ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ የቡድኑ እና የብሄራዊ ቡድናችን ተጨዋች ለሆነው ሱሌይማን ሀሚድ አቅርቦለት ምላሽን ሰጥቶበታል።

በአዳማ ከተማ ቡድን ላይ ስለተቀዳጁት ድል እና መቶ ፐርሰንት ያለ መሸነፍ ሪከርዳቸውን ስለማስቀጠላቸው

“ከአዳማ ከተማ ጋር በነበረን ጨዋታ እኛ አሸናፊ የሆንነው ከእነሱ በተሻለ መልኩ ጥሩ ስለተንቀሳቀስን እና በውጤት ደረጃም የበላይነትን ስለወሰድንባቸውም ነው። በጨዋታው ይህን ድል በመጎናፀፋችንም ያለ መሸነፍ ሪከርዳችንን ልናስቀጥልበት ችለናል። ባገኘነው ጣፋጭ ድልም በጣም ተደስተናል”።

በጨዋታው ስለነበራቸው ጠንካራ ጎን

“በእዚህ ግጥሚያ ብቻ ሳይሆን ከመጀመሪያው የሊጉ ጨዋታ ጀምሮ ቡድናችን ያለው ጠንካራ ጎን ህብረቱና ፍቅሩ ነው። ሲኒየር እና ወጣት ተጨዋቾች አሉን በደንብ ይግባባሉ። እንደ ታናሽና ታላቅ ወንድም በመተያየት እና በመተሳሰብ እየተጫወቱ ስለሆኑም ይሄ መልካም ጎናችን ነው። ደስ በሚል ሁኔታም ከጥሩ ውጤት ጋር እየተጓዝንም ነው”።

ስለ ደካማ እና ክፍተት ጎናቸው

“አልፎ አልፎ ካልሆነ በስተቀር ይሄን ያህል አለብን ብዬ አላስብም። እነዛም ቢሆኑ ማች ፊትነሳችን ሙሉ ለሙሉ ሲመጣ የሚስተካከሉ ነው የሚሆኑት”።

የቀድሞ ክለባቸውን አዳማ ከተማን በተቃራኒነት ስለመፋለማቸው

“በጨዋታው የእኛ ብዙ ተጨዋቾች ከአዳማ ከተማ ሀድያን በመቀላቀል የመጣን እንደመሆናችንና ግጥሚያው ላይ ደግሞ የእነሱም ተጨዋቾች አንድ አስበው የሚመጡት ነገር እንዳለ ስላወቅን ትልቅ ጫና ነበረብን። ያም ሆነ ይህ ግን እኛ ለአዲሱ ቡድናችን ታማኝ ሆነን በመጫወት እና ክለቡንም በጥሩ ሁኔታ በማገልገል የግጥሚያው አሸናፊ መሆን ችለናል”።

ከዚህ በፊት ላለመውረድ ይጫወት የነበረው ክለብ አሁን ሊጉን ስለመምራቱ እና ይሄን ውጤታማነት ያስቀጥል እንደሆነ

“አዎን ቡድኑ የሚታወቀው ላለመውረድ በመጫወት ነበር። አሁን ግን ጥሩ ጥሩ እና ልምድ ያላቸውን ተጨዋቾች በመያዝ እና ቡድኑን እንደ አዲስ በመገንባት ጠንካራነቱን እያሳየ ይገኛል። ከዛ በተጨማሪም የበፊት ጊዜው በመቀየሩ አሁን ላይ ደግሞ ውጤታማ ቡድንን ስለገነባን ከዓላ እርዳታም ጋር የአሸናፊነት ድላችን ይቀጥላል”።

ስለ ቡድናቸው አጨዋወት

“ይሄን በሚገርም ሁኔታ ነው የምገልፀው። በጣም ያጠቃል፤ ይከላከላልም። ልክ መኪና ላይ እንዳለ እንደ ዝናብ መጥረጊያም ነው ወደ ግራም ወደ ቀኝም ኳሱን በመጫወትም የሚንቀሳቀሰውና ቡድኑ ካለው ጥሩ የቡድን መንፈስ ጋር ተዳምሮም በጥሩ ሁኔታ እየተጓዝን ነው”።

ሀድያ ሆሳዕና ሊቆም ይችላል ስለመባሉ

“ሰዎች የከዚህ ቀደሙንና ላለመውረድ የሚጫወተውን ቡድን አይተው ብዙ ሊሉ ይችላሉ። የአሁኑ ቡድን ግን ልምድ ያላቸውን እና ወጣት ተጨዋቾችን የያዘ በመሆኑና እንደ ቡድን በጥሩ ሁኔታም በመዋቀሩ በፍፁም አይቆምም። እንደውም ከዚህ የበለጠም ነው የሚጎዘው”።

በምን ውጤት የውድድር ዘመኑን እንደሚያጠናቅቁ

“ለሻምፒዮንነት ነው የምንጫወተው። ዓላ ካለም ዋንጫውን እናነሳለን”።

ለቡድኑ በቂ የሚዲያ ሽፋን እየተሰጠው አይደለም ስለመባሉ

“በሚዲያ ደረጃ ስለ እኛ በበቂ ሁኔታ ቢወራም ባይወራም ያ እኛ ላይ ለውጥ አያመጣም። አሁን ላይ እኛ ስራችን ላይም ነው አተኩረን የምንሰራው። በሊጉ የተሻለ ውጤትን ለማስመዝገብም የማንችልበት ምንም ምክንያት ስለሌለንም ያኔ ሁሉም ሚዲያ ስለ እኛ በስፋት እና በበቂ ሁኔታ ይዘግቡልናል”።

ለሀድያ ሆሳዕና እየሰጠ ስላለው ግልጋሎት

“በጥሩ ሁኔታ ነው አዲሱን ክለቤን እያገለገልኩት የምገኘው። ይሄ ሊሆን የቻለውም ለብሄራዊ ቡድናችን ተመርጬና ተጫውቼም ስለነበር ያ አሁን ላይ ጥሩ ለመንቀሳቀሴ ትልቅ ነገርን ሊፈጥርልኝ ችሏል”።

በመጨረሻ….

“ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉን በአሁን ሰዓት በጥሩ ውጤት ጀምረነዋል። ከእዚህ በኋላም ዓላ ረድቶን በጥሩ ሁኔታም ከድል ጋር እንዲያስጨርሰን እለምነዋለሁ”።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...