መነሻ ገጽ ሰበታ ከተማ ” ሞራላችን ተጎድቷል ፣ ስድሰት ወር ደሞዝ አልተከፈለንም ” የሰበታ ከተማ ተጫዋቾች
ሰበታ ከተማቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

” ሞራላችን ተጎድቷል ፣ ስድሰት ወር ደሞዝ አልተከፈለንም ” የሰበታ ከተማ ተጫዋቾች

አጋራ
አጋራ

በአሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሀም መብርሀቱ የሚመራው እና ማረፊያው በአለም ገና አቅራቢያ በሚገኘው ሀድሜስ ሆቴል ማረፊያቸውን ያደረጉት ሰበታ ከተማ ተጫዋቾች ከፍተኛ ቅሬታቸውን እያሰሙ ይገኛሉ ።

ሀትሪክ ስፖርት ከውስጥ ምንጮች ባገኘችው መረጃ መሰረት የቡድኑ ተጫዋቾች ላለፉት ስድስት ወራት ምንም አይነት ክፍያ እንዳልተፈፀመባቸው ለማወቅ ተችሏል ።

ከዚህ በተጨማሪም ከውስጥ ምንጫችን ለማረጋገጥ እንደቻልነው ቡድኑ ከ ቅዱስ ጊዮርጊሱ ጨዋታ በኋላ ምንም አይነት ልምምድን አለመስራታቸው ለማወቅ ችለናል ።

ከሌላ የውስጥ ምንጭ በደረሰን መረጃ የሰበታ ከተማ ነባር ተጫዋቾች እንዳሳወቁን ” በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በስምምነት ደሞዛችንን ብንቀንስን ቀሪ ክፍያዎች ያልተፈፀመልን ሲሆን በድምሩ የስምንት ወራት ክፍያዎች አልተፈፀሙልንም ” ሲሉ ነግረውናል ።

የሰበታ ከተማ የቡድን አባላት ከዚህ ጋር በተያየዘ ከፍተኛ የሆነ የሞራል ጉዳት እንደደረሰባቸው ሲገለፅልን ቡድን ነገ ረፋድ 4:00 ሰዓት ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር የአምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብራቸውን እንዲያካሂዱ የወጣው የውድድር መርሐ ግብር ያሳያል ።

በዚህ ሁሉ ችግር ውስጥ እያለፉ የሚገኙት የሰበታ ከተማ ተጫዋች አዲስ ነገር ካልተፈጠረ በቀር የነገውን ጨዋታ የማካሄዳቸው ነገር አጠራጣሪ መሆኑን ለማወቅ ችለናል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...