ፕሪሚየር ሊጉ በ3 ስታዲየሞች ብቻ ይካሄዳል

ፕሪሚየር ሊጉ በ3 ስታዲየሞች ብቻ ይካሄዳል

* መቐለ…ባህርዳር…አዲስ አበባ
ለ1ኛው ዙር ታስበዋል

የኢትዮጲያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የጠራው የውይይት መድረክ ዛሬ ተጀምሯል፡፡ 68 ክለቦች ከሚነጋገሩበት ጉዳዮች አንዱ የውድድር አካሄድን ይመለከታል፡፡ ውድድሮቹ በ3 ስታዲየም የሚካሄድ ሲሆን ከ1-5ኛ ሳምንት ያሉ ውድድሮች መቀለ ላይ ከ6 -10ኛ ሳምንት ያሉ ደግሞ ባህርዳር ላይ ከ11-15ኛ ሳምንት ደግሞ በአዲስ አበባ የማካሄድ ዕቅድ ተይዟል፡፡ የኮቪድ ምርመራ ወጪውን መንግስት እንዲችል የታሰበ ሲሆን ጨዋታ አይተው ብቻ የሚወጡ ጋዜጠኞች የምርመራ መረጃ እንዲያቀርቡ አይገደዱም ከጨዋታ በኋላ አሰልጣኞችን ቃለምልልስ የሚሰሩ ታች ትራኩ አካባቢ እንዲገኙ የሚፈቀድላቸው ጋዜጠኞችና ካሜራ ማኖች የኮቪድ 19 ምርመራ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ተብሏል፡፡እነኚህ ክለቦቹ ይወያዩበት እንጂ አይነኬና መንግስት የግድ ይተገበራል ያላቸው ናቸው

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport