በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ግሩም የሚባል አጀማመርን በማሳየት የሊጉ አናት ላይ የቆዩት ወልዋሎዎች በአምስት የስራ ዘርፍ ላይ የቅጥር ማስታወቂያ አውጥተዋል ።
ሀትሪክ ስፖርት ባገኘችው ማስረጃ ወልዋሎዎች የክለብ ስራ አስኪያጅ ፣ ቴክኒካል ዳይሬክተር ፣ የቡድን መሪ ፣ የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝን ጨምሮ በማርኬቲንግ ሀላፊነት ላይ የስራ ቅጥር ማውጣታቸውን ለማወቅ ተችሏል ።
ክለቡ እንዳሳወቀው ማስታወቂያ ከሚወጣበት ከነገው ቀን አንስቶ ባሉት ሰባት ተከታታይ የስራ ቀናት በክለቡ ጽ/ቤት ወይም በተወካይ በመገኘት ማመልከት እንደሚቻል አሳስበዋል ።
- ማሰታውቂያ -
ክለቡ ያወጣው ይፋዊ የስራ ማስታወቂያ ይመልከቱ 👇