አስተያየት| ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ 3-3 ወልቂጤ ከተማ

 

ቢጫ ለባሾቹ ወልቂጤን አስተናግደው 3-3 አቻ ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ። የወልቂጤ ከተማው አሰልጣኝ ደግአረግ ይግዛው አስተያየታቸውን ሲሰጡን የወልዋሎ ደጋፊዎች በተጫዋቾቻቸው ሲገልፁ በነበሩበት ተቃውሞ ምክንያት የወልዋሎ አሰልጣኝ አስተያየት ሳናካትት ቀርተናል።

አሁን ላይ የምታስመዘግበው ውጤት ለሁተኛው ዙር ዋስትና ነው ደጋአረግ ይግዛው (ወልቂጤ ከተማ)

ስለጨዋታው

የዛሬው ጨዋታ የመጀመሪያ ዙር ማጠናቀቂያ ጨዋታ ነው። ከኛ ቀደመው የተጫወ ቡድኖች ስለነቡሩ ያ የራሱ የሆነ ጫና አለው። ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ ጠንካራ ነው። እኛም ሆንን እነሱ ለሜዳው አዲስ ነን። ወደ ሜዳ አቅደን የገባነው አሸንፈን ሶስት ነጥብ ይዘን ለመሄድ ነው። አሁን ላይ የምታስመዘግበው ውጤት ለሁተኛው ዙር ዋስትና ነው። ቢሆንም ጨዋታው በጠበቅነው መንገድ ማስኬድ አልቻልንም። በመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ግብ አስተናግደን ተጫዋቾቼ ከጨዋታ ቅኝት ወጥተው ነበር። እነሱን መልሰን ወደ ጨዋታ መንገድ ለማስገባት ምንያክል ጫና ውስጥ እንደገባን እናንተም የተመለከታችሁት ነው። የመስመር እንቅስቃሲያቸውን ለመቆጣጠር ተቸግረን ነበር ሆኖም ግን ከመመራት ተነስተን ግብ ማስቆጠራችን የተጫዋቾቼን ጥንካሬ ያሳያል። ይህ ለኛ ትልቅ ነጥብ ነው ወልዋሎዎች ጨዋታውን ጨርሰውት ነበር ሆኖም የዳኛው ፊሽካ እስኪነፋ ያደረግነው ተጋድሎ አቻ እንድንወጣ አስችሎናል።

ስለጫላ እንቅስቃሴ

ጫላ ለብሄራዊ ቡድንም የሚያስፈልግ ልጅ ነው። ምክንያቱም እኛ ሀገር እንደሱ አይነት የመስመር ተጫዋች ማጥቃት ላይ ብቻ የማይሳተፍ የለም። ወደ ኋላ ተመልሶ የመከላከል ላይ ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ነው። ጫላ ግብ ላይ የመድረስ ችግር የለበትም። ወደ ግብ የመቀየር ችግር መጀመሪያላይ ነበረበት እነሱን ደግሞ ከጨዋታ ጨዋታ እያረመ መጥቷል ዛሬ ክለባችን መታደግም ችሏል።