የጨዋታ ቅድመ-ዕይታ | ሲዳማ ቡና ከ ሰበታ ከተማ

 

የ15ኛ ሳምንት የሊጉ መርሀ ግብር ከዛሬ አርብ ጀምሮ ሲካሄዱ ነገም በአንድ ጨዋታ መካሄዱን ይቀጥላል። በነገው እለት ከሚካሄዱ ጨዋታዎች መካከል ሲዳማ ቡናን ከ ሰበታ ከተማ የሚያገናኘው ጨዋታ እንደሚከተለው ዳሰነዋል። መልካም ንባብ።

ጨዋታ: ሲዳማ ቡና ከ ሰበታ ከተማ
የጨዋታ ቀን: ቅዳሜ የካቲት 14/2012
የጨዋታ ቦታ: ሀዋሳ ስታድየም
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ፌደራል አርቢትር ተፈሪ አለባቸው

በደጋፊዎቻቸው ፊት በሚያደርጉት ጨዋታ በቀላሉ ነጥብ የማይጥሉት ሲዳማ ቡናዎች በነገው ጨዋታ የፊት መስመራቸው ጥምረት በጉጉት ይጠበቃል።

በተለይም ቡድኑ ከመከላከል ወደ ማጥቃት በሚሸጋገርበት ወቅት የአዲስ ግደይ እና ሀብታሙ ገዛኸኝ ፈጣን እንቅስቃሰዎች ለሰበታ ከተማ ከወዲሁ ፈታኝ እንደሚሆን ይጠበቃል።

በሰበታ በኩል ለቡድኑ የማጥቃት እንቅስቃሴ ጎል በማስቆጠር ጉልህ ሚናን እየተጫወተ የሚገኘው ፍፁም ገብረ ማርያም ይጠበቃል።

ሰበታ ከተማዎች በመስመር ላይ ባመዘነው የማጥቃት እንቅስቃሴያቸው ጫናዎችን በመፈጠር የጎል እድሎችን ሲፈጥሩ ሲስተዋል በመጠኑም ቢሆን ለሲዳማ ቡና ተከላካዮች ሊፈትኑ እንደሚችል ሲጠበቅ በሁለቱም ቡድኖች የአጨዋወት ሁኔታን ተከትሎ የነገው ጨዋታ ለተመልካች አዝናኝ እንደሚሆን ይጠበቃል።

ሲዳማ ቡና በሜዳው ባደረጋቸው ያለፉት ሶስት ጨዋታዎች ማግኘት የሚገባቸውን ዘጠኝ ነጥቦች ሲይሳኩ በተጋጣሚ መረብ ላይ አስራ አንድ ጎሎችን ማሳረፍ ችለዋል።

በሌላ በኩል ሰበታ ከተማዎች ከሜዳቸው ውጪ በሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ላይ ደካማ ጉዞን እያደረጉ ሲገኙ በሊጉም ከሜዳቸው ውጪ ባደረጓቸው ጨዋታዎች ላይ ማሸነፍ ተስኗቸው ታይተዋል።

በጨዋታው በሲዳማ ቡና በኩል ዮናታን ፍስሀ በጉዳት የማይኖር ሲሆን በሰበታ ከተማ በኩል ደግሞ ዳዊት እስጢፋኖስ እና በኃይሉ አሰፋ በጉዳት እንዲሁም መስዑድ መሀመድ በግል ጉዳይ ምክንያት ጨዋታው የሚይመልጣቸው ይሆናል።

በዚህ ተጠባቂ ጨዋታ ላይ ባለሜዳዎቹ ድል የሚቀናቸው ከሆነ የሌሎች ቡድኖችን ጨዋታ ጠብቀው በሶስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ ሰበታ ከተማ የሊጉ የመጀመሪያውን ከሜዳ ውጪ ድል የሚያስመዘግቡ ከሆነ በደረጃ ሰንጠረዡ እስከ አራተኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጡ ይሆናል።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor