የጨዋታ ቅድመ-ዕይታ | ሰበታ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና

 

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከቅዳሜ አንስቶ መካሄዳቸውን ሲጀምሩ በነገው እለትም በመጨረሻ መርሀ ግብር የሁለቱን ቡድኖች ጨዋታ ያስተናግዳል።

በዚህ ሳምንት ከሚካሄዱት ጨዋታዎች መካከል በአዲስ አበባ ስታዲየም ሰበታ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና የሚያስተናግድበት ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል።

ጨዋታ: ሰበታ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና
የጨዋታ ቀን: ሰኞ የካቲት 09/2012
የጨዋታ ሰዓት: 10:00
የጨዋታ አርቢትር : ፌደ. አርቢትር ባሕሩ ተካ
የጨዋታ ቦታ: አዲስ አበባ ስታዲየም

በአዲስ አበባ ስታዲየም በሚካሄደው በዚህ ተጠባቂ መርሀ ግብር በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኙትን ኢትዮጵያ ቡናን ከ ሰበታ የምያገናኝ ይሆናል ::

ባለ ሜዳዎቹ ሰበታዎች በውበቱ አባተ እየተመሩ በተጋጣሚያቸው ላይ የጨዋታ ብልጫን በመውሰድ በሁለቱ የመስመር ክፍሎች የማጥቃት እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ሲሞክሩ ሲታይ በተለይም በባኑ ዲያዋራ ተከላካዮች አስጨንቀው የጎል እድሎችን ለመፍጠር ሲሞክሩ ይስተዋላል ::

ኢትዮጵያ ቡናዎች ኳስን ከግብ ጠባቂ በማስጀምር መስርተው በመውጣት ተጋጣሚ ላይ ጫና ለመፍጠር አስበው ሲንቀሳቀሱ በተከላካዮች በሚሰሩ ስህተቶች ለአደጋ ሲጋለጡ ይስተዋላል ::

በነገው ጨዋታ ላይ የኢትዮጵያ ቡና የተከላካይ ክፍል በሰበታ ፈጣን የፊት መስመር አጥቂዎች እንደሚፈተኑ ሲጠበቅ ኢትዮጵያ ቡናዎች የፊት መስመር አጥቂያቸውን አቡበክር ነስሮን ከጉዳት መልስ በወልቂጤ ከተማው ጨዋታ ቀይረው ሲያስገቡ በነገው እለትም በቋሚ አሰላለፍ ጨዋታውን እንደሚጀምር ይጠበቃል ::

ሰበታ ከተማ በአዲስ አበባ ስታዲየም ባደረጋቸው የሊጉ ጨዋታዎች መሸነፍ የቻሉት በመጀመሪያዎቹ የሊጉ ሁለት ሳምንታት ውጪ ሽንፈትን አላስተናገዱም ::

ኢትዮጵያ ቡና ባለፉት በሊጉ ካደረጎቸው አምስት ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻሉት በአንዱ ብቻ ሲሆን በነገው እለት የሚደረገው ይህ ጨዋታም በደረጃ ሰንጠረዡ ላይ ካለው የነጥብ መቀራረብ በጉጉት እንዲጠበቅ አድርጎታል ::

ሰበታ ከተማዎች በጨዋታው ድል የሚቀናቸው ከሆነ አሁን ላይ ካሉበት 12ኛ ደረጃ ወደ ስድስተኛ ከፍ ማለት ሲችሉ በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታውን በበላይነት ካጠናቀቁ ከወራጅ ቀጠናው በመውጣት 12ኛ ደረጃን ይይዛሉ ::

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor