መነሻ ገጽ ስሁል ሽረ የጨዋታ ቅድመ-ዕይታ | ስሑል ሽረ ከ ጅማ አባጅፋር
ስሁል ሽረዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ቅድመ-ዕይታጅማ አባጅፋር

የጨዋታ ቅድመ-ዕይታ | ስሑል ሽረ ከ ጅማ አባጅፋር

አጋራ
አጋራ

 

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ የሚደረጉ ሲሆን ነገ (ቅዳሜ) በሚደረጉ 3 ጨዋታዎች ሲጀመር እሁድ ደግሞ ቀሪ አምስት ጨዋታዎችን ያስተናግዳል።በነገው እለት ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከል ስሑል ሽረ ከ ጅማ አባጅፋር የሚያደርጉትን ጨዋታ ለእናንተ እንዲስማማ አድርገን እንደሚከተለው ዳሰነዋል። መልካም ንባብ።

ጨዋታ: ስሑል ሽረ ከ ጅማ አባጅፋር
የጨዋታ ቀን: ቅዳሜ ጥር 16/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ፌዴ. አርቢትር ተከተል ተሾመ
የጨዋታ ቦታ: ትግራይ ስታዲየም

በ3ተኛው ሳምንት በወልዋሎ ከተሽነፋ በኃላ በተከታትይ ስድስት ጨዋታዎች ያልተሸነፋት ስሑል ሽረዎች በሜዳቸው ቀዋሚ የሆነ አቋም ማሳየት የተሳነውን ጅማ አባጅፋርን ያስተናግዳል።

ጥሩ መነሳሳት ላይ ሚገኙት ስሑል ሽረዎች ከመሪው መቐለ 70 እንደርታ ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ለማጥበብ ባለፋት ጨዋታዎች ላይ እያሳዩት ያሉትን ብቃት ማስቀጠል ግድ ሚላቸው ይሆናል።በፈጣን የመስመር አጥቂዎቻቸው አብዱልለጢፍ መሐመድ እና
ዲዲዬ ሌብሪ አማካኝነት ግልፅ የግብ እድሎችን ሚፈጥሩት ስሑል ሽረዎች በነገው ጨዋታም ተመሳሳይ አቀራረብ ይዘው ሊገቡ እንደሚችሉ ይገመታል።ሆኖም ጠጣሩን የጅማ አባጅፋር ተከላካይ ክፍልን ለማለፍ ከመስመር ከሚነሱ የማጥቃት እንቅስቃሴ በተጨማሪ ከመሀል ተጫዋቾቻቸው በሚነሱ ኳሶች እድሎችን መፍጠር ግድ ሚላቸው ይሆናል።

ጠንካራ የተከላካይ ክፍል ያለው ቡድን በመገንባት ሚታወቁት ጳውሎስ ጌታቸው(ማንጎ) አዲሱ ክለባቸው ጅማ አባጅፋርንም ተመሳሳይ ባህሪ አላብሰውታል።በተለይ ቡድኑ ከሜዳው ውጪ ሲጫወት ያለው የመከላከል ቅንጅት ለዚህ ማሳያ ነው።ከኢትዮጵያ ቡና፣ወልዋሎ፣አዳማ ከተማ እና ሰበታ ከተማ ጋር ከሜዳቸው ውጪ የተጫወቱት ጅማዎች በሦስቱ ጨዋታዎች መረባቸውን ሳያስደፍሩ አንድ ነጥብ ይዘው መውጣት ችለዋል።በነገውም ጨዋታ ወደ ኃላ አፈግፍገው መልሶ ማጥቃት ላይ መሰረት ያደርገ አጨዋወትን ይጠቀማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ስሑል ሽረ በሜዳቸው 5 ጨዋታዎችን አድርገው በሥስቱ ጨዋታ አሸንፈው በአንድ ጨዋታ አቻ ሲለያዩ በአንዱ ደሞ ተሸንፈዋል። ጅማዎች በበኩላቸው ከሜዳቸው ውጪ በአንፃሩ ከሜዳቸው ውጭ ከተጫወቱት 4 ጨዋታዎች በሥስቱ ጨዋታዎች አቻ ሲለያዩ በአንዱ ሽንፈት አስተናግደዋል።

በአራቱ የሜዳቸው ውጪ ጨዋታዎች 3 ግቦችን ሲያስተናግዱ ሥስቱም ግቦች የተቆጠሩት በ8ተኛው ሳምንት ሰበታ ከተማን በገጠሙበት ጨዋታ ነበር።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፊፋ

ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የዝውውር ዕገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ጥሎበት የነበረው የተጫዋቾች...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

ዋልያዎቹ በአሜሪካ የወዳጅነት ጨዋታን ሊያደርጉ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ ሊያመራ ነው ነገር ግን የወቅቱ የብሔራዊ ቡድኑ...