መነሻ ገጽ ሰበታ ከተማ ቅድመ ዳሰሳ | ስሑል ሽረ ከ ሰበታ ከተማ
ሰበታ ከተማስሁል ሽረቅድመ ዳሰሳዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ቅድመ ዳሰሳ | ስሑል ሽረ ከ ሰበታ ከተማ

አጋራ
አጋራ

ስሑል ሽረ ከ ሰበታ ከተማ
የጨዋታ ቀን: ማክሰኞ ታህሳስ 28/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ፌደራል አርቢትር አዳነ ወርቁ
ቦታ: ትግራይ ስታድየም

7ተኛ ሳምንት ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በበዓል ቀን ና ከበዓል ማግስት በሚካሄዱ ስምንት ጨዋታዎች ቀጥሎ ይውላል።ባሳለፍነው ሳምንት ከወልቂጤ ከተማ ጋር ነጥብ የተጋሩት ስሑል ሽረዎች ጥሩ ወቅታዊ አቋም ላይ ሚገኙትን ሰበታ ከተማዎችን ሚያስተናግዱበትን ጨዋታ በዚህ መልኩ ዳስሰነዋል።

ተከታታይ 4 ጨዋታዎችን ማሸነፍ ያልቻሉት ስሑል ሽረዎች ግብ ጠባቂያቸው ወንድወሰን አሸናፊን በጉዳት ሙሉአለም ረጋሳን በግል ምክንያት ለነገው ጨዋታ ማይደርሱላቸው ተጨዋቾች ናቸው።ሰበታዎች በበኩላቸው ጉዳት ላይ የነበሩት አንተነህ ተስፋዬ ና ሳቪዮ ካቩጉን አሁንም ከጉዳታቸው አለማገገማቸውን ተከትሎ ወደ ሜዳ ማይመለሱ ሲሆኑ ቡድኑ ወላይታ ድቻን ባሸነፋበት ጨዋታ ጉዳት ያጋጠማቸው አስቻለው ግርማ፣ሲይላ አሊባድራ እንዲሁም ባኑ ዲያዋራ ለነገው ጨዋታ ማይደርሱ ተጨማሪ ተጨዋቾች ናቸው።

መስመር ላይ ትኩረት ያደርገ የማጥቃት ስልትን ሚጠቀሙት ስሑል ሽረዎች ነገም በተመሳሳይ የጨዋታ አቀራረብ ይዘው ሊቀርቡ እንደሚችሉ ይገመታል።በመስመር በሚደረጉ ማጥቃቶች ላይ ከፍተኛ ድርሻን ሚወስዱት ዲድየር ሌብሪ እና አብዱልለጢፍ መሀመድ በቅርብ ጨዋታዎች ላይ የፊት አጥቂነትን ሚናውን እየመራ ካለው ብሩክ ሓዱሽ ጋር ሚኖራቸው ቅንጅት ቡድኑ የግብ እድሎች መፍጠር እና መጠቀም ላይ ለሚኖረው እንቅስቃሴ ወሳኝ ሚኖ ሊኖራቸው እንደሚችል ይገመታል።አጥቀተው ለመጫወት በሚሞክሩበት ጊዜ መፈረካከስ ሚታይበት የስሑል ሽረ ተከላካይ ክፍል የነ በኃይሉ ቱሳ፣ፍፁም ገብረማርያም ታደለ መንገሻ እንቅስቃሴን በቅርበት መከታተል ካልቻለ ነገም እንደባለፋት ጨዋታዎች ተመሳሳይ እጣ ሊገጥመው እንደሚችል መገመት ከባድ አይሆንም።

ከሌሎች ጊዜዎች በተለየ እንደ ተጋጣሚ ቡድን ከጨዋታ ጨዋታ ተቀያያሪ የሆነ አጨዋወትን ለመተግበር እየሞከሩ ሚገኙት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለነገው ጨዋታ ይዘውት ሊገቡ የሚችሉትን የጨዋታ አቀራረብ መገመት ከባድ ቢሆንም ከሜዳቸው ውጪ እንደመጫወታቸው ጥንቃቄ ላይ መሰረት ያደርገ መልሶ ማጥቃትን ሊመርጡ እንደሚችሉ ይገመታል።መሀል ላይ የፈጣሪ ተጨዋቾች ችግር የሌላቸው ሰበታዎች ከመሀል በፈጣን ሽግግር ወደ መስመር በሚላኩ ኳሶች ደካማውን የስሑል ሽረ ተከላካይ ክፍልን ለማስከፈት ይሞክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ስሑል ሽረዎች እስካሁን በሜዳቸው 3 ጨዋታዎችን አድርገው ኢትዮጵያ ቡናን ሲያሸንፋ፣በወልዋሎ ተሸንፈው ከአዳማ ከተማ እኩል ተለያይተዋል።

ከፕሪምየር ሊጉ አብይ ኮሚቴ በተሰጣቸው መመሪያ መሰረት ስታድየማቸውን ማስተካከል ላይ መሆናቸውን ተከትሎ የሜዳ ጨዋታዎቻቸውን በአዲስ አበባ ስታድየም ላይ እያደረጉ ሚገኙት ሰበታዎች በበኩላቸው ከሜዳቸው ወጥተው ባደረጉዋቸው 2 ጨዋታዎች በቅዱስ ጊዮርጊስ ተሸንፈው አዲስ አዳጊውን ወልቂጤን ማሸነፍ ችለዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...