ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ በሁለት ምድብ ተከፍሎ 32 ክለቦች ሲሳተፉበት የቆየው የከፍተኛ ሊግ ውድድር ከአንድ ሳምንት በፊት መጠናቀቁ ይታወሳል።
ዛሬ 10 ሰዓት ላይ በሞቃታማዋ የምስራቅ ክልል በድሬዳዋ ስታዲየም የሁለቱ ምድቦች አሸናፊ አገናኝቷል፡፡
አቅሌስያስ ግርማ በ20ኛው ደቂቃ የአሸናፊነቷን ግብ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።
- ማሰታውቂያ -
ሁለቱ ክለቦች ከየምድባቸው አንደኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቃቸው በ2010 ዓመተ ምህረት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳትፎን ማረጋገጣቸው ይታወሳል።
ሁለቱን ክለቦች ተከትሎ በ2010 ዓመተ ምህረት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚሳተፈው ሶስተኛ ቡድን መቀሌ ከተማ መሆኑ ትናንት ታውቋል።
የምድብ ሀ አሸናፊ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ከምድብ ለ አሸናፊ ጅማ ከተማ ጋር ያደረጉት ጨዋታ በጅማ ከተማ 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
በዚህም መሰረት በሚቀጥለው ዓመት ከትግራይ ክልል ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲና መቀሌ ከተማ በፕሪሚየር ሊጉ ይሳተፋሉ።
ጅማ ከተማ ደግሞ የጅማ አባ ቡናን መውረድ ተከትሎ ከተማዋንና አካባቢውን በብቸኝነት ይወክላል።
በ2010 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአራቱም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች የሚገኙ ክለቦች ተሳትፎ ያደርጋሉ።