ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ “በባየር 2020 ወጣቶች ዋንጫ” ተካፋይ ልትሆን ነው

በጀርመን ባየርሙኒክ እግር ኳስ ክለብ በየዓመቱ በዓለም አገራት መካከል በሚካሄደው የባየር ወጣቶች ዋንጫ ውድድር ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ተካፋይ መሆን የሚያስችላትን ስምምነት ከክለቡ ጋር በተደረገው መሠረት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከባየርሙኒክ እግር ኳስ ክለብ ጋር በመተባበር የ”ባየር 2020 ወጣቶች ዋንጫ” ማጣሪያ ውድድር የካቲት 19 እና 20 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም ያካሂዳል፡፡
በጀርመኑ የባየርሙኒክ እግር ኳስ ክለብ በየዓመቱ በዓለም ላይ በሚገኙ አገራት መካከል በሚካሄደው የባየር ወጣቶች ዋንጫ ውድድር በዘንድሮ ዓመት ባየር 2020 ወጣቶች ዋንጫ በሚል የሚካሄድ ይሆናል፡፡ በዚሁ ውድድር የኢትዮጵያ ከ16 ዓመት በታች ታዳጊ ቡድን ተካፋይ ለመሆን የሚያስችለውን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

ይህንን ኘሮግራም በተመለከተ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቴክኒክና ልማት ዳይሬክተር የሆኑት ኢንስትራክተር መኮንን ኩሩ በሰጡት አስተያየት በማጣሪያ ውድድሩ ለሁለቱ ከተማ መስተዳድርና ዘጠኙ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ከሁለት ወራት በፊት ተሳታፊ ወጣቶችን እንዲያሳውቁ ጥሪ የተደረገ ሲሆን ለተሳትፎ ትኩረት ከተደረገባቸው ነጥቦች ዋነኞቹ በክልሉ ከሚገኙ የግል እግር ኳስ ትምህርት ቤቶች፣ የመንግሥት ስፖርት አካዳሚዎች እንዲሁም ሌሎች ትምህርት ቤቶች ታዳጊዎችን በመምረጥ ተሳታፊ መሆናቸውን እንዲያሳውቁ ጥሪ ተደርጓል፡፡
ጥሪ ከተደረገላቸው መካከል መካከል አዲስ አበባ ፣ ቤኒሻንጉል፣ አማራ፣ ኦሮሚያ ፣ ደቡብ እና ሱማሌ እንዲሁም የኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት አካዳሚ እስካሁን ባለው መረጃ ተሳታ እንደሚሆኑ የገለፁ ሲሆን የቀሩት ክልሎች በእለቱ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በውድድሩ እያንዳንዱ ቡድን 10 ተጫዋቾች (ፋትሳል ቡድን) ተሳታፊ የሚያደርግ ሲሆን በጨዋታው ደንብ መሠረት በግማሽ ሜዳ ላይ እንዲካሄድ ይደረጋል፡፡ ዳኝነትን በተመለከተ በፌዴሬሽኑ ዳኞች የሚመራ ይሆናል፡፡ በአጠቃላይ በውድድሩ 14 ምድቦች በየአንዳንዱ 10 ተጫዋቾ በአጠቃላይ 140 የሚሆኑ ወጣቶች እንደሚሳተፋ ይጠበቃል፡፡

ውድድሩ የካቲት 19 እና 20 በሁለቱ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን በመጨረሻው ማጣሪያ የተሻለ ችሎታ እና አቅም ያላቸው ተመርጠው 10 ተጫዋቾች ወደ ጀርመን ባየር የሚጓዙ እንደሚሆን እና በዚህ ውድድር መክፈቻ ፌብሩዋሪ 27/2020 የባየርሙኒክ እግር ኳስ ክለብ ከተመሰረተ 120ኛ ዓመቱን የሚያከብርበት ቀን በመሆኑ ለውድድሩ ክለቡ ትልቅ ትኩረት በመስጠት ትጥቆችን በማዘጋጀት ለወጣቶች ጥሩ እድል የሚፈጥር በመሆኑ እና የታዳጊዎቹ ጨዋታ የመዝናኛ ኘሮግራም ስለሚሆን የእግር ኳስ ቤተሰቡ በእለቱ ተገኝቶ በመደገፍ የኘሮግራሙ ድምቀት በመሆን እንዲከታተል በማለት ጥሪያቸውንም አቅርበዋል፡፡

አክለውም የባየርሙኒክ እግር ኳስ ክለብ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በጋራ በመተባበር በእግር ኳሳችን ላይ በርካታ ሥራዎችን ለመስራት ስምምነት መድረሱን ገልጸዋል፡፡

Via- EFF

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor