በዋቢ ሸበሌ እየተካሄደ ያለውና በፕሪሚየር ሊጉ የመጀመርያዎቹ 11 ሳምንት ጨዋታዎች ዙሪያ ግምገማ ላይ ብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ ላይ ጠንካራ ትችት እየተሰነዘረ ነው።
ኢንተ.ረዳት ዳኛ ክንዴ ሙሴ እንደተናገረው “”የዛሬ 22 አመት ፕሮጀክት ያጫወተ ዳኛ በ1995 ፕሪሚየር ሊግን ያጫወተ ዳኛ አሳድጌያለሁ ማለት ምን ማለት ነው?” ሲል ጠይቋል።
ረዳት ዳኛው እንደሚለው “የዳኞች ኮሚቴ ሰርቷል ብዬ አላምንም የቀረበው ሪፖርት ጉባኤውን አይመጥንም የዛሬ 22 አመት ፕሮጀክት የመራ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ የዳኘን አሳድጌያለሁ ማለት ምን ማለት ነው?” ሲል ተናግሯል።
ኢንተርናሽናል አርቢትር ቴዎድሮስ ምትኩ በበኩሉ” ሚዲያው እየተነሳ ሲተች የመሰለውን ሲለጥፍ ነው የሰማሁት የውጪ ሚዲያ በዚህ ህግ መሰረት እያለ ነው እዚህ ሀገር ግን እንዲህ አይደለም የሙያ ኢቲክሱ ከፈቀደ ምን ማድረግ ይቻላል?” በማለት የሚዲያውን ትችቶች ተቃውሟል። ስለዳኞች መብት የተከራከረው አርቢትር ቴዎድሮስ”የአዲስ አበባ ዳኞች ላይ ርምጃ መውሰዱ ከፍቷል ተከራካሪ የለውም ተብሎ ይመስለኛል ይሄ መታረም አለበት በኛ በዳኞች በኩልም ጠንክረን ልንሰራ ይገባል ከነ ሊዲያና በአምላክ ጋር ልምምድ አልሰራምጭየሚል ዳኛ መኖሩ ቅር ያሰኛል አሞኝንኳ ከነሊዲያና በአምላክ ጋር ስሰራ እፈውሳለሁ” ብሏል።
በብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ የተቀጣው ፌዴራል አርቢትር አሸብር ” በተላለፈብኝ ቅጣት አዝኜ ይግባኝ ጠይቄ ምላሽ አጥቻለሁ ሚዲያ ሞራሌን ነክቷል ሙያ ለምን አይቀርም ተብዬ ተወርፌያለሁ የተቀጣሁበት ጨዋታ ዝርዝር ተገቢ አልነበረም በውሳኔው አዝኛለሁ ጥሩ ሰርተሃል ያለኝ ኮሚሽነር ወጥቶ የጻፈብኝ ሪፖርት ተገቢ አይደለም የስነ ልቦና ጉዳት ደርሶብኛል በሙስና ወይም በወንጀል የተባረርኩ ይመስል ጉዳት ያደረሰ ሪፖርት ቀርቦብኛል የጨዋታ ኮሚሽነሩ በደል አድርሶብኛል ይሄም ትልቅ ቅሬታ ፈጥሮብኛል”በማለት የተሰማውን ቅሬታ ገልጿል።
አስተያየት ይስጡ