የጅማ አባ ጅፋሩ ጠንካራው የተከላሀዐወትስፍራ ተጨዋች ሀወት ገብረሚካኤል ክለባቸው
በአፍሪካ ቶታል ቻምፒዮንስ ሊግ የግብፁን
አልአህሊ በሚፋለምበት የዐርቡ የመልስ ጨዋታ
ተጋጣሚያቸውን አሸንፈው ወደ ተከታዩ ዙር
ለማለፍ እንደተዘጋጁ አስተያየቱን ለሀትሪክ
ስፖርት ጋዜጣ ሰጥቷል፡፡
ጅማ አባጅፋር በአፍሪካ የቶታል ቻምፒዮንስ
ሊግ የክለቦች ጨዋታ የመጀመሪያ ግጥሚያውን
ከአልአህሊ ጋር ዐርብ ዕለት አድርጎ 2ለ0
የተሸነፈ ቢሆንም ይህን ውጤት መቀልበስ
እንደሚቻል የቡድኑ ተጨዋቾች ጭምር
አስተያየታቸውን እየሰጡ ይገኛል፡፡
የጅማ አባ ጅፋርና የአልአህሊን የመልስ
ጨዋታ በተመለከተና ስለመጀመሪያው ግጥሚያ
ከቡድኑ ተጨዋቾች መካከል ሀወትን አናግረነው
አጠር ባለ መልኩ ምላሹን ሰጥቷል፡፡
ከግብፁ አልአህሊ ተጫውተው 2ለ0
ስለተሸነፉበት ጨዋታና ስለነበራቸው አቋም?
‘‘የአፍሪካውንና የግብፁን ታላቅ ክለብ
አልአህሊን ተፋልመን 2ለ0 የተሸነፍንበት ጨዋታ
ለእኛ ከነበረን ጥሩ እንቅስቃሴ አንፃር እንደዚሁም
በውድድሩ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ከመሳተፋችን
አኳያ ሳየው ጥሩ የሚባል ነው፤ ውጤቱ
ጨዋታውን የሚገልፀው አልነበረም፤ የዐርቡን
ግጥሚያ ያደረግነው ከዚህ ዘግይተን በመሄድና
በተጨማሪ ደግሞ የ4 ሰዓት ተጨማሪ የመኪና
ጉዞ በማድረግ ያለ ብዙ እረፍት ነው፤ ያም ሆኖ
ግን በጨዋታው ብዙ ድካም ሳይታይብን ጥሩ
ልንጫወት መቻላችን የቡድናችንን ተጨዋቾች
እንዳመሰግናቸው አድርጎኛል፤ በዐርቡ ጨዋታ
እኛ ከተጋጣሚያችን በኳስ ቁጥጥሩ የተሻልን
ነበርን፤ ሆኖም ግን በጥቃቅን ችግሮች ጎል
ገብቶብን ልንሸነፍ ችለናል”፡፡
- ማሰታውቂያ -
በጨዋታው አልአህሊዎች ስለነበራቸው
አቋም?
“አልአህሊዎች ከእኛ ጋር ሲጫወቱ የነበራ
ቸው አቋም ጥሩ ሊባል የሚችል አይደለም፤
በማጥቃቱ በኩል ጫና ፈጥረው ሊጫወቱ
አልቻሉም፤ እኛ በሚገባ ተቋቁመናቸው ተጫ
ውተናልና እንደጠበቅናቸው አላገኘናቸውም”፡
ስለ ዐርቡ የመልስ ጨዋታ
“የግብፁን አልአህሊ የምንፋለምበት የዐርቡ
ጨዋታ ለእኛ በጣም ወሳኝ ነው፤ ጎሎች
የሚያስፈልጉን ስለሆነ ሙሉ 90 ደቂቃውን
አጥቅተን ነው የምንጫወተው፤ በመጀመሪያው
ግጥሚያ 2ለ0 ተሸንፈን የመጣን ቢሆንም ይህን
ውጤት ቀልብሰንና ተጋጣሚያችንን አሸንፈን
ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ተዘጋጅተናል”፡፡