በዘንድሮው የውድድር ዓመት በሲዳማ ቡና ጎልተው መውጣት ከቻሉ መካከል አንዱ የሆነው አበባየሁ ዮሐንስ በሲዳማ ቤት ውሉን ማራዘም ችሏል ።
አበባየሁ ዮሐንስ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ከአዲስ ግደይ እና ከሀብታሙ ገዛኸኝ ጋር የነበራቸው ጥምረት በሊጉ ሌላ ድምቀት ሲሆን በሊጉ ሲዳማ ቡና በርካታ ጎሎችን በተጋጣሚው ላይ ሲያሳርፍ የራሱን አስተዋፅዖ ማበርከት ችሏል ።
ሲዳማ ቡና በዛሬው ዕለት የግብ ጠባቂውን መሳይ አያኖ ውልም ከሰዓታት በፊት ማራዘሙ የሚታወቅ ነው ።