መነሻ ገጽ መቐለ ከተማ ሪፖርት | መቐለ ከተማ በሜዳው በግብ ተንበሽብሾ አሸንፏል
መቐለ ከተማሪፖርትአርባምንጭ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ሪፖርት | መቐለ ከተማ በሜዳው በግብ ተንበሽብሾ አሸንፏል

አጋራ
አጋራ

በሁለተኛው ዙር የኢትዮጵያ ኘሪሚዬር ሊግ 16ኛ ሳምንት መርሃ ግብር መቆለ ከተማ በሜዳው የሊጉ ግርጌ የሚገኘውን አርባምንጭ ከተማ ባስተናገደበት ጨዋታ በሰፊ የጎል ልዩነት አሸንፏል፡፡

ልክ 9:00 ሲል በግዙፉ ትግራይ ስታድየም መቆለ ከተማን ከአርባምንጭ ከተማ ያገናኘው የሁለተኛው ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ በበርካታ ተመልካች ታጅቦ ሲጀምር የሜዳው ድባብ እንደ ተለመደው ባይሞላም በግምት 25ሺ የሚሆን ደጋፊ ታድሟል፡፡በጨዋታው የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ በባለሜዳዎቹ መቆለ ከተማዎች በኩል በአንደኛ ዙር ከሚታዎቁበት ኳስን በረጅሙ ለፊት መስመር ተሰላፊዎች በማሻገር ግብ ለማስቆጠር የሚጫወቱት ባለሜዳዎቹ ዛሬ በአንፃራዊ የተለዩ ሁነው በአጭር የኳስ ቅብብል ተጋጣሚያቸው ሲፈትኑ በጥብቅ መከላከል የሚታወቁት ባለሜዳዎቹ ተጭነው በማጥቃት ላይ አተኩረው ሲጫዎቱ አምሽተዋል፡፡

እንግዳዎቹ አርባምንጭ ከተማዎች ከሜዳቸው ውጭ እንደመጫዎታቸው መከላከልን መሰረት አድርገው በደርሶ መልስ ግብ ለማስቆጠር ቢጫዎቱም ሳይሳካላቸው ገና በጨዋታው መጀመሪያ በ2ኛው ደቂቃ በቢስማርክ የግል ብቃት ግብ አስተናግደዋል፡፡የመሃል ሜዳውን ክፍል በበላይነት የወሰዱት ባለሜዳዎቹ የመሃል አማካኙ ተጨዋቻቸው ሚካኤል ደስታ(ጣልያን) ደምቆ በማሸበት ጨዋታ ልምዱን በመጠቀም ከአማካኝ ስፍራ ወደ ግብ የሚሻግራቸው ኳሶች የተሳኩ ነበሩ፡፡

የኢትዮጵያን ኘሪሚዬር ሊግ ጠንቅቆ የሚያውቀው ሚካኤል ደስታ የመቀለ ማሃል ክፍል ወሳኝ ተጫዋቾቹ አመለ ሚልክያስ በቅጣት ጋቶች ፓኖም በጉዳት ሳይዝ ቡድኑ ወደ ሜዳ ቢገባም ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ባለሜዳዎቹ እንዲወስዱ የነበረው ሚና ትልቅ ነበር፡፡

በጨዋታው ፍፁም የበላይነት የነበራቸው ባለሜዳዎቹ ብዙም ሳይቆዩ የመጀመሪያዋን ግብ ባስቆጠረው ፒስማርክ አማካኝነት በ16ኛው ደቂቃ ሌላ ጎል በማስቆጠር ጨዋታውን 2ለምንም መምራት ሲችሉ እንግዳዎቹ አዞዎቹ አጠፋውን ለመመለስ ቢንቀሳቀሱም የተሳካ የግብ ሙከራ ሳያደርጉ ከእረፍት መልስ በ48ኛው ደቂቃ ኮኮብ ሆኖ ያመሸው ፒስማርክ ሀትሪክ የሰራባትን ግብ ሲያስቆጥር የባለሜዳዎቹ አዲሱ ፈራሚ ጋናዊ ፉሴይኒ የማሳረግያ ግብ በ55ኛው ደቂቃ በማስቆጠር እንግዳውን አርባምንጭ ከነማን 4ለ ምንም በማሸነፍ በዋንጫው ፍክክር በትክክልም ተሳታፊ መሆናቸውን ያሳዩበትን ውጤት አስመዝግበዋል፡፡

አስተያየት=>አፖንግ ቢስማርክ

በጨዋታው 3 ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ በመስራት ጎልቶ ያመሸው አፖንግ ቢስማርክ  በመጀመሪያው ዙር በድምሩ 10 ግብ አግብተን ማጠናቀቃችን የሚታወስ ነው፡፡ በዚህኛው ዙር በዛሬው ጨዋታ 4 ግብ አስቆጥረናል፡፡የዛሬው ውጤት ጠንክረን በመስራታችን በአሁኑ ዝውውር ወደ ክለቡ የፈረሙ የአዳዲስ ተጫዋቾች ውጤት ጭምር ነው፡፡ከእግዚአብሔር ጋር ለዋንጫ የማንጫወትበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ለደጋፊውም ክብር አለኝ፡፡

የአሰልጣኞች አስተያየት

☞እዮብ ማለ -የአርባምንጭ ከተማ አሰልጣኝ

በጨዋታው ጥሩ ተጫውተናል በተጋጣሚያችን የግብ ክልል ስንገባ ምን ማድረግ እንዳለብን ተቸግረን አምሽተናል፡፡በምናጠቃበት ወቅት ከሜዳችን ነቅለን ስንወጣ በተካላካዮቻችን ስህተት በመስራታቸው መቀለዎች በመልሶ ማጥቃት ከኛ የተሻሉ ስለነበሩ ግብ አስቆጥረውብን ተሸንፈናል፡፡

☞ጎይቶኦም ሃይለ- የመቀለ ከተማ ምክትል አሰልጣኝ

በመጀመሪያው ዙር የነበረብንን የአጨራረስ ችግር በትክክልም ያረምንበትን ግቦች አስቆጥረን አሸንፈናል፡፡አሁን የምናስበው ቀጣይ አዲግራት ስታዲዬም ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ የሚጠብቀንን ጨዋታ ነው፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...