መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ ፌዴሬሽኑ የ2009 ዓ.ም ውድድሮችን በልዩ የሽልማት ስነስርዓት ለማከናወን እየሰራ መሆኑን ገለፀ ፤የዘንድሮ ሻምፒዮን ለሚሆነው ቡድን የሚሰጠው የገንዘብ መጠን ከፍ ለማድረግም ታቅዷል
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ፌዴሬሽኑ የ2009 ዓ.ም ውድድሮችን በልዩ የሽልማት ስነስርዓት ለማከናወን እየሰራ መሆኑን ገለፀ ፤የዘንድሮ ሻምፒዮን ለሚሆነው ቡድን የሚሰጠው የገንዘብ መጠን ከፍ ለማድረግም ታቅዷል

አጋራ
አጋራ

በመጨረሻው የሥራ ዘመን ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2009 ዓ ም ውድድሮችን በልዩ የሽልማት ስነስርዓትና በከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት ለማከናወን እየሰራ መሆኑን ገለፀ።
ፌዴሬሽኑ ማምሻውን ለሁሉም የመገናኛ ብዙሃን በኢ-ሜይል እንዳሳወቀው በ2009 ዓ.ም የውድድር ዘመን ቀደም ሲል ከነበሩት ውድድሮች ቁጥራቸውን በመጨመር የስድስት ሊጎች ውድድሮች በማደራጀትና ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ እንዲከናወን ማድረጉን ገልፆ በእነዚህ ውድድሮች አሸናፊና ኮኮብ ለሚሆኑ ተወዳዳሪዎችና አሰልጣኞች ዳኛች የዋንጫና የሜዳሊያ ሽልማት እንዲሁም የገንዘብ አሰጣጥ ስነስርዓቶችን ለማከናወን ዝግጅቱን የተለያዩ ድርጅቶች ስፖንሰር በማድረግ ገንዘብ የማሰባሰብ ስራ ሲሰራ መቆየቱንና ይሄንንም በተመለከተ በ2009ዓ.ም እየተካሄዱ የሚገኙትን ውድድሮችን የኮኮቦችን ሽልማት በተናጠል ከመስጠት ይልቅ በተሻለ ስነስርዓት ማከናወን አስፈላጊ እንደሆነ የገለፀው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በዚህ መሰረትም እንደ አለም አቀፉና አህጉር አቀፍ ውድድሮች ባማረና ደረጃውን በጠበቀ ሆቴል ለማከናወን በተለያዩ ሊጎች ኮኮብ የሆኑትን በተናጠል ሳይሆን በአንድ ቦታ እንዲሸለሙ ለማድረግ፤ለአሸናፊዎች የሚሰጠውን የገንዘብ ሽልማት ካለፉት ዓመታት ከፍ ለማድረግና የገንዘብ ሽልማት የሚሰጡ ድርጅቶችን በበለጠ ሁኔታ ከኮከብ ተሸላሚዎች ጋር ለማቀራረብና በቀጣይም ሊጉ ድጋፍ እንዲያገኝ ለማስቻል በአጠቃላይ ከሽልማት ጋር በተያያዘ አዲስ አብዮት ለማጣት ትልቅ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
የዋንጫና የሜዳሊያ ሽልማቶችን ግን በጨዋታ ፍፃሜዎች ላይ መሆኑን በኢ-ሜይል የገለፀው ፌዴሬሽኑ ዝርዝር ሁኔታዎችን በቀጣይ እንደሚገልፅ ለሚዲያ አካላት ከላከው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...