መነሻ ገጽ ዜናዎች ፋሲል ከነማ የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ቃል ተገባለት፡፡
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግፋሲል ከተማ

ፋሲል ከነማ የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ቃል ተገባለት፡፡

አጋራ
አጋራ

 

ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ቡድንን ለማጠናከር የደጋፊ ማኅበሩ የገቢ ማሰባሰብና ሀብት ማፈላለግ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ማኅበር ሊቀ መንበር ኃይለማርያም ፈረደ ለአብመድ እንደተናጋረው ቡድኑን ለማጠናከር ማኅበሩ በሀብት ማፈላግ ሥራ ላይ አተኩሮ እየሠራ ነው፡፡
እንደ አቶ ኃይለማርያም ገለጸ የአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ፋሲል ከነማ የእግር ኳስ ቡድንን ለማጠናከር የ10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ከሰሞኑ ቃል ገብቷል፤ ከኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች መካከል ደግሞ አቶ ወርቁ ዓይተነው ትናንት ከደጋፊ ማኅበሩና ከቡድኑ አባላት ጋር ተነጋግረው 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡

ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ቡድን በገንዘብ አቅሙ ተጠናክሮ የሚያስፈልገውን ሁሉ ማሟላት ወደሚችልበት ደረጃ እንዲደርስ ደጋፊ ማኅበሩ የድጋፍ የመነሻ ሐሳቦችን (ፕሮፖዛል) ቀርጾ ለተቋማትና ግለሰቦች እየሰጠ መሆኑን የተናገረው ሊቀ መንበሩ ከተናጠል የድጋፍ ጥያቄው በተጨማሪ እንደ ጎዳና ላይ ሩጫ ያሉ የገቢ ማስገኛ ዝግጅቶች መታቀዳቸውንም አስታውቋል፡፡
የጎዳና ላይ ሩጫው መቼና የት፣ በማን ስፖንሰር አድራጊነት እንደሚካሄድ ወደፊት እንደሚያስታውቁ የገለጸው አቶ ኃይለማርያም ሌሎችንም ተጨማሪ የገቢ ማስገኛ ዝግጅቶችን በመፍጠር ፋሲል ከነማ እንዲጠናከር እንደሚሠሩ አመልክቷል፡፡

ፋሲል ከነማ የዘንድሮውን የኢትዮጵያ የወንዶች እግር ኳስ ፕሪሚየር ሊግ እየመራ ይገኛል፤ በውጤታማነቱ እንዲቀጥል ደግሞ የገንዘብ አቅሙን ማጎልበትና የተጫዋቾቹን በራስ መተማመን መገንባት፣ የስታዲዬሙን ደረጃ ማሳደግ ያስፈልገዋል፡፡ ለዚህም ከቡድኑ በተመጨማሪ የደጋፊ ማኅበሩ ጉልበት ሆኖ እየሠራ እንደሆነ ነው ሊቀ መንበሩ ያመለከተው፡፡

Via-amma

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...

መቐለ 70 እንደርታዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ዘርአይ ሙሉ በቴክኒክ አማካሪነት ወደ ፕሪምየር ሊጉ ተመልሷል

አሰልጣኙን ያሰናበተው መቐለ 70 እንደርታ ሌላ ሹመትን ፈፅሟል። በያዝነዉ የዉድድር አመት ደካማ...