ፋሲል ከነማ የተጫዋቻቸውን ውል በማራዘሙ ቀጥለዋል !

 

በፕርሚየር ሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪነታቸውን እያሳያ የሚገኙት ፋሲል ከነማዎች የተጫዋቻቸውን ውል በማራዘሙ ቀጥለዋል ።

ሀትሪክ ስፖርት ከታማኝ ምንጯ ባገኘችው መረጃ ከቀናት በፊት የአምሳሉ ጥላሁንን ውል ማራዘማቸውን ስታደርስዎ በዛሬው ዕለት ደግም የሁለት ተጫዋቾቻቸውን ውል አድሰዋል ።

በዘንድሮው የውድድር ዓመት የማሊያዊው ግብ ጠባቂ ሳማኪ ተጠባባቂ የነበረው ቁመተ መለልዎ ቴዎድሮስ ጌታሁን በአፄዎቹ ቤት ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት የሚያቆየውን ውል አራዝሟል ።

ሌላኛው በዛሬው ዕለት በክለቡ ለመቆየት የተስማማው የመሐል ክፍል ተጫዋቹ መጣባቸው ሙሉ በአፄዎቹ ቤት ለመቆየት የተስማማ ተጫዋች ነው ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor