ፊፋ በአፍሪካ የትምህርት ቤቶች ሻምፒዮና ሊያዘጋጅ ነው።

 

በትንናትናው እለት በ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዋና ከተማ ኪንሻሳ በተካሄደው የFIFA አውደ ጥናት ይፋ በተደረገው መረጃ መሰረት በአፍሪካ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ በሁለቱም ጾታዎች የሚካሄድ የትምህርት ቤቶች የእግርኳስ ውድድር FIFA ሊያዘጋጅ መሆኑ ታውቋል።

ለውድድሩ የሚያልፉ ትምህርት ቤቶችን ለመለየት በየዞኑ ተከፋፍለው ከየአንዳንዱ ሀገር ሁለት ሁለት ትምህርት ቤቶች ተወክለው ማጣሪያቸውን የሚያደርጉ ሲሆን የመጀመሪያው ውድድር እ.ኤ.አ በሀምሌ 2020 በቤኒን አዘጋጅነት የሚካሄድ ይሆናል።

FIFA እ.ኤ.አ በ2016 የጀመረው የFIFA Forward ፕሮጀክት አንድ አካል መሆኑ የታወቀው ይህ የትምህርት ቤቶች ውድድር ለበርካታ አፍሪካ ታዳጊዎች በትልቅ ደረጃ የመጨወት እድል እንደሚፈጥር ይጠበቃል። በሀገራችም ኢትዮጵያዊ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችም በውድድሩ ለመሳተፉ በሚያደርጉት ሂደት ለአያሌ ተማሪዎች በር ይከፍታሉ ተብሎ ይጠበቃል።