በኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ታሪክ ከሚጠሩ ግለሰቦች አንዱ ነው። ለእግርኳሱ አዲስ የሆነ ታዳጊ ተጫዋችን ለስፖርቱ ብቅ ሊል ሲል ከስፖርተኛው ጋር አብሮ ብቅ የሚል ስም አለ፣ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ አንጋፋ ተጫዋቾችን ትውልድ ፣ ዕድገት ስም እና ክለባቸውን ለማስታወስ የእሱ ተባባሪነት ይጠየቃል፣፣ በቅንነት እና በተባባሪነት ለሌሎች የሙያ ባልደረቦች ትብብሩን ያደርጋል።
_
……ከልጅ እስከ አዋቂ፣ ከጀማሪ እስከ አንጋፋ፣ሴትም የወንድም፣ ወጣትም ተጫዋቾችን ጠንቅቆ ያውቃቸዋል፣ እድገት እና አመጣጣቸውንም በዝርዝር የሚያውቅበት በመንገድ የተለየ ያደርገዋል።
ትውልድ እና እድገቱ በተለምዶ አውቶብስተራ ሰባተኛ ተብሎ የሚጠራው ሰፈር ነው፣፣ ዳግማዊ ቴዎድሮስ፣ የካቲት 23 ፣ ኮልፌ ኮምፕሬሲቭ እንዲሁም ተግባረ ዕድ የተማረባቸው ትምህርት ቤቶች ናቸው።
_
ከ35 ዓመት በላይ እግር ኳስን ከሰፈር አንስቶ እስከ የሊግ ጨዋታ ሜዳዎች እና ክልሎች ተከታትሏል፣፣ ጋዜጠኝነትን በ1989 ላይ በይፋ ጀምሮታል፣፣ ግሎባል፣ ማራቶን፣ካታንጋ፣ካምቦሎጆ እና በ90ዎቹ ለነበሩ ሌሎች በርካታ ጋዜጦችም ፅሁፉን በንባብ አቅርቧል።
_
ከ1996 ጀምሮ ደግሞ በሊግ ጋዜጣ ሲሰራ ከ1997 ከዚያም እስካሁን ድረስም በሀትሪክ ጋዜጣ ላይ በሁለቱም ዕትሞች ላይ በከፍተኛ ብርታት እና ጥንካሬ እየሰራ ይገኛል። በሬዲዮም በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ በፕላኔት ስፖርት እንዲሁም በስሙ ተሰይሞ በነበረው ሌላ ፕሮግራም ላይ በስፖርት አዘጋጅነት ሰርቷል።
ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ውድድሮች ሽፋን ይሰጣል ይከታተላል ፣ ትኩረትም ተሰጥቷቸዋል፣፣ ከ35ዓመት በላይ በሙያው በታታሪነት በመልካም ስነ ምግባር ትኩረቱ ስራው እና ስራው ላይ ብቻ ሲሰራ ቆይቷል።
በተለይ የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን የውስጥ ውድድሮችን በየሜዳዎቹ በመገኘት ክረምት በጋ ሳይል ሲዘግብ ቆዮታል ይህ አንጋፋ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ላበረከተው የላቀ ተሳትፎ በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን የክብር ሽልማት አበርክቶለታል።
ስለእውነት ከሆነ ስለሀገራችን ስፖርት ዕድገት የምናስብ ከሆነ መሸሻ /መሼ/ መሸለም የነበረበት ቀደም ብሎ በኢትዮጰያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ወይም በጋዜጠኞች ስፖርት ማህበር በኩል ነበር፡፡ የአዲስ አበባ ኳስ ፌዴሬሽን ይሄን በማድርጉ ሊመሰገን ይገባል፡፡ የሚገርም የማስታወስ ችሎታ ያለው ተጨዋጮችን እንዳይረሱ ታሪካቸውን የሚነግረን ታዳጊዎችን የሚያበረታታ የሀገር ውስጥ ውድድሮችን ቅድሚያ ሰጥቶ የሚዘገብ አመለ ሸጋ ጋዜጠኛ ነው፡፡ በርታ መሸ……ከሴት እህቶችችንም ኑራ ዕውቅና ቢሰጣት የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡