THE BIG INTERVIEW WITH ADANE GIRMA
“ስለ ፖለቲካ ብዙ እውቀቱ ባይኖረኝም ፖለቲከኛውንም ሆነ
አክቲቪስቱን ከኳሳችን ውስጥ ማውጣት ግን አለብን”“አዳነ እኮ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ብዙ የሰራና ብዙ ዋንጫ
ያገኘ ተጨዋች ነው በቀላሉ አቁም ሲባል እንዴት ያቁም?”
አዳነ ግርማ
/የወልቂጤ ከተማ ምክትል አሰልጣኝ
በዮሴፍ ከፈለኝ
ሀትሪክ፡- የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎችን
አቀባበል እንዴት አገኘኸው?
አዳነ፡- ጎል ማስቆጠር ደስታን ይፈጥራል
ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን ማንነቴን ያገኘሁበት
ቤቴና ክለቤ ነው፡፡ አቀባበሉ የሰጡኝ ፍቅር
አስደስቶኛል፡፡ ማንኛውም ሰው ሲከበር ደስ
ይለዋል የለፋሁለት የጊዮርጊስ ደጋፊዎች
አክብረውኝ ፕሮግራሙን በማዘጋጀታቸው
ከልብ አመሰግናለሁ፡፡ ሁሌም አቅሜ
የፈቀደውን በማድረግ እነርሱን ለማስደሰት
11 አመት ለፍቻለው ያን ተረድተው
የሰጡኝ ፍቅር በመሆኑ ተደስቻለሁ፡፡ ይህን
ደጋፊ ማስጨፈሬ አስደሰተኝ….. ትልቅ
ክብር ሰጥተውኛልና በጣም ላመሰግናቸው
እፈልጋለው ሁሌም በልቤ ውስጥ ይኖራሉ
ሁሌም ሳከብራቸው እኖራለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- የግቡን መታሰቢያነት ለማን
ሰጠህ?
አዳነ፡- ለቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች
የግቧን መታሰቢያነት ሰጥቻለው ምክንያቱም
ጊዮርጊስ ላይ ጎሉ ገብቶ ደጋፊው የጨፈረበት
የመጀመሪያ ጎል ይመስለኛል ደጋፊዎቹ
ራሣቸው ላይ ተቆጥሮባቸው የጨፈሩበትን
ጊዜ አላስታውስም በታሪክም የመጀመሪያ ጊዜ
ይመስኛል…..ምን ያህል እንደሚወዱኝ ምን
ያህል እንደሚያከብሩኝ ያሳዩበት አጋጣሚ
ነውና መታሰቢያነቱን ለእነርሱ ሰጥቻለው
በቀጣይም ምን ያህል እንደማከብራቸው
የማሳየት ፍላጎት አለኝ፡፡
ሀትሪክ፡-ሳላሀዲን ግብ ሲያስቆጥር
አንተ ተቀይረህ ወጥተሃል አብረኸው ብዙ ጊዜ
እንደማሳለፍህ ግብ ሲያስቆጥር ልታቅፈው
አልሞከርክም…?
አዳነ፡- (ሳቅ በሳቅ) የሳላ ግቦች ድንቅና
ምን ያህል ሲኒየር ተጨዋች መሆኑን ያሳየበት
ይመስለኛል፡፡ በተለይ የመጀመሪያ የሹት ግቡ
ያምራል፡፡ የራሱ ሹቶች ተፈጥሯዊ ናቸው
በክለብም ሆነ በብሔራዊ ቡድን አብረን
ተጫውተናልና በቅርብ አውቀዋለው፡፡ ነገር ግን
ሜዳ ውስጥ ሆኜ ብሆን ኖሮ ሳላሀዲን ጎሎቹን
አያገባም ነበር (ሳቅ) ምክንያቱም በቅርብ
ርቀት እየተከተልኩ ለተጨዋቾቹ እነግር
ነበር፡፡ ሁለቱም ጎሎች የገቡት እኔ ከወጣው
በኋላ ነው፡፡ የሳላን እንቅስቃሴ አውቀዋለው
ጌታነህም በደንብ ይያዝ ነበር እርሱ እግር
ስር ኳስ ሲገባ እየተቀያየርን እንይዘው ነበር
እነ ቶማስና መሀመድ የሚባሉ ተከላካዮች
በደንብ እንዲቆጣጠሩ አበረታታ ነበርና ጎሎቹ
አይገቡም ነበር….. ሁለቱ አጥቂዎች ጊዜና
ክፍተት ከሰጠሃቸው በጣም ከባድ አጥቂዎች
ናቸው ሁለቱም ግቦች የገቡት ለሳላህዲን
ክፍተት ስለሰጡት ነው ሳላ የነበረው ፖዚሽን
ልዩ ነበር ከሲኒየርነቱ አንፃር ይጠበቅ ስለነበር
አልገረመኝም….. እንደ ሳላህዲንና ጌታነህ
ከባድ አጥቂ ኢትዮጵያ ውስጥ በዚህ ዘመን
አልተፈጠረም….. የሳላህዲን የሹት ግብ
የተለመደ ነው ኳሷን ወግቶ ያስቆጠራት
ሶስተኛ ግብ በልምዱ የተጠቀመው ነው ጎሎቹ
ማንነቱን የገለፀበት ግቦች ቢሆኑም ባልወጣ
ኖሮ ግን ግቦቹን አያገባም ነበር (ሣቅ)
ሀትሪክ፡-የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች
ሳሪስ አካባቢ ፕሮግራም አዘጋጅተው ሲጠሩህ
አለቀስክ… በጣም ስሜታዊ ሆነህ ነበር… እስቲ
ሁኔታውን አስረዳኝ?

አዳነ፡- አዎ እውነት ነው ከቅዱስ
ጊዮርጊስ እወጣለው ብዬ በፍፁም አልጠበኩም
ጭንቅላቴ ውስጥ ሃሳቡም አልነበረም፡
፡ ለዕረፍት ጀርመን ሄጄ እንደተመለከስኩ
ከቢሮ ተደወለና ነገ 4 ሰዓት ላይ ትፈለጋለህ
ና ተባልኩና ሄድኩ…. ለጊዮርጊስ ስፈርም
የቦርድ ፕሬዚዳንቱ አቶ አብነት ገ/መስቀልና
እነ ኤፍሬምን የመሳሰሉት ብዙ ሰዎች ነበሩ
ነገር ግን ስወጣ አቶ ሰለሞን በቀለ ብቻ ነበርና
ተከፋሁ አዳነ አሰልጣኙ ከ25 ተጨዋቾች
ውጪ አድርጎሃልና ለእስከዛሬው ግልጋሎትህ
እናመሰግናለን የክብር ሽኝት ይኖርሃል ካሁን
ጀምር ቀጣይ ክለብህን መፈለግ ትችላለህ
ሲሉኝ አዘንኩ.. በቃ ከጊዮርጊስ ልወጣ ነው
ማለት ነው ያልኩት በጣም ተሰምቶኝ ነበር፡
፡ አንድ ምሣሌ ልናገር የኢትዮጵያ ቡና
ደጋፊዎች ሜዳ ውስጥ ሲያገኙኝ የሚሰድቡኝ
ከኔ ጋር ምንም ችግር ኖሮባቸው አይደለም
ከማንም በላይ ብሔራዊ ቡድን ስጫወትና
መኪና ስሸለም ይገባዋል ብለው የጨፈሩልኝ
የቡና ደጋፊዎች ናቸው ጥላቻቸው የጊዮርጊስ
ስለሆንኩ ብቻ ነው የኔ ጥሩ መሆን ጊዮርጊስን
ስለሚጠቅም ነው ጊዮርጊስን የሚያበሽቁ
የሚያናድዱ መስሏቸው ነው የሚሰድቡኝ
በክብሬም ይመጡ የነበረው ለዚህ ነው…. ብዙ
የቡና ደጋፊዎች መንገድ ላይ ሲያገኙኝ የቡና
ደጋፊ ነን ግን በጣም እንወድሃለን ይሉኛል
በእልህ ለቡድኑ የምትከፍለው መስዋትነት
ያስደስታል ይላሉ… ምን ያህል ለጊዮርጊስ
መሰጠቴን ስለሚያውቁ ነው የሚሳደቡት..
እናም ይሄን ቡድን ስለቅ እንዴት አይሰማኝ?
አሁንም ወደፊትም ጊዮርጊሳዊ ነኝ ነገር
ግን እወጣለው ብዬ አስቤ ባለማወቄ ልቀቅ
ስባል ተከፋሁ.. ያኔ ታዲያ ደጋፊዎቹ
ከክለቡ ቀድመው አክብረው ሳሪስ አካባቢ
ያሉ ደጋፊዎች ሲጠሩኝ ተደሰትኩ ያኔ
የሀዋሳ ተጨዋች ብሆንም አስፈቅጄ ቦታው
ስገኝ የደጋፊው ድባብ የሰጡኝ ፍቅርና ክብር
ትልቅ ነበር የመወጣቴ እልህ ገና አለቀቀኝም
ነበርና አለቀስኩ…. ጊዮርጊስን እወደዋለው
የመጀመሪያ ልጄ ገብርኤል ይባላል ቅ/
ጊዮርጊስን እንደዚህ ልጄ ነው የምወደው
ብዬ ተናገርኩ፡፡ የሰው ልጅ ገንዘብን ሰርቶ
ለፍቶ ያገኛል ክብርን ግን ዝም ብሎ አያገኝም
ከነርሱ ያገኘሁት ክብር አስደስቶኛል ከሰጡኝ
ክብር በላይ እነሱን አክብሬ ማስደሰት
እፈልጋለው…. ይሄ ደጋፊ ምንም ብሰጠው
አይበዛበትም ለቅሶዬ ፍቅሬን ያሳየሁበት ለቅሶ
ነው፡፡
ሀትሪክ፡- ምክትል አሰልጣኝና ተጨዋች
ሆነህ ወልቄጤ ከተማን እያገለገልክ ነው እንዴት
ይዞሃል አሰልጣኝነቱ?
አዳነ፡- በጣም አሪፍ ነው በሀዋሳ
በጊዮርጊስ እንደገና በሀዋሳ ያሳለፍኩት
የተጨዋችነት ዘመኔ ቀላል አይደለም
በብሔራዊ ቡድን አንቱ የተባሉ አሰልጣኞች
አሰልጥነውኛል፡፡ ተጨዋቾችን መምራት
ከቻልክ ሌላው ከባድ አይደለም እግር ኳስ
እንደ አትሌቲክስ የግለሰብ ስፖርት አይደለም
የቡድን ስራ በመሆኑ በተጨዋችነት ምን
እንሚመስል አይቻለሁና ይህን መስራት
ይከብደኛል ብዬ አላስብም… ከሰው ጋር
ተመሳስዬና ተግባብቼ መኖር እችላለው
አሰልጣኝነቱን በጥሩ ማኔጅመንት ካስኬድከው
አይከብድም ልምምዶቹ ስለተሟርኳቸው
አውቃቸዋለው እየሰራሁ እያሳየሁ ነው…
ስሰራ የከረምኩትን ነገር ማሰራት ቀላል ነው፡፡
ሀትሪክ፡-በውጪም ሆነ በሀገር ውስጥ
አሰልጣኞች ሰልጥነሃል ትልቁ ልዩነት የቱ
ይመስልሃል?
አዳነ፡- አንድ መሰረታዊ ልዩነት አላቸው
የኛ ሀገር አሰልጣኞች ቡድኑን እየጠቀመ
ብቻውን ይዞ እየወጣ ያለ ተጨዋች ካለ
ብዙም ወሳኝነት የሌላቸውን ተጨዋቾች
ክብር ለማግኘት ሲሉ ጎበዙን ይናገሩታል
ይሰድቡታል መጠፋፋት ነው የሚይዙት
ኮከቡን ተጨዋች በመቅጣትና በማሸማቀቅ
ሌሎቹ እንዲማሩ ያደርጋሉ ይሄ ስህተት ነው
ይሄ በህይወቴ የደረሰብኝ ነገር ነው…. የውጪ
አሰልጣኞች ግን አንድ ወይም ሁለት ካገባው
ሶስትና አራት ማግባት እንድችል እንድታወቅ
በራስ መተማመን ቡድኑን እንድጠቅም
ያደርጋሉ አጠገቤ የሚጣመረኝ ተጨዋች
ማን እንዲሆን ትፈልጋለህ የቱ ይመችሃል
በማለት ተጨዋቹ የሚገንበትን መንገድ ነው
የሚከተሉት አሰልጣኝ የሆንኩትም ለዚህ ነው
አሰልጣኝነት ከባድ የሚሆነው ቅንነት ከሌለ
ብቻ ነው ቀናና ሆደ ሰፊ መሆን ከቻልክ ስራው
ይቀላል ከ25-3ዐ ተጨዋቾች ለመምራት
ልብህ እኩል አሳቢ መሆን አለበት… በፊት
ብቻዬን ነበር የማስበው ምናልባት አምበል
ስሆን ነው ሜዳ ውስጥ ሲላሉ 11 ተጨዋቾች
የማስበው አሰልጣኝነት ግን ሁሉንም የቡድኑ
ተጨዋቾች ወደ አንድነት አምጥተህ ያ
አንድ ሃሣብ በአሰልጣኙ ልብ ውስጥ ቦታ
አግኝቶ በአሰልጣኙ ልብ ውስጥ ያለውን
ሃሣብ ተረድተው ውስጣቸው ገብቶ እንዲሰሩ
ማድረግ ነው፡፡ አሁን እየተጫወትኩ ነው
የማሰልጥነው…. አጠገቤ ያሉት የአሰልጣኞች
ስትፍ በፍቅርና በመከባበርና በህብረት ፊት
ለፊት እየተነጋገርን ተግባብተን እየሰራን ነው፡
፡ በስራዬ ደስተኛ ነኝ፡፡ ለወጣቶቹ ብዙ ልምድ
እያካፈልኩ መሆኔም አስደስቶኛል፡፡
ሀትሪክ፡- እድለኛ ነህ ልበል? በሄድክበት
ክለብ ሁሉ ጥሩ የሆነ ተቀባይነት ታገኛለህ…
ከአመራሮቹ ጋር ስለምትግባባ ይሆን?
አዳነ፡- መሆን የፈኩትን ነገር በህይወት
ዘመኔ አጥቼ አላውቅም አንድ ነገር ማድረግ
ስፈልግ ወይም መሆን ለምፍለገው ነገር
100 ፐርሰንት ተሰጥቼ ነው የምሰራው…
ትልቅ ተጫዋች መሆን ፈለኩ ፈልጌ ብቻ
ሣይሆን ለፍቼ ሰርቼም ነው የምፈልገውን
ያገኘሁት.. ብሔራዊ ቡድኑን አገልግያለው
ጊዮርጊስ ይሁን አዋሳ አሁንም ወልቂጤ ስገባ
ተለምኜ ነው ለምን ቢባል ስራዬን አከብራለሁ
ምን ማድረግና መስራት እንዳለብኝ
አውቃለው፣ ስለዚህ የፈለኩትን ነገር አጥቼ
አላውቅም እግዚአብሔርም አሳክቶልኛል፡፡

ሀትሪክ፡- ከሀዋሳ ስትወጣ በሠላም አይደለም የሚል
መረጃ አገኘሁ ምን ተፈጠረ?
አዳነ፡-ተጨዋችነትህን
አቁምና ወደ አሰልጣኝነት ግባ አሉኝ….
አዳነ ግርማ
ነኝኮ… እንደ ትንሽ ተጨዋች ጀምሬ አቁም ስባል ማቆም አልፈለኩም፡፡
አዳነኮ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ብዙ የሰራና ብዙ
ዋንጫ ያገኘ ተጨዋች ነው በቀላሉ አቁም ሲባል
እንዴት ያቁም? የተጨዋችነት
ዘመኔ ሲያበቃ ለሚዲያ ታሪኬን ገልጬ መደረግ ያለበት ነገር
ተደርጎ በክብር ነው መሸኘት የምፈልገው፡፡
ይሄ አመለካከቴ ነው ያላግባባን… ኳስ ተጨዋችነት
ስጀምር ትንሽ ነበርኩ ሰርቼ
ትልቅ ሆኛለው የትኛውምአለም እንደሚደረገው
ከኳስ አለም ስገለል
በስርዓትና በስርዓት
ብቻ መሆን አለበት
ብዬ ስለማስብ
ለወልቂጤ ልፈርም
ችያለው፡፡ እስቲ
አስበው ለብሔራዊ
ቡድን ግልጋሎት
የሰጠ ከታላላቅ ክለቦች
ጋር ዋንጫ የበላ…
ብዙ ስኬታማ ታሪክ
የሰራ ተጨዋቾች
ዝም ብለህ አቁም
ይባላል? አትለውም
ይሄ ተገቢ አይደለም….
ልበ ቀና የሆነ ሰው
እግዚአብሔርም
ይረዳዋል……የፈለኩትን አሳጥቶኝ
አያውቅምና እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፡
፡ በነገራችን ላይ ከሃዋሳ አመራሮች ጋ ሰላም
ነኝ ሃዋሳ ቤቴ ነው ያደኩበት ማንነቴን
ያገኘሁበት ኳስን ሀ ብዬ የጀመርኩበት ክለቤ
ነው በየትኛውም አጋጣሚ የምመለስበት
ቤቴ ነው… አሰልጣኙ አዲሴ ካሳ የምወደው
ኳስን በደንብ ያስተማረኝ አባቴ ነውና
በየትኛውም ጊዜ መመለስ እችላለው የተጋነነ
ችግር የለም ውሌ ግን አልቆ ወጥቻለው፡፡
ሀትሪክ፡- አዳነና የእግር ኳስ ተጨዋችነት
መቼ የሚለያዩ ይመስልሃል?
አዳነ፡- የመጨረሻ የተጨዋችነት ዘመኔ
ላይ እገኛለው ዘንድሮ ወልቂጤን በምክትል
አሰልጣኝነና ተጨዋችነት ካገለገልኩ በኋላ
ውድድሩ ሲጠናቀቅ ጫማዬን እሰቅላለው፡፡
ሀትሪክ፡-ታዲያ ከኳስ ልገለል ወራቶች
ቀሩኝ እያልከን ነዋ?
አዳነ፡- አዎ ከ2013 ጀምሬ ሙሉ
ትኩረቴ አሰልጣኝነቱ ላይ ይሆናል፡፡
ሀትሪክ፡-የወልቂጤ ከተማ ወቅታዊ
አቋም ለፕሪሚየር ሊጉ ዝግጁ ያደርገዋል
ደጋፊዎቹን እንዴትስ አገኘኋቸው?
አዳነ፡- ደጋፊዎቹ ያን ያህል ኪሎ
ሜትር ድረስ መጥተው እየደገፉን ከጎናችን
ሆነው ፍቅራቸውን እያሳዩን በመሆኑ
እናመሰግናለን…. በሲቲ ከፑ 2 ጨዋታ
ተሸንፈናል ይህን እንደ መዘጋጃ እያየን
ነው ከታች ቡድኑን ያሳደጉትን ተጨዋቾች
ብዙም አልቀነሰም እነዚያ ሲታዩ ደግሞ
የችሎታ ማነስ አይደለም የልምድ ማነስ
ነው የታየባቸው ሊጉን አያውቁትም አዲስ
በመሆናቸው ተደናግጠዋል…. በርግጥ እግር
ኳስ የስህተቶች ጥርቅም ቢሆንም የገቡብን
ጎሎች በሙሉ በቀላል ስህተቶች የገቡ ናቸው
ይሄ ውድድር ደግሞ ለሊጉ እንድንዘጋጅ
ለተጨዋቾቹም ሆነ ለአልጣኞቹ ትልቅ
ትምህርት ሰጥቷል በጣም አሪፍ ውድድርነው የተወሰኑ
ተ ጨ ዋ ቾ ች
ያላቸውን አቅም
ያየንበት ነው በዚህ
ውድድር በመካፈለችን
እድለኞችና ደስተኞች ነን፡
፡ አሁን መሸነፍ ማሸነፍ ላይ
ትኩረት እናደርግም በበርካታ
ደጋፊ መሀል መጫወት ምን
ይመስላል የሚለው ተጨዋቾቹ
ያዩበት ይመስለኛል ሌሎች
ክልሎች ጋብዘውን ነበር እዚያ
ግን ያልሄድነው በበርካታ ህዝብ
መሀል የመጫወት አቅማቸውን
የሚያዩበት እዚህ በመሆኑ አዲስ
አበባ ለመገኘት ችለናል ጥሩ ልምድ
አግኝተንበታል በዚህም ደስተኞች
ነን፡፡
ሀትሪክ፡- የፀጥታ ዋስትና
በሌለበት ፕሪሚየር ሊጉ ይጀመር
የሚለው አላስጋህም?
አዳነ፡- አስቸጋሪ ነው….
በመጀመሪያ ሀገራችንን ሠላም
ያደርግልን የተባረከ ሃገር ነው
ያለን… እግዚአብሔር ኢትዮጵያን
አይተዋትም…. የወቅቱ የፖለቲካ
ሁኔታ አስቸጋሪ ነው፡፡ ፖለቲከኞች
ኳሱን ለኛ ተዉልን ፖለቲካ ውስጥ
ብቻ የፈለጋችሁትን መሆን ትችላላችሁ
ሊባሉ ይገባል…ስለ ፖለቲካ ብዙ
እውቀቱ ባይኖረኝም ፖለቲከኛውንም ሆነ
አክቲቪስቱን
ከኳሳችን ውስጥ
ማውጣት ግን
አለብን፡፡ እግር ኳስ
የአንድነት፣ የህብረት፣
የሠላም ህዝብን የማስታረቂያ
ውድድር ነው ኢትዮጵያዊያን
እግር ኳስ ስለምንወድ ከኳሱ
ውስጥ ፖለቲካው መውጣት አለበት
ፌዴሬሽኑም ኳሱም ለስፖርት ወዳዱ
ህዝብ እንዲተዉ ማድረግ አለበት፡፡
የማንም ደጋፊ ሆኜ ሳይሆን የኳሱ መርሁ
መከበር አለበት ባይ ነኝ… ከአንዱ ቦታ
ወደ አንዱ ቦታ መሄድ ከባድ ሆኗል… ክለቡ
ሲሸነፍ ብሔሩ ዘሩ ማንነቱ እንደተሸነፈ
የሚታሰብ ከሆነ አደጋ ነው፡፡ እንግዳ
ሆነህ ሌላ ከተማ ሄደህ ማንም የከተማው
ሰው ይልይሃል እንዴት ነው የምትሆነው
ይሄ ስጋት ነው ፖለቲከኞች የራሣቸውን
ጨዋታ ለራሣቸው ሊያደርጉ ይገባል ኳሱን
ተውልን ማለት እፈልጋው… ለኳስ የሄደ
ደጋፊ ተፈንክቶ ወይም ህይወቱ አልፎ
ማየት ያማል ለማንኛውም ሁሉን ማድረግ
የሚችለው እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ሠላም
ያድርጋት፡፡
ሀትሪክ፡- በሁሉም የተጫወትክባቸው
ክለቦች የለበስከው 19 ቁጥር ነው ልጅህ
ገብርኤል ይባላል፡፡ ይሄንስ እንዴት ሆነ….
ቁጥሩን አለቅም ያለ ተጨዋች አለመኖሩ
እልገረመህም?
አዳነ፡- ልጆቹ እግዚአብሔር ይሰጣቸው
ፈቅደው እየሰጡኝ ነው… ሀዋሳ ተመልሼ
ስሄድ ቁጥሩን የለበሰው ተጨዋች ብዙም
ሜዳ ውስጥ የሚገባ አይደለም ነገር ግን
ማክበር አለብኝ ኦኮቴ ይባላል ሄድኩና ኦኩ
ይህን ማሊያን መልበስ እፈልጋለው ስልው
በደስታ ነው የፈቀደልኝ ችግር የለውም ብሎ
አክብሮ ነው 19 ቁጥሩን የሰጠኝ ማመስገን
እፈልጋለው…. ሀዋሳ ስመለስ ደስታ ዮሃንስ
(አባት) ነበር አምበሉ ዳኒና አዲስም
ሌሎቹ ካፒቴኖች ናቸው… በርግጥም
ካፒቴን የመሆን ሱስ የለብኝም ሀዋሳ
ስብሰባ ስናደርግ …አይደለም ክለብ
አገር የመራ ልጅ ነው ካፒቴንነነቴን
ለአዳነ ስሰጥ በደስታ ነው እርሱ ነው
ካፒቴናችን እጅ አውጥቶ ምርጫ
ብሎ ነገር የለም በማለት አባት
ሲናገር ረካሁ፡፡ ሰው ሲያከብረኝ
ካከበረኝ ልክ በላይ ማክበር
እፈልጋለሁና ስላከበረኝ አባትንም
ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡ አሁን
ትንሽ እግሩ ተጎድቶ ከጨዋታ
ወጥቷል እግዚአብሔር ፈፅሞ
ይማርህ ልለው እፈልጋለው
ስላለከበርከኝ እግዚአብሔር
ያክብርህ ማለትም
እፈልጋለው… ወልቂጤ
አሰልጣኙ አልዬ ነው የሰጠኝ፡
፡ 19 እና እኔ በዚህ አጋጣሚ
አሁን ድረስ አልተለያየንም
(ሣቅ)

ሀትሪክ፡- አዴ ከዋሊያዎቹ
ተሰላፊነት የራቅከው ተቀንሰህ
ወይስ እንቢ ብለህ ነው?
አዳነ፡- መነሻው
አሰልጣኝ ማርያኖ ባሬቶ
ቀንሶኝ ነው… ከዚያ
በኋላ አሰልጣኝ አሸናፊና
አሰልጣኝ ዮሃንስ በተደጋጋሚ
ጠርተውኝ ነበር፡፡ በቃ
አገሬን 10 አመት አገለገልኩ
አይደል ቦታዬን ለወጣቶቹ
መልቀቅ አለብኝ ብዬ ወስኜ
ነው የተሰናበትኩት፡፡
በነገራችን ላይ ስቀነስ ግን
ተበሳጭቻለው በችሎታ
ማነስ ሳይሆን
የአሰልጣኝ ሰውነት
ቢሻውን ቡድን
ላጥፋው ብሎ
በተነሳበት መንገድ
ቅር ተሰኝቼ በመናገሬ
ይመስለኛል… ሰው የራሱ ደካማ ጎን
ቢኖረውም ጠንካራ ጎንም አለው፡፡ ባሬቶ
ቡድኑ ሲሸነፍ መቶ በመቶ የኔ ጥፋት
ነው ይላል ይሄ የሁሉም አሰልጣኝ ባህሪ
መሆን አለበት ብዬ አስባለው እዚህ አገር
ስታሸንፍ ድሉ የእኔ ነው ይላል ቡድኑ
ሲሸነፍ ደግሞ ኃላፊነት መውሰድ
ይፈራል ይሄ ሰው ግን ስንሸነፍ
እናንተ ምንም አላደረጋችሁም ወንዶች
ናችሁ ተሸናፊው እኔ ነኝ ብሎ
ከጎንናችን ይቆማል እንደዚህ አይነቱ
አሰልጣኝ ደስ ይላል ሲጀመር
አሰልጣኝነት ራሱ ኃላፊነት ነው
ኃላፊነት የሚሸሽ አሰልጣኝ ደግሞ
አይመቸኝም በየትኛውም ቦታና
ኃላፊነት ደረጃ ይሁን ኃላፊነት
መሸከም ለምጃለሁና መሸከምም
ደስ ይለኛል… አሰልጣኙ ከሰው
ሰምቶ ይሁን አይሁን ባላውቅም
የሰውነትን ቲም ያፈራረሰው እርሱ
መሆኑ ግን አበሳጨኝ…. በጣምም ቅር
ብሎኝ ነበር በዘመኔ ሁሉ በችሎታ ማነስ
አይደለም ልቀነስ ለመቀነስ ታስቤም
አላውቅም…. ለመጀመሪያ ጊዜ ግን ቀነሰኝ
ከዚያ በኋላም መመለስ አልፈለኩም፡፡
ሀትሪክ፡- የዋሊያዎቹ ስብስብ እንዴት
ታዘብከው…ተደጋጋሚ ሽንፈት አልበዛም?
አዳነ፡- ሁለት ሃሳብ አለኝ… ቡድን
ሲሰራ በአንድ ጀንበር አይሆንም… በአንዴ
ቡድን ወጥ አቅም ሊያሳይ አይችልም ጊዜ
ያስፈልጋል ይሄ እውነት ነው…. ሌላው ግራ
የገባኝ ነገር እንዴት እንደታሰበ አላውኩም….
በመላው አለም ቡድን በአንዴ እንደማይገነባ
ሁሉ በአንዴም አይፈርስም የአሰልጣኝ
አብርሃም ቡድን መቼ እንደሚገነባ ነው
ማወቅ ያልቻልኩት፡፡ በየምርጫው የተለያየ
ሰው ነው የሚመረጠው….የተለያዩ ቤስት
11 እያየን ነው፡፡ እኛ በነበርንበት ጊዜ ቤስቱ
ወጥ ነው፡፡ ጉዳት ወይም የአቋም መውረድ
ሲመጣ አንድ ወይም ሁለት ሰው ነው
የሚቀየረው… አሁን ግን እንዲህ አይደለም
የቤስት 11 ስትራክቸሩ ሳይለቅ አንዳንድ
ቦታ ላይ ሲሰካካ ነው የማውቀው አሁን
ላይ ግን ሁሌ የማየው ካልተጎዳ በስተቀር
አስቻለሁ ታመነን ብቻ ነው…. ሌሎቹ
የተቀየሩ እንደገና አዲስ ጥሪ እየተደረገ እንጂ
እየተሳካካ አይደለም… በየምርጫው የተለያዩ
ተጫቾች ከተመረጡ ከባድ ይመስለኛል…..
አሰልጣኞቹ ይጠፋቸዋል እያልኩ አይደለም
ነገር ግን ለኔ ግራ ገብቶኛል……አሰልጣኝ
አብርሃምና ቡድኑን ለመተቸት ገና ነው፡
፡ አዲስ ቡድን ግንባታ ላይ ስለሆነ መደገፍ
አለበት ባይ ነኝ በርግጥ ቡድኑ መገንቢያው
መቼ ነው የሚለው አሳስቦኛል፡፡
ሀትሪክ፡-ክለቦችስ ጋር ያለው ደካማ
አቋም ብሔራዊ ቡድኑን አልጎዳውም?
አዳነ፡- የሁሉም ተጨዋቾችም ይሁን
ክለቦች ትልቁ ግብኮ ብሔራዊ ቡድኑ
ነው….. ክለቦች ሲጠነክሩ ብሔራዊ ቡድኑም
ይጠነክራል… ቡድኑ ጠንክሮ እንዲገኝ ክለቦች
ራሳቸውን ማጠናከር አለባቸው… አሁን ላይ
ያለው ውጤት ቢያስቸግርም በቀጣይ በርትቶ
ከተሰራ ለውጥ ይመጣል ብዬ አስባለው፡፡

ሀትሪክ፡-ማክሰኞ ከኮትዲቯር ጋር ጨዋታ
አላቸው….የምትላቸው ነገር አለ?
አዳነ፡- በመጀመሪያ ለብሔራዊ ቡድኑ
መልካም ውጤት እመኛለሁ… አገር
ስታሸንፍ ሁሉም ህዝብ ይነቃል ደስ ይለዋል፡
፡ መላው ኢትዮጵያዊያን አንድ የሚያደርግ
ብሔራዊ ቡድን ያስፈልገናል አገራችን
ሠላም የምትሆንበት የሀገራችንን አንድነት
የምናስጠብቅበት ውጤት እንዲገጥመን
እመኛለሁ፡፡ ኮትዲቯር በመላው አለም
የሚታወቁ ኮከቦች አሏት ጠንካራ መሆኗም
ይታወቃል… በፊት እኔ መጫወት የምፈልገው
ከጠንካራ ቡድኖች ጋር ነው የአገራችንን
ብቃት የምንለካበት ጨዋታ ከጠንካሮች ጋር
ስናደርግ ነው ለተጨዋቾቹ የማስተላለፈው
መልዕክት በአንድነት መነሳሳት አለባቸው
ከነዊልፍሬድ ዛሃና ኒኮላስ ፔፔ ጋር
እንደመጋጠማቸው በጠንካራ ወኔና ህብረት
ሊጋፈጡ ይገባል እግር ኳስ የግለሰብ ሳይሆን
የህብረት ስፖርት ነው… በዚህ ህብረት ላይ
በደንብ ሊያስቡበት ይገባል ውጤቱ የሚፈለግ
ነው.. የተከፋፈልንበትና አንድነታችን ገጭ
ገጭ ያለበት ጊዜ እንደመሆኑ ኮትዲቯርን
በመርታት ኢትዮጲያዊያንን ወደ አንድነት
ያመጣሉ ብዬ ተስፋ አደርጋው…ለዚህም
እግዚብሔር ይርዳን፡፡
ሀትሪክ፡- ጨረስኩ.. የምትለው
የመጨረሻ ቃል አለ?
አዳነ፡- በመጀመሪያ ይህን ያደረገ
እግዚአብሄር ይመስገን… በረጅም የጨዋታ
ዘመኔ ትልቅ ጉዳት ተጎድቼ አላውቅም በሙሉ
ጤንነት እንድጫወት አድርጎኛልና አምላኬን
ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡ ቤተሰቦቼን፣
አሰልጣኞቼን፣ የተጫወትኩባቸው ክለቦች
ተጨዋቾችና ደጋፊዎችን አመሰግናለሁ፡፡
በተለይ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ላሳዩኝ
ፍቅር ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለው… አገሬ
ኢትዮጵያ አንድነቷ ተጠብቆ ሠላሟ ፀንቶ
ህዝቧ ተባብሮ የሚኖርበት ሀገር እንድትሆን
እመኛለው፡፡
አስተያየት ይስጡ