መነሻ ገጽ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ​ጅማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ የ2009 ዓ.ም የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ አጠቃላይ  ውድድር ሻምፒዮን ሆነ።
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

​ጅማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ የ2009 ዓ.ም የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ አጠቃላይ  ውድድር ሻምፒዮን ሆነ።

አጋራ
አጋራ

ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ በሁለት ምድብ ተከፍሎ 32 ክለቦች ሲሳተፉበት የቆየው የከፍተኛ ሊግ ውድድር ከአንድ ሳምንት በፊት መጠናቀቁ ይታወሳል።

ዛሬ 10 ሰዓት  ላይ በሞቃታማዋ የምስራቅ ክልል በድሬዳዋ ስታዲየም የሁለቱ ምድቦች አሸናፊ አገናኝቷል፡፡

አቅሌስያስ ግርማ በ20ኛው ደቂቃ የአሸናፊነቷን ግብ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል። 

ሁለቱ ክለቦች ከየምድባቸው አንደኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቃቸው በ2010 ዓመተ ምህረት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳትፎን ማረጋገጣቸው ይታወሳል።

ሁለቱን ክለቦች ተከትሎ በ2010 ዓመተ ምህረት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚሳተፈው ሶስተኛ ቡድን መቀሌ ከተማ መሆኑ ትናንት ታውቋል። 

የምድብ ሀ አሸናፊ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ከምድብ ለ አሸናፊ ጅማ ከተማ ጋር ያደረጉት ጨዋታ በጅማ ከተማ 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

በዚህም መሰረት በሚቀጥለው ዓመት ከትግራይ ክልል ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲና መቀሌ ከተማ በፕሪሚየር ሊጉ ይሳተፋሉ።

ጅማ ከተማ ደግሞ የጅማ አባ ቡናን መውረድ ተከትሎ ከተማዋንና አካባቢውን በብቸኝነት ይወክላል።

በ2010 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአራቱም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች የሚገኙ ክለቦች ተሳትፎ ያደርጋሉ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

አሰልጣኝ ጳውሎስ (ማንጎ) ከአምስት ጨዋታዎች በኋላ ተሰናበቱ

አዲስ የተቀጠሩት እና ዛሬ ቡድኑን የመሩት አሰልጣኝ መሳይ በየነ ቡድኑን በአንድ ጨዋታ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ለሌብነት ምቹ ወደ መሆን የቀረበው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ?

ለወትሮ ሀሜት የማያጣው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ትኩረት ሊሰጠው ወደ ሚገባው ምዕራፍ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ሦስት ስመ ጥር አሰልጣኞች ሦስት ክለቦች ለማትረፍ በሀላፊነት ተረክበዋል

ላለመውረድ እየተጫወቱ የሚገኙ ሦስት የከፍተኛ ሊግ ክለቦች በሦስት የሚታወቁ አሰልጣኞች ይመራሉ። በኢትዮጵያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግጋሞ ጨንቻ

የጋሞ ጨንቻው ወጣቱ አሰልጣኝ ማነው ?

ራሱ የመሠረተውን ክለብ ወደ ፕሪምየር ሊጉ እያንደረደው የሚገኘው አሰልጣኝ። ከአመት አመት አዳዲስ...