ጅማ አባጅፋሮች ወደ ሀዋሳ አምርተዋል

ባለፉት ቀናት ከደሞዝ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ቅሬታ ልምምድ ያልሰሩት የጅማ አባጅፋር ተጫዋቾች ከሀድያ ሆሳዕና ጋር ላለባቸው ጨዋታ ወደ ሀዋሳ ለማምራት ተዘጋጅተዋል።

ክለቡ ደሞዝ አልከፈለንም በሚል ቅሬታ ከሳምንቱ መጀመርያ ወዲህ ቡድኑ መደበኛ ልምምድ ሳይሰራ የቆየ ሲሆን ይህም የ15ኛው ሳምንት ጨዋታን ስለማድረጉ አጠራጥሮ ቆይቷል። ዛሬ ጡዋት የከተማው አስተዳደር ባደረጉት ጥረት ለተጫዋቾቹ ለጊዜውም ቢሆን የሁለት ወር
ደሞዝ ክፍያ ፈፅሟል።

ቡድኑ በአሁኑ ሰዓት ወደ አዲስ አበባ ጉዞ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን አዲስ አበባ አረፈው በጠዋቱ በረራ ወደ ሀዋሳ እንደሚያቀኑ ታውቋል። ጅማ አባጅፋር በ15ኛው ሳምንት ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ነገ በ9፡00 ሀዋሳ ላይ እንደሚጫወት ይታወቃል።

Hatricksport website writer

ዳዊት ታደሰ

Hatricksport website writer