መነሻ ገጽ ሪፖርት ሪፖርት | ጅማ አባጅፋር በኦኪኪ አፎላቢ ብቸኛ ግብ ደደቢትን አሸነፈ
ሪፖርትዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግደደቢትጅማ አባጅፋር

ሪፖርት | ጅማ አባጅፋር በኦኪኪ አፎላቢ ብቸኛ ግብ ደደቢትን አሸነፈ

አጋራ
አጋራ

በ21ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ትግራይ ስታድየም ላይ ያገናኘው የደደቢትና ጅማ አባጅፋር ጨዋታ በእንግዳው ቡድን ጅማ አሸናፊነት ተጠናቋል።ደደቢት ባሳለፍነው ሳምንት በድሬዳዋ ከተሸነፈው ቡድን እንዳለ ከበደን በመድሃኔ ብርሃኔ፣ዳዊት ወርቁን በዳግማዊ አባይ፣ረሺድ ማታውኪን በሙሴ ዮሐንስ፣ኤፍሬም ጌታቸውን በእሸናፊ እንዳለ፣ሙሉጌታ አምዶም በአቤል እንዳለ ቀይረው ገብተዋል።ጅማዎች በበኩላቸው ስሑል ሽረን ካሸነፈው ስብስብ ኤልያስ እታሮን በዓወት ገብረሚካኤል፣ኸድር ኸይረዲንን በመላኩ ወልዴ፣መስኡድ መሐመድን በእክሊሉ ዋለልኝ፣እስቻለው ግርማን በዋለልኝ ገብሬ በእጠቃላይ 4 ቅያሬዎችን እድርገዋል።

የደደቢት የኳስ ቁጥጥር ብልጫ በታየበት የመጀመርያ አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች በአተገባበራቸው እሚለያዩ 4-4-2 እሰላለፎችን ተጠቅመዋል።ኳስን ከኃላ በሚገባ መስርተው በመውጣት ጅማ ሜዳ ላይ በተደጋጋሚ የደረሱት ደደቢቶች ከርቀት በየአብስራ ተስፋዬ፣እለም አንተካሳ እማካኝነት ከሚደረጉ ሙከራዎች ውጪ ንጹህ የግብ እድሎችን መፍጠር ተስኗቸው ተስተውሏል ።ለግብ የቀረበ የደደቢት ሙከራ 31ኛው ደቂቃ ከመሃል ሜዳ በረጅሙ የተሻገረውን ኳስ በፍፁም ቅጣት ሳጥን በግራ በኩል የነበረው መድሃኔ ብርሀነ ፍጥነቱን በመጠቀም በግራ እግሩ የመታው ኳስ ለትንሽ የግቡን የጎን ብረት ታኮ ወጥቷል።ከመስመር እንዲሁም ከመሃል ሜዳ በሚላኩ ኳሶች ማጥቃት ምርጫቸውን ያረጉት ጅማዎች በዲድየ ሌብሪ እና ማማዱ ሲዲቤ እማካኝነት ለግብ የቀረቡ ሙከራዎችን ማድረግ ችለዋል።ጨዋታው በተጀመረ በ35ኛው ደቂቃ ከመሃል ሜዳ በረጅሙ የተላከውን ኳስ ኦኪኪ ኦፎላቢ ተቆጣጥሮ እንቶንዮ እቡዋላን በመቀነስ በጥሩ እጨራረስ ጅማን ቀዳሚ ማድረግ ችልዋል።ከግቡ መቆጠር በኃላ ደደቢቶች እቻ ለመሆን ከመስመር በሚሻገሩ ኳሶች ግብ ለማግኘት ያደረጉት ሙከራ ሳይሳካላቸው ቀርቷል።

ዳግም የደደቢቶች ሙሉ ብልጫ በታየበት ሁለተኛው አጋማሽ ምንም ግብ ሳይታይበት ተጠናቋል።ጅማዎች መጀመርያ አጋማሽ ላይ ያገኙትን ግብ ማስጠበቅ ምርጫቸውን አድርገው ታይተዋል በተለይ በአዳማ ሲሶኮና መላኩ ወልዴ እሚመራው የጅማ ተከላካይ ክፍል ከሁለቱም መስመር እሚላኩ ኳሶችን በማራቅ ጥሩ ሲከላከል ታይቷል።ደደቢቶች የመሃል ሜዳ ተጨዋቾችን ቀይሮ በማስገባት እድሎችን ለመፍጠር ያደረጉት ሙከራ ፍሬ ሳያፈራ ጨዋታው ሊጠናቀቅ ችሏል።

ውጤቱን ተከትሎ ሁለት ተከታታይ ድሎችን ያስመዘገበው ጅማ እባጅፋር ነጥቡን 34 በማድረስ አራተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ደደቢት የሊጉ ግርጌን ይዞ ቀጥሏል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሽንፈት ሲገጥመው በድንጉዛ ደርቢ የጦና ንቦቹ እና ኤሌክትሪክ ድል ቀንቷቸዋል

በሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ተከታታይ ሽንፈትን በሸገር ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፊፋ

ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የዝውውር ዕገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ጥሎበት የነበረው የተጫዋቾች...