መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ ጅማ አባቡና እግር ኳስ ክለብ በቴሌቶን 1ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር አገኘ
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ጅማ አባቡና እግር ኳስ ክለብ በቴሌቶን 1ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር አገኘ

አጋራ
አጋራ

የጅማ አባቡና የእግር ኳስ ክለብን ለማጠናከር ትናንት በተካሄደ ቴሌቶን 1ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተገኘ ።

 የክለቡ ፕሬዝዳንት አቶ አብዱልከሪም አባገሮ  እንደገለፁት ክለቡን ህዝባዊ መሰረት ለማስያስያዝ በተካሄደው ቴሌቶን የጅማ ዞንና ከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ አስተዋፅኦ ነበራቸው ።

ከቴሌቶኑ የተገኘው ገንዘብ የክለቡን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ገልፀዋል ።

 የክለቡን የሴቶች ቡድን የማቋቋም ስራም እንደሚሰራ አመላክተዋል።

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በመወዳደር ላይ የሚገኘው ጅማ አባቡና በወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኝ ሲሆን  በቀጣይ በሜዳው ከሃዋሳ ከነማና ከሜዳው ውጭ ደግሞ ከድሬደዋ ከነማ ጋር በመጫወት ዓመታዊ የውድድር መርሃ ግብሩን ያጠናቅቃል  ።

በቴሌቶኑ የጅማ ዞን ፣ ወረዳና ከተማ አስተዳደሮችና ባለሃብቶች ተሳትፈዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...