በአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ዙር ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ የአህጉሪቱን ትልቅ ክለብ ኤስፔራንስን አስተነናግዶ ያለግብ አቻ ወጧል፡፡
ጨዋታው በጊዮርጊስ አማካኝነት ሲጀመር ሰልሀዲን ሰኢድ በፈጥነት አልፎ ይዞት የሄደውን ኳስ ለአዳነ ቢያቀብለውም ሳይጠቀምበት ቀርቷል ፡፡
በ11ኛ ደቂቃ ላይ የፈረሰኞቹ ግብ ጠባቂ ሮበርቶ ኦዶንካራ በጉዳት ምክኒየት ሜዳ ወድቆ የህክምና እርዳት ሲደረግለት ቢቆይም ጉዳቱ ወደ ሜዳ መልሶ ሊያስገባው ባለመቻሉ ከሜዳ በስተሬቸር ለመወጣት ተገዷል፡፡በዚህም ፈረሰኞቹ የመጀመሪያ የተጫዋቾች ቀያሪ ሲያደርጉ ዘሪሁን ታደለን ወደሜዳ አስገብተዋል ፡፡ጨዋታው በቀጠለ በ 19ኛ ደቂቃ ላይ ሰልሀዲን ሰይድ በመስመር ይዞት የወጣውን ኳስ መልሶ ለ ምንተስኖት አቀብሎት ምንተስኖት አክርሮ ወደ ጎል የመታውን ኳስ በረኛው ለጥቂት አድኖታል
በጨዋታው የዳኞች መለያ ከኢስፔራስ ክለብ መለያ ጋር ተመሳሳይ በመሆኑ ሰልሀዲን ከዳኛው ጋር ሲነጋግር ለመታዘብ ተችሏል፡፡
- ማሰታውቂያ -
በ34ኛው ደቂቃ ላይ በናትናኤል ዘለቀ ላይ በተሰራ ጥፋት በግምት 34 ሜ ርቀት ቅጣት ምት ለፈረሰኞቹ ሲሰጥ አበባው ቡጧቆ መቶ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡ የመጀመሪያ አጋማሽ መጠናቀቅ ላ አብዱል ከሪም በመስመር ለአዳነ ያሻገረለት ኳስ የኤስፔራንሱ 2ቁጥር አሊ ማቻኒ ደረቦ በማውጣቱ ፡ የመጀመሪያ የመአዝን ምት ፈረሰኞቹ አጊንተው ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል፡፡ በዚህም የመጀመርያው አጋማሽ ተጠናቋል በሚል አራተኛው ዳኛ ተጨማሪ ደቂቃ 4 አሳይተዋል ፡፡ በ47ኛ ደቂቃ የኤስፔራንሱ 2 ቁጥር ጊህላኒ ቼላሊ ሰአት አባክነሀል በሚል የመጀመርያ ቢጫ ካርድ ተመልክቷል፡፡ ጨዋታው ሊጠናቀቅ በ48 ኛ ደቂቃ ጊህላኒ የመታውን ቅጣት ምት ዘሪሁን ታደለ በጥሩ ሁኔታ አድኖበት የመጀመሪያው አጋማሽ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡
በሁለተኛው አጋማሽ መጀመሪያ የፈረሰኞቹ አጥቂ ባቀረበው አቤቱታ ዳኞች መለያቸውን ቀይረው ገብተዋል፡፡ ጨዋታው በኢስፔራንሶች አማካኝነት ሲጀመር ፈረሰኞቹ ቀጣት ምት ሲያገኙ አበባው ቡጣቆ መቶት ማንም ሳይጠቀምበት ወደ ውጭ ልኳታል፡፡ ፈረሰኞቹ በሁለተኛው አጋማሽ ጫና ፈጥረው መጫወት ችለዋል በ50ኛው ደቂቃ ሰልሀዲን ሰይድ ወደ ጎል ይዞት የገባውን ኳስ ወደ ኀላ መልሶ ለ አዳነ ግርማ የሰጠው ኳስ በጎሉ አናት ላይ ልኳታል፡፡ ጨዋታው በቀጠለ በ57 ደቂቃ ፕሪንስ በመስመር ያሻገረውን ኳስ ሳልሀዲን ተኝቶ በግንባሩ የመታውን ለጥቂት ወደ ውጭ የወጣው ኳስ እሚያስቆጭ ነበር፡፡
በጨረታው 65 ደቂቃ ላይ የኤስፔራንሱ ጊህላኒ ቼላሊ ፕሪንስ ላይ በሰራው ጥፋት በሁለት ቢጫ ከሜዳ ሊሰናበት ችሏል፡፡ በቀሪዎቹ 35ደቂቃዎች ኤስፔራንሶች በ10 ተጨዋቾች ለመጨረስ ሲገደዱ ፈረሰኞቹ ያገኙትን የቁጥር ብልጫ አለመጠቀማቸው እሚያስቆጭ አጋጣሚ ነበር፡፡
በ73ኛ ደቂቃ ፕሪንስ አክርሮ የመታውን ኳስ በረኛ ቢያወጣበትም ሰልሀዲን ኳሱን ተቆጣጥሮ ወደ ጎል የላከውን በረኛ ሲያድንበት በድጋሜ እድሉን አግኝቶ የሞከረውን ኳስ ተከላካይ የኤስፔራንሱ ተከላካይ አውጥቶበታል፡፡
የሁለተኛው አጋማሽ ሊጠናቀቅ 10 ያህል ደቂቃዎች እየቀሩ ሁለተኛ ቅያሪ ያደረጉት ፈረሰኞቹ ፕሪንስን አቡበከር ሳኒ ቀይረዋል፡፡ ጨዋታው በቀጠለ መሀል ሜዳ ላይ አስቻለው ፈቅረዲን ላይ በሰራው ጥፋት ቢጫ ካርድ ተመልክቷል፡፡
ሶስተኛ ቅያሪ ያደረጉት ጊዮርጊሶች ናትናኤልን በተስፋዬ አለባቸው ቀይረዋል፡፡ በጨዋታው መጠናቀቂያ ተቀይሮ የገባው አብድልከሪም ከሩቅ አክርሮ የመታውን ኳስ የኤስፔራንሱ ግብ ጠባቂ ከጎልነት አድኗታል፡፡ ተጨማሪ 3ደቂቃዎች ተጨመረው ጨወታው በያለግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡
ስለጨዋታው ቁጥሮች እንዲህ ይላሉ
የአሰልጣኞች አስተያየት
ቅዱስ ጊዮርጊስ
ምክትል አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ
በውጤቱ ደስተኛ ባልሆንም ተጫዋቾቼ ያላቸውን አቅም አውጥተው በመጫወታቸው በውጤቱ አልተከፋሁም
በመጀመርያው አጋማሽ ተጭነን መጫወት አልቻልንም ይሁን እንጂ ሁለተኛው አጋማሽ ማሸነፍ የምንችልበት አጋጣሚ ነበር አልተጠቀምንበትም ፡፡ዛሬ ደጋፊዎቻችን ከኛ ጋር ዘጠና ደቂቃ ባሳዩት ድጋፍ በውጤት ባናረካቸውም በአደጋገፋቸው ፍፁም ደስተኛ ነኝ፡፡
ኤስፔራንስ ደ ቱኒዝ
የኢስፔራንስ አሰልጣኝ በእንግሊዝኛ ተጠይቆ በፈረንሳይኛ ምላሽ ሰጥቷል፡፡
በመጨረሻም አሰልጣኙ ጋዜጣዊ መግለጫ ጨርሶ ሲነሳ ለጋዜጠኞች” ለምን እናንተ በፈረሳይኛ አትጠይቁም ” ብሎ በመናገሩ ፣ከአንዱ ጋዜጠኛ ” እኛ በቀኝ ግዛት አልተገዛንም” የሚል ምላሽ ተሰጥቶታል፡፡