ድሬዳዋ ከተማ ሶስተኛ ተጫዋች አስፈረመ !

ለሚቀጥለው የውድድር ዘመን የነባር ተጫዋቾችን ውል በማደስ እና አዳዲስ ተጫዋቾችም እያስፈረመ የሚገኙት ቡርትካናማዎቹ ሶስተኛ ተጫዋች ማስፈረም ችለዋል ።

ድሬድዋ ከተማ ግብ ጠባቂውን ሐምዲ ቶፊቅን ከጌዲዮ ዲላ የግላቸው ማድረጋቸው ተገልጿል ።

በአንድ አመት ኮንትራት ቡርትካናማዎቹን የተቀላቀለው ሐምዲ ቶፊቅ ከዚህ በፊትም በ 2010 ግማሽ የውድድር ዘመን በድሬድዋ ከተማ ያሳለፈ ሲሆን በዉሰት ግማሹን ዓመት ለናሽናል ሲሜንት ከተጫወተ በኋላ 2011 ከወልቂጤ ጋር ጥሩ ጊዜያትን በማሳለፍ በ 2012 የውድድር ዓመት እስከ ተቋረጠበት ድረስ በጌዲዮ ዲላ በመጫወት አሳልፏል፡፡

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor