ሊጠናቀቅ የሰዓታት ዕድሜ በቀረው የኢትዮጵያ የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ላይ በንቃት እየተሳተፋ ሚገኙት ደደቢቶች የዮውሃንስ ፀጋይ ና አያሱ ለገሰ ዝውውርን አጠናቀዋል።
ባሳለፍናው ውድድር ዓመት በከፍተኛ ሊጉ አክሱም ከተማ ጋር ቆይታ ያደረገው የቀድሞ የደደቢት፣ወልቂጤ ከተማ፣መቐለ 70 እንደርታ ተጨዋች ዮውሃንስ ፀጋይ ሰመያዊዎቹን ሊቀላቀል ችልዋል።የትራንስ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ቡድን ውጤት የሆነው ዮውሀንስ ዋና አጥቂ እንዲሁም የመስመር አጥቂ ቦታዎችን መጫወት ይችላል።
ሁለተኛው ፈራሚ ከአዲስ አበባ ከተማ ከ20 ዓመት በታች ቡድን የተገኘው እያሱ ለገሰ ነው።የተከላካይ መስመር ተጨዋቹ እያሱ ለገሰ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከ20 ዓመት በታች የተጫወተ ሲሆን ልምድ ያላቸው ተጨዋቾችን በያዘው የደደቢት የተከላካይ ክፍል የቀዋሚ ተሰላፊነት ዕድል ለማግኘት ከባድ ፋክክር ይጠብቀዋል
አስተያየት ይስጡ