የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ | የሀድያ ሆሳዕና የመጀመሪያው ዙር ጉዞ ሲዳሰስ

 

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ትላንት ተጠናቋል :: እኛም የሀድያ ሆሳዕና ጉዞ ምን ይመስል ነበር የሚለውን ተመልክተንላችኋል።

 

በሊጉ ዝቅተኛ ነጥብ በመሰብሰብ 13 ነጥብ ይዘው በሊጉ ግርጌ የሚገኙት ነብሮቹ በቀዳሚነት በመጡበት አመት የመውረድ ስጋት ከተጋረጠበት ቡድን ነው። ከከፊተኛው ሊጉ ወደ ፕሪምየር ሊግ ባሳደጋቸው የቀድሞ አሰልጣኛቸው ግርማ ታደሰ እየተመሩ አስከፊ የሊግ ጅማሮ አድርጉው በሁለት ጨዋታዎች መጠነኛ መነቃቃት ቢያሳዩም። ወደነበሩበት አስከፊ ጉዞ መመለስ ችለዋል። ቡድኑ ያገኘውን አጋጣሚ ወደ ግብነት የመቀየር ደካማነት በሜዳቸውም ከሜዳቸው ውጭ በሚጥሉት ነጥብ ተዳምሮ አሁንለ ላሉበት ደረጃ መገኘት አስተዋፅኦ አድርጓል።

 

በሊጉ ለመቆየት ከፍተኛ ትግል የሚጠበቅባቸው ሀድያዎች በዚህ ዙር ኳስን መሰረት ያደረገ አጨዋወት በብዛት ሲከተሉ ታይተዋል። ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ፀጋየ ኪዳነ ማርያምን በዋና አሰልጣኝነት ከቀጠሩ በኋላ ግን አፍወርቅ ኃይሉን ማእከል ያደረጉ ኳሶች ለሁለቱም የፊት መስመር አጥቂዎች ፒስማርኮች በማድረስ የግብ እድል በመፍጠር እና የተጋጣሚን አጨዋወት አይቶ ለጨዋታው ያዋጣኛል የሚሉትን አጨዋወት መከተል ችለዋል።

 

ከአሰልጣኝ ለውጥ በኋላ ሶስት ጨዋታዎችን በአሰልጣኝ ፀጋየ ኪዳነማርያም እየተመሩ በ13 ነጥብ የሊጉ ግርጌ ላይ የሚገኙት ነብሮቹ በመጀመሪያ ዙር ካደረጓቸው 15 ጨዋታዎች በ3 ጨዋታ ሲያሸንፉ በ 8 ተሸንፈው በቀሪው 4 ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል አቻ ተለያይተዋል። በቅጣት ምክንያት ሀዋሳ ላይ ያደረጉትን ጨዋታ ጨምሮ በሜዳቸው ካደረጓቸው 7 ጨዋታዎች 2 ብቻ ሲያሸንፉ በ2 ተሸንፈው 3 ነጥብ ተጋርተዋል። በሜዳቸው የሚያደርጓቸውን ጨዋታዎች በድል ለመወጣት እንደሚቸገሩ ለመረዳት አያስቸግርም። በሜዳቸው ባደረጓቸው ጨዋታዎች ላይ በተጋጣሚ ቡድን ላይ 8 ግቦችን ብቻ ሲያሳርፍ 8 ግቦች ተቆጥረውበታል። ይህም በሜዳው በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች አንድ አግብቶ አንድ የሚገባበት ሀድያ ሆሳዕና የሚል ድምዳሜ ላይ እንድንደርስ ያደርገናል።

 

ነብሮቹ ከሜዳቸው ውጭ ያደረጓቸውን 8 ጨዋታዎች 1 ሲያሸንፍ በ 6 ተሸንፈው በ1 ብቻ ነጥብ ተጋርተዋል። ሀድያዎች ከሜዳቸው ውጭ ነጥቦች ይዞ መውጣት ቢችልም ከነበራቸው ጉዞ አንፃር ነጥብ ይዞ ለመመለስ እጅጉኑ ደካማ ነው ማለት ያስችላል። ከሜዳቸው ውጭ በነበራቸው ጨዋታ 3 ግቦችን ሲያስቆጥሩ 15 ተቆጥሮባቸዋል። ስራ ፈት የፊት መስመር እና በቀላሉሉ ግብ የሚያስተናግድ ደካማ የመከላከል አቅም እንዳላቸው የሚያሳይ ነው። በአጠቃላይ ነብሮቹ በመጀመሪያው ዙር 11 ግቦችን ሲያስቆጥሩ 23 ግቦች ተቆጥረውበታል። ይህም ማለት በየጨዋታው 0.7 ሲያገባ 1.6 በአንፃሩ የሚገባበት ቡድን ያደርገዋል። በኢትዮጵያ ቡና 5-0 የተሸነፉበት ጨዋታ በመጀመሪያው ዙር በርካታ ግቦችን ያስተናገዱበት ጨዋታ ነበር። በ6 ጨዋታዎች ግብ ሳያስቆጥሩ ሲወጡ በ2 ጨዋታዎች ሳይቆጠርባቸው ወጥተዋል። በተከታታይ ስድስት ጨዋታዎች ድል ያላስመዘገቡበት የመጀመሪያው ጉዝ አስከፊው የሊጉ ጉዟቸው ነበር። ፒስማርክ አፒያ ሶስት ግብ በማስቆጠር የመጀመሪያው ዙር የቡድኑ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው። በአጠቃላይ የሀድያ ሆሳዕናዎች የመጀመሪያው ዙር ነጥብ አምና ከወረዱት ቡድኖች በመጀመሪያው ዙር ይዘው ካጠናቀቁት ጋር ሲነፃፀር ጥሩ ይመስላል። ነገር ግን የዘንድሮው የክለቦች ነጥብ መቀራረብ አስጊ አድርጎባቸዋል። ደቡብ ፖሊስ 11፣መከላከያ 17 እና ደደቢት 4 አምና በመጀሪያው ዙር ወራጅ ቀጠና ይዘው ያጠናቀቁበት ነጥብ ሲሆን። ሀድያዎች አምና ወራጅ ከነበሩት ቡድኖች በተሻለ መልኩ ጥሩ ነጥብ አለው ማለት ይቻላል።

 

የነብሮቹ የመጀመሪያው ዙር ጥንካሬ እና ድክመት

ወደ ተጋጣሚ ግብ ክልል በመድረስ ረገድ ጠንካራ ጎኑ ሲሆን። ግብ የማስቆጠር፣ደካማ የመከላከል አቅም እና ከፍተኛ ግቦችን ማስተናገድ ደግሞ በመጀመሪያው ዙር በስፋት የተስተዋለባቸው ደካማ ጎን ነበር።

 

በሁለኛው ዙር የሚጠበቅባቸው

ሆሳዕናዎች በሉጉ ለመቆየት ከፍተኛ ግብ የሚያስተናግደው ኋላ መሰመራቸው እና በቅርብ ጨዋታዎች ላይ ግብ የማስቆጠር ብሎም የተገኙትን አጋጣሚዎች ወደ ግብ ያለመቀየር ችግራቸው በሁለተኛው ዙር የማይስተካከል ከሆነ በሉጉ ለመቆየት በጣም የሚቸገር ይሆናል።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor