በዛሬው እለት የ2010 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የእጣ አወጣጥ እና ግምገማ በጁፒተር ሆቴል ተካሂዷል፡፡
የጅማ አባቡና እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተወካዮች ባለተገኙበት የእጣ ማውጣት ስነስረዓቱ ተደርጓል፡፡
በ2009 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ከዳኞች መደባ በብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ ሪፖርት መሠረት በውድድር ዓመቱ አንድ ዳኛ ያጫወቱት በዋና ዳኝነት
ከፍተኛው – 17
ዝቅተኛው ደግሞ -7 መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
እንዲሁም ረዳት ዳኞች ደግሞ
ከፍተኛው-17
ዝቅተኛው – 8 ያክል ጨዋታዎች አጫውተዋል።
ይህም ባሳዩት የጨዋታ የመምራት ብቃት መሠረት ምደባው ሊከናወን ችሏል፡፡
በ2009 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የወድድር ዘመን በዲሲፒሊን ኮሚቴ የገንዘብ ቅጣት ጋር በተያያዘ በአጠቃላይ የቅጣት ገንዘብ 659,000 ሺ ብር በቅጣት ተወስኗል፡፡
በዚህም መሠረት 405,000 ሺ ብር ገቢ መሆን ችሏል ቀሪ 253,500 ሺ ብር ገቢ እንዳልተደረገ ተጠቅሷል ፡፡
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎች ከታች የዘረዘሩትን የመስላሉ
በምድብ- ሀ
ባህር ዳር ከተማ ከ አክሱም ከተማ
ሱሉልታ ከተማ ከ አዲስአበባ ከተማ
ቡራዩ ከተማ ከ ፌደራል ፖሊስ
ደሴ ከተማ ከ ለገጣፎ ለገዳዲ
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ወሎ ኮምቦልቻ
የካ ክፍለ ከተማ ከ ሰበታ ከተማ
አውስኮድ ከ ኢትዮጵያ ውሀ ስፖርት
ሽሬ እንዳላስላሴ ከ ኢትዮጵያ መድን
በምድብ – ለ
ሻሸመኔ ከተማ ከ ከፋ ቡና
ሀዲያ ሆሳዕና ከ ስልጤ ወራቤ
ሚዛን አማን ከ ጅማአባቡና
ወልቂጤ ከ ናሽናል ሲሚንት
ድሬደዋ ፖሊስ ከ ሀላባ
መቂ ከተማ ከ ደቡብ ፖሊስ
ዲላ ከተማ ከ ሀምበሪቾ
ቡታጀራ ከ ነገሌ ቦረና
የ2010 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ጥቅምት 24 እንደሚጀመረ ተገልጿል፡፡
ሙሉውን ፕሮግራም በቀጣይ በድህረ ገፃችን እምንለጥፍ መሆናችንን እንገልፃለን
አስተያየት ይስጡ