የፕርሚየር ሊጉ ተሳታፊ ክለቦች ለውድድር ሟሟያ መክፈል ያለባቸው በድምሩ ከሳባት ሚልዮን ብር በላይ እዳ እንዳለባቸው ተገልጿል ::

 

መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ ዛሬ ባቀረቡት ሪፖርት ዘጠኝ ክለቦች የሊግ ምዝገባ የኮሚሽነር እና የዳኞች ክፍያን በከፊል እንደፈፀሙ የተናገሩ ሲሆን ተመሳሳዩን ክፍያ ግን ሰባት ክለቦች ከነጭራሽኑ እስከ አሁን እንዳልፈፅሙ አብራርተዋል ::

በከፊል ክፍያ የፈፀሙ ክለቦች ዝርዝር እና የገንዘብ መጠን ከስር ተገልጿል ::

ወላይታ ድቻ 750,000 ብር ሲከፍል 120,000 ብር ቀሪ እንዳለበት ተነግራል ::

ቅዱስ ጊዮርጊስ ፤ ኢትዮጵያ ቡና ፤ ድሬድዋ ከተማ ፤ ሀዋሳ ከነማ እና ፋሲል ከነማ እስካሁን 708,000 ብር የከፈሉ ሲሆን 162,000 ብር ቀሪ ክፍያ አለባቸው ::

መቐለ 70 እንደርታ በበኩሉ 570,000 ብር የከፈለ ሲሆን 300,000 ብር ቀሪ ክፍያ እንዳለበት ተገልጿል ::

ባህርዳር ከተማ 510,000 ብር የከፈለ ሲሆን ቀሪ 360,000 ብር እንዳለበት ተገልጿል ::

በከፊል ክፍያቸውን ከፈፀሙ ክለቦች አንዱ አዳማ ከተማ ሲሆን ነገር ግን የአዳማ ከተማ ቀሪ ክፍያ መጠን ስላልተገለፀ ለማወቅ አልተቻለም ::

ከነዚህ ውጪ ያሉት ( ሰበታ ከተማ ፤ ወልቂጤ ከተማ ፤ ጅማ አባ ጅፋር ፤ሲዳማ ቡና ፤ ወልዋሎ አዲግራት ዩ. ፤ ስሁል ሽረ እና ሀደያ ሆሳዕና ) ክለቦች እያንዳንዳቸው 870,000 ብር እዳ ያለባቸው ሲሆን ከዛሬ የካቲ 21/2012 ጀምሮ የማይከፍሉ ከሆነ ከውድድር ውጪ እንዲሆኑ እና የየካቲት ወር የተጫዋቾች የዝውውር ላይ ተሳታፊ እንዳይሆኑ እገዳ ተጥሎባቸዋል ::

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team