መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ የጨዋታ ዘገባ | ፈረሰኞቹ የሸገር ደርቢን በሙሉአለም መስፍን ብቸኛ ግብ በድል ማጠናቀቅ ችለዋል
ቅዱስ ጊዮርጊስኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | ፈረሰኞቹ የሸገር ደርቢን በሙሉአለም መስፍን ብቸኛ ግብ በድል ማጠናቀቅ ችለዋል

አጋራ
አጋራ

የውድድር ዓመቱ እጅጉኑ ተጠባቂ የሆነው የሸገር ደርቢ ዛሬ በ10 ሰዓት በሁለቱም ደጋፊዎች ባማረ እና ባሸበረቀ ድጋፍ ታጅቦ ተካሂዷል። ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት በኩላሊት ህመም ተጠቅታ በእግርኳስ ወዳዱ ህብረተሰብ ርብርብ ከህመሟ ያገገመችውን የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዋ ሀያት ስታድዮሙን በመዞር እግርኳስ አፍቃሪው ከህመሟ እንድትድን ላደረገላት ድጋፍ ምስጋና መስጠት ችላለች።

በጨዋታው የመጀመሪያ አስራ አምስት ደቂቃዎች እንደተጠበቀው ኢትዮጵያ ቡናዎች ኳስን በመቆጣጠር ለመጫወት ሲሞክሩ በአንፃሩ ደግሞ ፈረሰኛዎቹ በመጠኑም ቢሆን ፕሬስ በማድረግ ቡናማዎቹ ኳስን ከራሳቸው አጋማሽ ይዘው እንዳይወጡ ሲያደርጉ ተስተውሏል።

ቅዱስ ጊዮርጊሶች የመጀመሪያ ለጎል ቅርብ የሆነችዋን ሙከራ ቀኝ ተከላካዩ ደስታ ደሙ አማካኝነት ማድረግ ሲችሉ: ደስታ ከግብ ጠባቂ ጋር ተገናኝቶ ኳሷን በቀላሉ ግብ ማድረግ የሚችልባትን እድል አግኝቶ የነበረ ቢሆንም ሳይጠቀምባት ቀርቷል።

ኳስን በተከላካይ ስፍራ በመቀባበል ቦታ እያስከፈቱ ወደተጋጣሚ ግብ የመድረስ እቅድ የነበራቸው የሚመስሉት ኢትዮጵያ ቡናዎች በተደጋጋሚ ኳስን በጥሩ ሁኔታ በራሳቸው የሜዳ አጋማሽ ከተቀባበሉ በኋላ ኳሶቻቸው በፈረሰኞቹ ተጨዋቾች እየተጨናገፉባቸው ወደ ተጋጣሚያቸው ፍፁም ቅጣት ምት ክልል መግባት ሲሳናቸው ማስተዋል ችለናል ።

በተደጋጋሚ የተሳካ የማጥቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ያቃታቸው ኢትዮጵያ ቡናዎች በመጀመሪያዎቹ ሰላሳ ደቂቃዎች ካደረጓቸው ሙከራዎች በጣም ለግብ የቀረበችዋ የግራ መስመር ተከላካዩ አህመድ ረሺድ (ሽሪላው) ከፍፁም ቅጣቱ ማእዘን በኩል የመታት ግሩም ኳስ ስትሆን: የቅዱስ ጊዮርጊሱ ኬንያዊ ግብ ጠባቂ ማታሲ ተስፈንጥሮ አድኗታል።

 

ወደኋላ አፈግፍገው እየተጫወቱ የነበሩት ፈረሰኞቹ በመልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴ ወደግብ በመቅረብ በአጥቂያቸው ጌታነህ ከበደ አማካኝነት ግሩም የግብ ሙከራ ቢያደርጉም ኳሷ ቋሚ ብረቱን መታ ወጥታለች።

ኳስን በመቆጣጠር በመጀመሪያው አጋማሽ እድሎችን ለመፍጠር ሲሞክሩ የነበሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች የመጀመሪያው አጋማሽ መጠናቀቂያ አቅራቢያ ላይ በድንቅ ቅብብል ወደ ፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን ይዘዋት የገቧትን ኳስ ለጥቂት ሳይጠቀሙባት ቀርተዋል።

ሁለተኛው አጋማሽ እንደተጀመረ ሁለት ደቂቃ ሳይሞላው የጊዮርጊሱ ጌታነህ ከበደ ከመስመር የተሻገረችለትን እና በግንባር የሞከራትን ኳስ የቡናው ግብጠባቂ በድንቅ ሁኔታ አውጥቷል።

እንደመጀመሪያው አጋማሽ ሁላ በሁለተኛው አጋማሽ መጀመሪያ አስር ደቂቃዎች ኳስን በአጭሩ በመቀባበል ለመመስረት ሲሞክሩ የተስተዋሉት ኢትዮጵያ ቡናዎች በቂ የግብ እድልን ለአጥቂዎቻቸው መፍጠር ሲያቅታቸው ተመልክተናል።

የፈረሰኞቹ ዘጠኝ ቁጥር ጌታነህ ከበደ በረጅም የተሻገረችለትን ኳስ ከኢትዮጵያ ቡና ሁለት ተከላካዮች ጋር በመፋለም ኳሷ እንድትወጣ በማድረግ ለቡድኑ የማዕዘን ምት ማስገኘት ችሏል። የማዕዘን ምቷን ጋዲሳ መብራቴ ያሻማት ኳስ በግሩም አቋቋም ላይ ይገኝ የነበረው ሙሉአለም መስፍን (ዲኮ) ኳሷን በቀኝ እግሩ በመግጨት የጨዋታውን ብቸኛ እና ቡድኑን አሸናፊ ማድረግ የቻለችዋን ግብ ማስቆጠር ችሏል።

ግቧ ከተቆጠረች በኋላ ኢትዮጵያ ቡናዎች ኳስን በመቆጣጠር ወደ ግብ ለመድረስ በተደጋጋሚ ቢሞክሩም በቂ የግብ እድል መፍጠር አልቻሉም ነበር። በአንፅሩ ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊሶች ውጤታቸውን አስጠብቀው ለመውጣት እና ኳስን በረጅሙ ለአጥቂዎቻቸው በማሻገር የግብ እድልን ለመፍጠር ሲሞክሩ ተስተውለዋል።

የጨዋታው መጠናቀቂያ ሲቃረብ ኢትዮጵያ ቡናዎች በተጋጣሚያቸው የሜዳ ክፍል በርካታ ኳሶችን በመቀባበል ለጎል የሚሆኑ እድሎችን ለመፍጠር ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው ቀርቷል። ጨዋታውም ፍፁም ሰላማዊ በሆነ የደጋፊዎች ውብ ድባብ በፈረሰኞቹ 1-0 አሸናፊነት መጠናቀቅ ችሏል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...