“ዳኛው ጠቅላላ የጨዋታው መንፈስ ስለረበሸው ጨዋታው እንደዚህ ነው ብዬ መናገር አልችልም” ሳምሶን አየለ
“የተረጋጋ ነገር ባይኖርም ግብ አስቆጥረን ማሸነፍ ችለናል እና ለቀጣይ ጥሩ ስንቅ ይሆነናል” ገብረመድህን ሀይሌ
ትግራይ ስታድየም ላይ ተካሂዶ በምዐም አናብስቶቹ አሸናፊነት ከተጠናቀቀው የመቐለ 70 እንደርታና ስሑል ሽረ ጨዋታ በኃላ የሁለቱ ቡድን አሰልጣኞች ሚከተለውን አስተያየት ሰጥተዋል።
አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ (ስሁል ሽረ)
- ማሰታውቂያ -
“ጨዋታው እንዳያችሁት የተጫወትነው ከመቐለ 70 እንደርታ ነው።መቐለ 70 እንደርታ ደግሞ ውድድሩን እየመራ ያለ ክለብ ነው ስለዚ በሜዳውና በሰፊ ደጋፊ ታግዞ እንደመጫወቱ መጠን ትንሽ ጠንካራ ሊሆን እንደሚችል እኛም ገምተን ነበር።ነገር ግን ይዘን የገባነው የጨዋታ አቀራረብ ለመተግበር በማንችልበት ሁኔታ ጨዋታው በተጀመረ በ13ኛው ደቂቃ ላይ ተጨዋቻችን በቀይ ካርድ በመውጣቱ የተለየ ነገር መስራት አልቻልንም።እኔ ስለዛሬው ጨዋታ ዳኛው ጠቅላላ የጨዋታው መንፈስ ስለረበሸው ጨዋታው እንደዚህ ነው ብዬ መናገር አልችልም።
አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ (መቐለ 70 እንደርታ)
“ጨዋታው ሁለታችን ቡድኖች አሸንፈን ስላልመጣን በርግጥ እነሱ አንድ ነጥብ ይዘው ወጥተዋል እኛ ግን ከሜዳችን ውጪ ያጣነውን ሥስት ነጥብ ለማካካስ በሚል ፍላጎት ነው የገባነው።ባጋጣሚ ሆኖ ጨዋታው መጀመርያ ላይ የተሰጠው ቀይ ካርድ ዳኛው ላይ ተፅእኖ ፈጥሯል፤ዳኛው ተጨዋቾቹ በስራአት እንዳይጫወቱ አድርግዋቸዋል።ቀይ ካርዱ ትክክል ነው አደለም ለሚለው ማንም ሊያየው ሚችል ነገር ነው።ከዚህ በላይ ግን ከአጋጣሚው በኃላ ጨዋታውን ዳኛው ጨዋታውን መቆጠጠር ይችል ነበር በዛ ምክንያት ወደ አላስፈላጊ ጨዋታዎች መግባት ይታይ ነበር።ሆኖም ከእረፍት በኃላ የቁጥር ብልጫም ስለነበረን እሱን ለመጠቀም ይዘን የገባነው ታክቲክ ለመተግበር ተጨዋቾቼ ዲሲፒሊን አልነበሩም።ሆኖም ግን የተረጋጋ ነገር ባይኖርም ግብ አስቆጥረን ማሸነፍ ችለናል እና ለቀጣይ ጥሩ ስንቅ ይሆነናል።”