በ 11ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አዳማን ያስተናገደው ባርዳር ከተማ በፍቃዱ ወርቁ የመጀረሻ ደቂቃ ግብ 2-1 በማሸነፍ ሶስት ነጥብ ጨብጠዋል።
የጣናው ሞገድ ወደ አዲስ አበባ አቅንተው ቅዱስ ጊዩርጊስን ከገጠሙበት ስብስብ በቀይ ካርድ ከሜዳ የተሰናበተው ሳሙኤል ተስፋየ በአዳም ሲሴኮ ተክተው ሲገቡ። አዳማ ከተማ በበኩላቸው በሜዳው ሀድያ ሆሳዕናን ሲያሸንፉ ያልተጠቀሙባቸውን ፉአድ ፈረጃ እና በመናፍ ዐወል አስገብተዋል።
- ማሰታውቂያ -
ለተመልካቾች ብዙም ሳቢ ያልነበረው የመጀመሪያው አጋማሽ ሁለት ግቦችን ማስተናገድ ችሏል። በተለይ በመጀመሪያዎቹ 10 ደቂቃዎች በሁለቱም ቡድኖች በኩል ኳስን ተቆጣጥሮ ለመጫወት ሞክረዋል።በ 10ኛው ደቂቃ ዜናው ፈረደ በቀኝ መስመር በኩል ጥሩ ሙከራ አድርጓል። በተመሳሳይ አዳማዎችም በቀኝ በመስመር በኩል በቡልቻ ሹራ አማካኝነት አከናውነዋል። በ 13ኛው ደቂቃም በጨዋታው ጥሩ ሲንቀሳቀስ የነበረው በረከት ደስታ በቀኝ መስመር አሾልኮ ያቀበለውን ኳስ ፉአድ ፈረጃ በአስደናቂ ሁኔታ አስቆጥሮ ቡድኑን መሪ አድርጓል።
ከጎሉ መቆጠር በኃላ ጫና ፈጥረው የተጫወቱን የጣናው ሞገዶች አቻ ለመሆን የወሰደባቸው 6 ደቂቃ ብቻ ነበር ማመዱ ሲዲቤ ላይ የተሰራውን ጥፋት ተከትሎ በተሰጠው የቅጣት ምት ግርማ ዲሳሳ አሻምቶ ራሱ ማመዱ ሲዲቤ አስቆጥሮ አቻ ማድረግ ችሏል። በጎሏ የተነቃቁት ባለሜዳዎቹ ይበልጥ ጫና ፈጥረው በመተጫወት በማማዱ ሲዲቤ እና ግርማ ዲሳሳ አማካኝነት ሙከራ ተከታታይ ጥቃቶችን ሲሰነዝሩ። በአዳማዎች በኩል በረከት ደስታ ሁለት ግዜ ያሻገረውን ኳስ ቡልቻ ሹራ ሳይጠቀምበት የቀረው ኳስ ለሙከራ የተቃረቡ ነበሩ። በመጀመሪያው አጋማሽ መገባደጃ ላይ ሳምሶን ያሻገረውን የቅጣት ምት ማመዱ ሲዲቤ በግንባሩ ገጭቶ ወደ ውጭ ወጥታ 1-1 በሆነ ውጤት ለእረፍት አምርተዋል።
በሁለተኛው አጋማሽ በተለይ የተጫዋች ቅያሪ በማድረግ ተጭነው መጫወት የቻሉት ባለሜዳዎቹ። 54ኛው ደቂቃ ሳምሶን ጥላሁን ያሻማውን የማእዘን ምት ግብ ጠባቂው ጃኮፕ ፔንዝ በትክክል ሳይቆጣጠራት ቀርቶ ከጁ አምልጣ ስተወጣ ያገኛት አዳማ ሲሲኮ ሳይጠቀምበት የቀረችው አስቆጪ ሙከራ ነበረች። በአንፃሩ አዳማ ከተማዎች ረጃጅም ኳሶችን ሲጠቀሙ ተስተውሏል። በ 70ኛው ደቂቃ ሰለሞን ውዴሳ የሰራውን ስህተት ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል።
ከዚህ ደቂቃ በኃላ በተደጋጋሚ ወደ አዳማ የጎል ክልል መድረስ የቻሉት ባህር ዳሮች ጎል ማስቆጠር ግን አልቻሉም። በተለይ በ85ኛው ደቂቃ በግራ መስመር ግርማ ዲሳሳ ሰብሮ ቢገባም የአዳማው ግብ ጠባቂ ፔንዜ አድኖበታል ። በ87ኛው ደቂቃ ኢስማኤል ሳንጋሪ አዳማዎችን መሪ የሚያደረገው አጋጣሚ አባክኗል። በጭማሪ በ94ኛው ደቂቃ ፍቃዱ ወርቁ ያሻማውን ኳስ ሲዲቤ በግንባሩ ገጭቶ ለጥቂት ወደ ውጭ ወጦበታል።ተጨማሪ ጎል ለማስቆጠር ተጭነው ሲጫወቱ የነበሩት ባለ ሜዳዎቹ ከማዕዘን ግርማ ዲሳሳ ያሻገረውን ኳስ ፍቃዱ ወርቁ አስቆጥሮ ባለሜዳዎቹን 2-1 አሸንፈው እንዲወጡ አስችሏል።