መነሻ ገጽ ሰበታ ከተማ የጨዋታ ዘገባ | ድሬዳዋ ከተማ ወደ ድል የተመለሰበትን ውጤት አስመዝግቧል።
ሰበታ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባድሬዳዋ ከተማ

የጨዋታ ዘገባ | ድሬዳዋ ከተማ ወደ ድል የተመለሰበትን ውጤት አስመዝግቧል።

አጋራ
አጋራ

 

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ አጋማሽ ሲደረጉ ድሬዳዋ ከተማ በሜዳው ሰበታ ከተማን አስተናግዶ 1-0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ደረጃውን ወደ 11ኛ በማሳደግ ከወራጅ ቀጠናው መውጣት ችሏል።

በ10ኛው ሳምንት ሰበታ ከተማ በሜዳው ሀዋሳ ከተማን ድል ያደረገ ሲሆን ድሬዳዋ ከተማ ደግሞ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ በወልቂጤ ከተማ ሽንፈት ማስተናገዱ ይታወሳል። ስለሆነም ሰበታ ከተማ ድሉን ለማስቀጠል ድሬዳዋ ከተማም ከሽንፈት ወደ ድል በመመለስ ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት ያደረጉት ጨዋታ በመሆኑ በደጋፊዎቻቸው ዘንድ በጉጉት ተጠብቆ ነበር።

በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ድሬዳዋ ከተማዎች ሰበታ ከተማን ተጭነው መጫወት ችለው ተስተውለዋል። ይህንንም ተከትሎ በተደጋጋሚ በኦዶንጎ ሪችሞንድ እና በያሬድ ታደሰ አማካኝነት የሰበታ ከተማን ተከላካዮች ሲያስጨንቁ ውለዋል። ሰበታ ከተማዎችም ወደ ኋላ በማፈግፈግ በመልሶ ማጥቃት ለመጫወት ሲሞክሩ ታይተዋል።

በጨዋታው 19ኛው ደቂቃ ላይ የድሬዳዋ ከተማው ሙህዲን ሙሳ ያስቆጠራት ግብ ድሬዳዋን ከወራጅ ቀጠናው ለማውጣት በቂ ሆና ተገኝታለች። ውጤቱንም ተከትሎ ድሬዳዋ ከተማ በ13ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሽንፈት ያስተናገደው ሰበታ ከተማ በ14 ነጥቦች 8ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል።

ሊጉን መቐለ 70 እንደርታ በ22 ነጥቦች ሲመሩ በሸገር ደርቢ ድል የቀናቸው ቅዱስ ጊዮርጊሶች በ2ነጥብ ዝቅ ብለው በ20ነጥቦች ሁለተኛ እንዲሁም ወደ ጅማ አቅንተው ያለግብ አቻ የተለያዩት ፋሲል ከተማዎች በ19ነጥቦች 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ወላይታ ድቻ፣ ጅማ አባጅፋር እና ሀድያ ሆሳዕና ደግሞ ከ14ኛ እስከ 16ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል። የኮከብ ግብ አግቢነቱን የፋሲል ከተማው ሙጂብ ቃሲም በ10 ግቦች ሲመራ የባህር ዳር ከተማው ፍፁም አለሙ፣ የመቐለ 70 እንደርታው አማኑኤል ገ/ሚካኤል እና የሀዋሳ ከተማው ብሩክ በነዠየነ በእኩል 6ግቦች ይከተሉታል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...

መቐለ 70 እንደርታዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ዘርአይ ሙሉ በቴክኒክ አማካሪነት ወደ ፕሪምየር ሊጉ ተመልሷል

አሰልጣኙን ያሰናበተው መቐለ 70 እንደርታ ሌላ ሹመትን ፈፅሟል። በያዝነዉ የዉድድር አመት ደካማ...