የኢትዩጲያ ፕሪምየር ሊግ 11ኛ ሳምንት መርሀ ግብር አካል የሆነው ሀዋሳ ላይ የተከናወነው የሀዋሳ ከተማ እና ወላይታ ድቻ ጨዋታ በአለልኝ አዘነ የመጨረሻ ደቂቃ ግብ ሀይቆች 2-1 በሆነ ውጤት አሸንፈው ወጥተዋል።

ሁለቱምቡድኖች ከባለፈው አሰላለፋቸው የአንድ ተጫዋች ብቻ ለውጥ አድርገው ገብተዋል።በዚህም
ሀይቆች ወደ አዲስ አበባ አቅንተው በሰበታ 2-1 ከተሸነፈው ጨዋታ ያልተጠቀመበትን ሄኖክ አየለን በቋሚ አሰላለፍ ሲያካትት። ተጋባዦቹ የጦና ንቦች የሊጉን መሪ 1-0 ሲያሸንፉ ያለተጠቀመበትን ብቸኛው ፀጋየ አበራ ይዞ ወደ ሜዳ ገብቷል።
በኢንተርናሽናል ዳኛ ዮናስ ካሳሀን እየተመራ የጀመረው ይህ ጨዋታ ኳስ ወደ ግብ ለመድረስ የፈጀባት አንድ ደቂቃ ብቻ ነበር። ከመሀል ሜዳ የተጀመረችውን ኳስ ያገኘው የግራ መስመር አጥቂው መስፍን ታፈሰ ሳጥን ውስጥ ከፍ አድርጌ ለሄኖክ አየለ አቀብላለው ሲል በመሀል ተከላካይ ስፍራ የተሰለፈው ውብሸት አለማየሁ ሳጥን ውስጥ በእጁ ቢነካውም የመሀል ዳኛ ሳይመለከቱት በመቅረታቸው ጨዋታው ቀጥሏል።
በመጀመሪያዎቹ አስር ደቂቃዎች ባለሜዳዎቹ ከዘለአለም ኢሳያስ በሚነሱ ኳሶች በሁለቱም መስመር ለተሰለፉት አጥቂዎቻቸው ኳስ ለማድረስ ሲጫወቱ ቢስተዋሉም። በይበልጥ ግን ብሩክ በየነ የተሰለፈበትን የቀኝ መስመር አጋድሎ በመጫወት አጋጣሚዎችን ለመፍጠር ሞክሯል።በዚህም ሄኖክ አየለ እና ብሩክ በየነ ያደረጉትን ግሩም አንድ ሁለት ቅብብል ብሩክ በየነ ተቆጣጥሮ ቢሞክራትም ግብ ጠባቂው መክብብ ደገፉ የተቆጣጠረበት ማሳያ ነበረች።ደቂቃዎች በገፉ ቁጥር ተጋባዦቹ የጦና ንቦች ወደ ኋላ አፈግፍገው ጥንቃቄ የተሞላበት የመከላከል አጨዋወት ስልት ሲከተሉ። በሁለት አጥቂ አማራጫቸውን አድርገው ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል ለመድረስ ሲታትሩ ሲታትሩ ታይተዋል። በጨዋታው ጥሩ ሲንቀሳቀስ የነበረው ውብሸት አለማየው እድልሎችን መመጠቀም ችግር እንጂ የሀዋሳን ተከላካዩች ሲያፈረክርካቸው ይስተዋል ነበር።
ባንፃሩ ሀይቆቹ የድቻዎች አጨዋወት በመሀል ሜዳው ክፍል እና በተከላካይ ያለውን ስፋት ስላጠበቡባቸው ጥቃት ከርቀት ለመሰንዘርተ ተገደዋል።ሄኖክ ድልቢ በተደጋጋሚ ከርቀት ወደ ግብ ስሞክራቸው የነበሩ ኳሶች አብነት ናቸው። እንደ ጋባዦቹ ሁሉ ወላይታ ዲቻዎች በተደጋጋሚ ከርቀት ጥቃቶችን ዘንዝረዋል።23ኛ ደቂቃ ላይ ፀጋዬ አበራ ከርቀት በቀጥታ ወደ ግብ መትቶ ለጥቂት ባግዳሚ የወጣችበት እና እዩብ አለማየው ከተመሳሳይ ቦታ ወደ ግብ ሞክሮ ወደ ውጪ የወጣችበት የሚጠቀሱ ናቸው።የወላይታ ድቻ ግብ ጠባቂ መክብብ ደገፉ 40ኛው ደቂቃ ላይ ባጋጠመው ጉዳት ጨዋታውንመቀጠል ሳይችል ቀርቶ ከሜዳ ወቷል።እሱን ተክቶ የገባው ግብ ጠባቂው መኳንንት አሸናፊ ግብ ለማስተናገድ ሶስት ደቂቃ ብቻ ፈድቶበታል።ሄኖክ አየለ ሳጥንውስጥ ከመስፍን ታፈሰ ያገኛትን ኳስ ተጠቅሞ ኳስ እና መረብን በማገናኘት ሀዋሳዎችን 1-0 መሪ በማድረግ ለእረፍት ወተዋል ።

በሁለተኛው አጋማሽ ባለ ሜዳዎች ውጤት አስጠብቆ ለመውጣት መከላከልን መሰረት በማድረግ ኳስን ይዘው ለመጫወት ሙከራ አድርገዋል።ከመጀመሪያው አጋማሽ ለየት ያለ አቀራረብ ወደ ሜዳ ይዘው የገቡት ወላይታ ድቻዎች ስኬታማ የሚባል የማጥቃት አጨዋወትን ተከትለዋል።ሳጥን ውስጥ የነበረው ቸርነት ጉግሳ ከቀኝ መስመርየተሻገረለትን ኳስ ሳይቆጣጠራት ቀረ እንጂ እንግዳዎቹን አቻ የማድረግ አጋጣሚ ነበረው።በዛሬው ጨዋታ ከወትሮ በተለ ጥፋቶችን ሲሰራ የነበረው የሀዋሳ የተከላካይ ስፍራ ግብ ከማስተናገድ ወደኋላ አላለም 79ኛው ደቂቃ ተስፋዬ አለባቸው መሬት ለመሬት አክርሮ የመታውን ኳስ ላውረንስ ላርቴ አወጣለው ሲል ኳስ ተጨርፋበት አጠገቡ የነበረው ባዬ ገዛኸኝ ተቆጣጥሮ ወደ ግብ በመቀየር ድቻዎችን አቻ ማድረግ ችሏል።

ግብ ከተቆጠረባቸው በኳላ ተጭነው መጫወት የቻሉት ሀዋሳዎች በርካታ እየግብ አጋጣሚዎችን መፍጠር ችላዋል።ከማአዘን ምት ዘላለምኢሳያስ ያሻማውን ኳስ በወላይታ ድቻ ተከላካዩች ተገጭታ ስትመለስ ያገኛትን ኳስ ብሩክ በየነ በግንባሩ ገጭቶ አገባው ሲባል ከግቡ አፋፍ ላይ እዩብ አለማየው በግንባሩ ገጭቶ በማውጣት ቁጭት ቢፈጥርባቸውም የማታ ማታ የአሸናፊነቱን ግን ከአለልኝ አዘነ 93ኛ ደቂቃ ላይ አግኝተዋል።

በድጋሚ ዘላለም ኢሳያስ ከተመሳሳይ ቦታ ያሻማውን የመአዘን ምት አለልኝ አዘነ በግንባሩ ገጭቶ ሀዋሳዎችን ሶስት ነጥብ ማሳካት ሲችሉ የወላይታ ድቻዎች ተከታታይ አሸናፊነት ተገቷል።
አስተያየት ይስጡ