ደሴ ከተማ ለቀድሞ ተጫዋቾቹ ደሞዛቸውን እንዲከፍል ተወሰነ።
ፌደሬሽኑ ደሞዛችን አልተከፈለንም በማለት ክስ ያስገቡት በከፍተኛው ሊግ የሚሳተፈው የደሴ ከተማ ተጫዋቾች ደሞዛቸው እንዲከፈላቸው ውሳኔ አስተላልፏል። ሚሊዮን በየነ፣አለማየሁ ማሞ፣ሊቁ አልታየ እና ኃ/ማርያም እሸቱ የተባሉ ተጫዋቾች ከ1/08/11 እስከ 30/17/12 ከክለቡ ጋር የሚያቆያቸው ውል ቢኖራቸውም ክለቡ ዝግጅት በሚያደርግበት ወቅት አልመጠራታቸው ጠቅሰው ውላቸው ሳያልቅ ክለቡ እንዳሰናበታቸው ነበር ቅሬታቸውን ለፌደሬሽኑ ያቀረቡት የቅሬተ ደብዳቤ የሚያመላክተው። ሆኖም ክለቡ በራሳቸው ፍቃድ እንጂ እኔ አላሰናበትኳቸውም ሲል በ 5ገፅ የተፃፈ የማስረጃ ሰነድ በማቅረብ ለተጫዋቾቹ ደብዳቤ እንደላከ ቢያሳውቅም። ማስታወቂያው ባወጣበት እለተ ግልቤጭ ለገለልተኛው አካል የኢትዮጵያ እግር ኳስ የላከ አለመሆኑን ተከትሎ ፌደሬሽኑ የሚከተለውን ውሳኔ አሳርፏል።
ውሳኔ
1.ክለቡ ለተጫዋቾቹ ከ2012 ጀምሮ ይህ ውሳኔ እስከተላለፈበት ድረስ ደሞዛቸውን እንዲከፍል
2.ክለቡ ለቀረው የውል ጊዜ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ እንዲመልስ ካልፈለገ ደግሞ የቀሪ ውላቸውን ደሞዝ እንዲከፍል
3. ክለቡ በ7 ቀን ውስጥ ክፍያውን ካላጠናቀቀ ምንም አይነት አገልግሎት ከፌደሬሽኑ አንደማያገኝ ውሳኔው ያመላክታል።
- ማሰታውቂያ -
የፌደሬሽኑ ውሳኔ የሚከተለው ይመስላል👇👇👇👇