መነሻ ገጽ ሀዋሳ ከተማ የጨዋታ ዘገባ | ሰበታ ከተማ ሀዋሳን በማሸነፍ ወሳኝ የሜዳ ሶስት ነጥብ አሳካ
ሀዋሳ ከተማሪፖርትሰበታ ከተማየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የጨዋታ ዘገባ | ሰበታ ከተማ ሀዋሳን በማሸነፍ ወሳኝ የሜዳ ሶስት ነጥብ አሳካ

አጋራ
አጋራ

 

በ 10ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አዲስ አበባ ስታዲዮም ላይ ሀዋሳ ከተማን ያስተናገደው ሰበታ ከተማ በፍፁም ገብረማርያም እና አዲሱ ተስፋየ ግብ 2-1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ባለሜዳዎቹ ሰበታ ከተማዎች ወደ ትግራይ አቅንተው በሊጉ መሪ መቐለ 70 እንደርታ 2-0 ከተሸነፉበት ቋሚ አሰላለፍ የሁለት ተጫዋቾች ለውጥ በማድረግ ጌቱ ኃለማርያምን እና ሰይድ አሊን በማስወጣት እንዳ ዘውግ እና ናትናኤል ጋንቹላን በመተካት ወደ ሜዳ ሲገቡ በአንፃሩ እንግዳዎቹ ሀይቆች ከወልቂጤ ጣፋጭ ሶስት ነጥብ ካገኙበት አሰላለፍ የሶስት ተጫዋቾች ለውጥ አድርገዋል። በዚህም በዳንኤል ደርቤ፣አክሊሉ ተፈራ እና ሄኖክ አየለ ምትክ ከዲስአለም ተስፋየ፣ ዘላለም ኢሳያስን እና መስፍን ታፈሰን አስገብተው ወደ ጨዋታ ገብተዋል።

በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ኳስን መሰረት አድርገው በመጫወት ወደ ግብ ለመድረስ ቢፈልጉም ሙከራ በማድረግ ረገድ ግን የተገደቡ ነበሩ። ባለሜዳዎቹ ኳስን ከግብ ጠባቂ በመመስረት ሁለቱን መስመር ተጠቀመው ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል ለመድረስ ሙከራ ቢያደርጉም ሲሰሯቸው የነበሩ የቅብብል ስህተቶች ኢላማቸውን የጠበቀ ካለማድረጉ በተጨማሪ ጥቃት እንዲሰነዘርባቸው ምክንያት ነበር። ወጣቱ አጥቂ ብሩክ በየነ የሰበታ አማካዮች ስህተት በሚገባ ተመልክቶ ወደ ግብ የመታትን ለጥቂት በግቡ አናት የወጣችው ማሳያ ነበር። ሀዋሳ ከተማዎች ኳስ በሚያገኙበት አጋጠጣሚ ለመስፍን ታፈሰ በማሻገር ኳስ እና መረብን ለማገናኘት ጥረት ሲያደርጉ ተሰተውሏል። መስፍን ታፈሰ ከመሀል ሜዳ የተላከችለትን ኳስ ይዞ ወደ ግብ ቢደርስም ግብ ጠባቂው ዳንኤል ኣጃዮ ያመከነበት ኳስ ሀዋሳ መሪ ሊሆን የሚችልበት አጋጣሚ ነበረች።

ሁለቱንም መስመር በመጠቀም የግብ አማራጮቹ በመፈለግ ውጤታማ ያደረጋቸው ሰበታዎች የቀኝ መስመር አጥቂው ባኑ ዲያባራ ኢኖህ ቤሊንጋ ባጠበበት ቦታ በቀጥታ አክርሮ መትቶ ሲተፋት በጥሩ አቋቋም ላይ የነበረው ፍፁም ገብረማርያም ስትመለስ ያገኛትን ኳስ ወደ ግብነት ቀይሮ ክለቡን መሪ ማድረግ ችሏል። ከግቧ መቆጠር በኋላ የተነቃቁት ሀዋሳዎች ኳስን ተቆጣጠርው በግራ መስመር በኩል አጋድለው በመጫወት የአቻነት ግብ ለማግኘት ቢታትሩም ሳይሳካላቸው ቀርቶ በሰበታ ከተማ 1-0 መሪነት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።

በሁለተኛው አጋማሽ ባለሜዳዎቹ ውጤታቸውን አስጠብቀው ለመውጣት ወደ ኋላ በማፈግፈፈግ በመልሶ ማጥቃት የሚገኙ እድሎችን ለመጠቀም ሲሞክሩ። በአንፃሩ ሀይቆች ደግሞ ኳስን በመቆጣጠር ማጥቃቶን ምርጫቸው አድርገው ወደ ሜዳ በመግባት እድሎችን ለመፍጠር ሞክረዋል። ብሩክ በየነ ከቀኝ መስመር ወደ ሳጥኑ ይዞ በመግባት አክርሮ መትቶ ወደ ውጭ የወጣችበት እና መስፍን ታፈሰ ሳጥነሸ ውስጥ አክርሮ መትቶ ለጥቂት በአግዳሚው የወጣችበት በሀጻሳዎች በኩል የሚያስቆጩ ሙከራዎች ነበሩ። በአንፃሩ ባለሜዳዎቹ በመልሶ ማጥቃት ያገኙትን ጥሩ አጋጣሚ ተጠቅመው ወደ ግብ ቢሞክሩም ግብ ጠባቂው ኢኖህ ቤሊንጋ አውጥቷት የተገኘችውን የማእዘን ምት በታደለ መንገሻ ስትሻማ አዲስ ተስፋዮ አግንቶ በመጠቀም ኳስ እና መረብን በማገናኘት መሪነቱን ወደ ሁለት ከፍ ማደረግ ችሏል።

ግብ ካስተናገዱ በኋላ ተጭነው መጫወት የቻሉት ሀይቆች በጨዋታው ድንቅ እንቅስቃሴን ሲያደርግ በነበረው ወጣቱ አጥቂ መሰፍን ታፈሰ አማካኝነት ከተከላካዮች መሀል አፈትልኮ በመውጣት ባያስቆራት ግብ የመጀመሪያ ግባቸውን አግኝተዋል። ጨዋታው ተጨማሪ ግብ ሳያስተናግድ በባለሜዳዎቹ 2-1 አሸናፊነት ሲጠናቀቅ። ሰበታ 14 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሽንፈት ያስተናገዱት ሀዋሳዎች በ13 ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...

መቐለ 70 እንደርታዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ዘርአይ ሙሉ በቴክኒክ አማካሪነት ወደ ፕሪምየር ሊጉ ተመልሷል

አሰልጣኙን ያሰናበተው መቐለ 70 እንደርታ ሌላ ሹመትን ፈፅሟል። በያዝነዉ የዉድድር አመት ደካማ...