መነሻ ገጽ ወልዋሎ የጨዋታ ቅድመ-ዕይታ | ፋሲል ከነማ ከ ወልዋሎ
ወልዋሎዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግፋሲል ከተማ

የጨዋታ ቅድመ-ዕይታ | ፋሲል ከነማ ከ ወልዋሎ

አጋራ
አጋራ

 

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ነገ(ሰኞ) ሁለት ጨዋታዎችን በማስተናገድ ፍፃሜውን ያገኛል።በአፄ ፋሲለደስ ስታድየም ሚካሄደው የፋሲል ከነማና ወልዋሎ ጨዋታ እንደሚከተለው ዳስሰነዋል።

ጨዋታ: ፋሲል ከነማ ከ ወልዋሎ
የጨዋታ ቀን: ሰኞ ጥር 25/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ፌደራል ዳኛ ተፈሪ አለባቸው
የጨዋታ ቦታ: አፄ ፋሲለደስ ስታድየም

በ12ተኛው ሳምንት የኢትዮጲያ ፕሪምየር ሊግ በሜዳቸው ማይደፈሩት አፄዎቹ ውጤት ማጣት ውስጥ ሚገኙትን ወልዋሎዎችን በሜዳቸው አፄ ፋሲለደስ ስታድየም ያስተናግዳሉ።

በሜዳቸው 5 ጨዋታዎችን አድርገው አምስቱን ማሸነፍ የቻሉት ፋሲሎች በነገው ጨዋታ ማጥቃት ላይ መሠረት ያደረገ አጨዋወትን ይዘው ሊገቡ እንደሚችሉ ይገመታል።የኳስ ቁጥጥር ብልጫን ወስደው መጫወት ሚፈልጉት አፄዎቹ በነገው ጨዋታ ወደ ራሱ ሜዳ ክፍል ተጠግቶ ሚከላከለውን ወልዋሎን ለማስከፈት የሜዳውን የጎን ስፋት በመጠቀም ክፍተቶችን ለማግኘት ይሞክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከመጨረሻዎቹ 4 ጨዋታዎች አንድ ነጥብ ብቻ ማግኘት የቻሉት በዮውሀንስ ሳህሌ ሚመሩት ወልዋሎዎች ከገቡበት የውጤት ማጣት ለመውጣት ከነገው ጨዋታ ቢያንስ አንድ ነጥብ ማግኘት ሳያስፈልጋቸው አይቀርም።ጥንቃቄ ላይ መሰረት ያደረገ መልሶ ማጥቃትን ምርጫጨውን ሚይደርጉት ወልዋሎዎች ነገም ተመሳሳይ አቀራረብ ሊኖራቸው ይችላል።በተለይ ፊት መስመር ላይ ሚኖረው የኢታሙና ኩሜይኒ እና ጁንያንስ ናጋንጂቦ ጥምረት የወላዋሎ መልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴ ላይ ወሳኙን ሚና ሚጫወት ይሆናል።

ፋሲል ከነማ በዘንድሮው የኢትዮጲያ ፕሪምየር ሊግ 5 ጨዋታዎችን በሜዳቸው አካሂደው 14 ግቦችን ሲያስቆጥሩ አንድ ግብ ብቻ አስተናግደዋል።ከአምስቱ ጨዋታዎች አራቱ ላይ ግብ ሳያስተናግዱ መውጣት ችለዋል።

ቢጫ ለባሾቹ ወልዋሎዎች በበኩላቸው 7ተኛው ሳምንት ላይ ድሬዳዋ ከተማን ካሸነፋ በኃላ ምንም ጨዋታ ማሸነፍ አልቻሉም።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
መቐለ 70 እንደርታዜናዎች

ገረሱ ሸመና መቐለ 70 እንደርታን ተቀላቀለ

በሊጉ ለመቆየት እየዳዱ የሚገኙት መቐለ 70 እንደርታዎች ረዳት አሰልጣኝ ሾመዋል። በኢትዮጵያ እግር...

ወላይታ ድቻዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

“የቀዶ ጥገና ህክምና ይደረግለታል” የወላይታ ድቻ ስራ አስኪያጅ አቶ ምትኩ ሐይሌ

ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከባድ ጉዳትን ያስተናገደው ወጣቱ ተጫዋች ቅዱስ ቂርቆስ በምን...

ኢትዮጵያን በውጪዜናዎች

በካናዳ የኢትዮጵያዊያን የባህል እና ስፖርት ሊግ በይፋ ተመሠረተ

በካናዳ የኢትዮጵያ የባህል እና ስፖርት በሚል ስያሜ ሊግ ተቋቋመ። የኢትዮጵያን ባህል ለአለም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...