የጨዋታ ቅድመ- ዕይታ | ወልዋሎ አ.ዮ ከ ሰበታ ከተማ

የጨዋታ ቅድመ-ዕይታ | ወልዋሎ ከ ሰበታ ከተማ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ዙር ውድድሮች ከሳምንታት እረፍት በኃላ ዛሬ(ቅዳሜ) በተካሄዱ 2 ጨዋታዎች ሲጀምር ነገ(እሁድ) 6 ጨዋታዎችን በማስተናገድ ቀጥሎ ይውላል።በወልዋሎ ስታድየም ሚካሄደው የወልዋሎ ና ሰበታ ከተማ ጨዋታ እንደሚከተለው ዳሰነዋል።

ጨዋታ: ወልዋሎ ከ ሰበታ ከተማ
የጨዋታ ቀን: እሁድ የካቲት 28/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ኢንተርናሽናል አርቢትር ቴዎድሮስ ምትኩ
የጨዋታ ቦታ: ወልዋሎ ስታድየም

ከአንድ ዓመት 6 ወር ቆይታ በኃላ በ15ኛው ሳምንት ወደ ሜዳቸው የተመለሱት ወልዋሎዎች በአዲስ አሰልጣኝ እና በርካታ አዳዲስ ፈራሚ ተጨዋቾች ታጅበው ሰበታ ከተማን ያስተናግዳሉ።በመሀላቸው የሁለት ነጥብ ልዩነት ብቻ ይዘው ሚገናኙት ሁለቱም ቡድኖች ማጥቃት ላይ መሰረት ያደርገ አጨዋወትን ይዘው ሊገቡ እንደሚችሉ ይገመታል።

አዲሱ አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ቡድኑን ከተረከበ በኃላ ሁለት ልምምዶችን ብቻ ማሰራታቸውን ከግምት ሲገባ በነገው ጨዋታ ይዘውት ሊገቡ ሚችሉትን አጨዋወት ለመገመት ከባድ ያደርገዋል።ሆኖም ቡድኑ ላይ በርከት ያሉ የመስመር ተጨዋቾች መኖራቸውን ከግምት ሲገባ ፈጣን የመስመር አጨዋወትን ይከተላሉ ተብሎ ይጠበቃል። መሀል ሜዳ ላይ ተፈጥሮአዊ የአማካይ ተጨዋች እጥረት የነበራቸው ወልዋሎዎች የአመለ ሚኪያስ፣ዮናስ በርታና ሃይማኖት ወርቁ ዝውውር ማጠናቀቃቸው የመሀል ሜዳ ክፍላቸውን ሚያጠነክርላቸው ይሆናል።ተከላካይ መስመር ላይ ክፍተቶች እየታዩባቸው ሚገኙት ወልዋሎዎች የተጋጣሚያቸው ፈጣን የአጥቂ መስመር ተጨዋቾች በግምት ስታስገባ ከኃላ ሚሰርዋቸውን ስህተቶች መቀነስ ግድ ሚላቸው ይሆናል።

የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ወስደው እድሎችን በመፍጠር ጨዋታዎችን ሚያሸንፍ ቡድን ለመገንባት ሚሞክሩት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በነገው ጨዋታ ቡድናቸው ከወራጅ ቀጠናው በአንድ ነጥብ ብቻ መራቃቸውና ከሜዳቸው ውጪ ያላቸው መጥፎ ክብረወሰን በግምት ሲገባ ጥንቃቄ ላይ መሰረት ያደርገ መልሶ ማጥቃትን ምርጫጨውን ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።ሰበታዎች ከሜዳቸው ውጪ ሰባት ጨዋታዎችን አካሂደው ወልቂጤ ከተማን ካሸነፋት ጨዋታ ውጪ ስድስቱ ላይ ሽንፈት አስተናግደዋል።

Hatricksport website writer

Twitter

ዳዊት ብርሀነ

Hatricksport website writer