የጨዋታ ቅድመ-ዕይታ | ወልቂጤ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከቅዳሜ አንስቶ መካሄዳቸውን ሲጀምሩ በነገው እለትም የሁለቱን ቡድኖች ጨዋታ ያስተናግዳል።

በዚህ ሳምንት ከሚካሄዱት ጨዋታዎች መካከል በወልቂጤ ስታዲየም ወልቂጤ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና የሚያስተናግድበት ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል።

ጨዋታ: ወልቂጤ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና
የጨዋታ ቀን: ሰኞ የካቲት 09/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ፌደራል አርቢትር ዮናስ ካሳሁን
የጨዋታ ቦታ: ወልቂጤ ስታዲየም

በወልቂጤ ሜዳ በሚካሄደው በዚህ መርሀ ግብር ወልቂጤዎች በአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው እየተመሩ ከጨዋታ ጨዋታ የሊጉ ክሰተት መሆናቸውን እያሳዩ ይገኛሉ ::

ወልቂጤዎች በተለይም በሜዳቸው በሚያደርጎቸው ጨዋታዎች ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ መሆናቸውን ሲያሳዩ ካለፉት በሜዳቸው ካደረጉት ሶስት ጨዋታዎች ላይ ማግኘት ከሚገባቸው ዘጠኝ ነጥቦች ስድስቱን ማሳካት ችለዋል ::

ሲዳማ ቡናዎች ምንም እንኳን አስፈሪ የሆነ የፊት መስመር ጥምረትን ቢይዙም የተጠበቀውን ያክል ውጤት ሲያስመዘግቡ አይስተዋልም ::

በተለይም ከሜዳቸው ውጪ በሚደረጉ ጨዋታዎች ላይ ሶስት ነጥብ ማግኘት ከብዳችው ይስተዋላል :: ሲዳማ ቡና ባለፉት ከሜዳቸው ውጪ ባደረጉት ሶስት ጨዋታዎች ሶስት ነጥብ ማሳካት ሳይችሉ ሲቀሩ ዘጠኝ ጎሎች ተቆጥረውባቸው ሶስት ጎሎችን ብቻ ማስቆጠር ችለዋል ::

በወልቂጤዎች በኩል በተለይም የፊት መስመር ተጫዋቹ አህመድ ሁሴን ፈጣን እንቅስቃሴዎች ለሲዳማ ቡና የተከላካይ ክፍል ፈተና እንደሚሆን ከወዲሁ ይጠበቃል።

በተመሳሳይ ነጥብ 18 ላይ ሆነው የሚገናኙት ሁለቱ ቡድኖች ወልቂጤዎች በጨዋታው ድል የሚቀናቸው ከሆነ በ 21 ነጥቦች በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በአራተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ ሲዳማዎች ከተከታታይ ከሜዳ ውጪ ሽንፈት በሃላ ድል ማድረግ የሚችሉ ከሆኑ በተመሳሳይ ሁኔታ አራተኛ ደረጃን መያዝ የሚችሉ ይሆናል ::

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor