የጨዋታ ቅድመ-ዕይታ | ወላይታ ድቻ ከ ወልዋሎ አ.ዮ

 

ዛሬ(ሐሙስ) በተካሄደው የወልቂጤ ከተማ እና አዳማ ከተማ ጨዋታ የጀመረው 17ተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ነገ 7 ጨዋታዎችን ሚያስተናግድ ይሆናል።ሶዶ ላይ ወላይታ ድቻ ወልዋሎን ሚያስተናግድበትን ጨዋታ እንደሚከተለው ዳሰነዋል።

ጨዋታ: ወላይታ ድቻ ከ ወልዋሎ
የጨዋታ ቀን: አርብ መጋቢት 4/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ፌደራል አርቢትር ሀብታሙ መንግስቴ
የጨዋታ ቦታ: ሶዶ ስታድየም

ባሳለፍነው ሳምንት ወላይታድቻ በሲዳማ ቡና ሽንፈት ሲያስተናግዱ በአንፃሩ ወልዋሎ አዲግራቶች በመጨረሻው ደቂቃ በተቆጠረባቸው ግብ አቻ ሆነው ሶስት ነጥብ ማግኘት ሳይችሉ መቅረታቸው ይታወሳል። ቡድኖች ያጡትን ነጥብ ለማካካስ ከፍተኛ ፋክክር ያለበት ጨዋታ ያሳያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በደቡብ ደርቢ በሲዳማ ቡና ሽንፈት ያስተናገዱት ወላይታዎች ከደለለኝ ደቻሳ ቅጥር በኃላ መልሰው ያገኙትን በሜዳቸው ያለመበገር ስሜትን ተጠቅመው ከጨዋታው ነጥብ ይዘው ሊወጡ እንደሚችሉ ይገመታል።ከ9ኛው ሳምንት በኃላ በሜዳቸው ሶዶ ስታድየም ላይ ባካሄድዋቸው 3 ጨዋታዎች ላይ አንድ ግብ ሳያስተናግዱ ዘጠኝ ነጥቦችን ሰብስበው 5 ግቦችን ማስቆጠር ችለዋል።

የቡድኑን በፍላጎት የመጫወት ስሜትን መመለስ የቻሉት አሰልጣኝ ደለለኝ ደቻሳ መስመር ላይ በቀኝ እና በግራ በኩል በሚሰለፋት እዮብ አለማየሁ እና ቸርነት ጉግሳ ላይ መሠረት ባደረገ አጨዋወት መረጋጋት የተሳነውን የወልዋሎ ተከላካይ ክፍልን ይፈትናሉ ተብሎ ይጠበቃል።በተጨማሪም ከአጥቂ ጀርባ ሚሰለፈውና ከባዬ ገዛሀኝ ጋር ጥሩ ጥምረት እየፈጠረ ሚገኘው ኢድሪስ ሰይድ በነገው ጨዋታም ከታታሪው አጥቂ ጋር ሚኖራቸው መግባባት ሚጠበቅ ነው።

በወላይታ ድቻዎች ውብሸት አለማየሁ በጉዳት የነገው ጨዋታ የሚያመልጠው ብቸኛ ተጨዋች ሲሆን ባሳለፍነው ሳምንት በጉዳት ያልተሰለፈው ደጉ ደበበ ከጉዳቱ አገግሞ ለነገው ጨዋታ ዝግጁ ሆኗል።

አለመረጋጋት ውስጥ ሚገኙት ቢጫ ለባሾቹ ከገቡበት የውጤት ቀውስ ለመውጣት ከነገው ጨዋታ ውጤት ይዞ መውጣት ግድ ሚላቸው ይሆናል።በ7ተኛው ሳምንት ድሬዳዋ ላይ ድል ካስመዘገቡ በኃላ ባለፋት 9 ጨዋታዎች ላይ ማሸነፍ ያልቻሉት ወልዋሎዎች ከወራጅ ቀጠናው ለመውጣት ጥንቃቄ ላይ መሠረት ያደረገ አጨዋወትን ለመተግበር ይሞክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከሰበታው ጨዋታ በኃላ ለጋዜጠኞች በሰጡት ድህረ ጨዋታ አስተያየት ላይ የራሳቸው አጨዋወትን ለመተግበር ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው የተናገሩት ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ከዚህ ቀደም ቡድኑ የሚጠቀመውን ጁንያንስ ናጋንጂቡ እና ኢታሙና ኬይሙኔ ላይ ትኩረት ያደረገ ረጃጅም ኳሶችን በመጠቀም እድሎችን ለመፍጠር ሊሞክሩ እንደሚችሉ ይገመታል።ባሳለፍነው ሳምንት ሰበታን በገጠመው ስብስብ ላይ በግማሽ ዓመቱ የተጨዋቾች ዝውውር ላይ ካስፈረምዋቸው 5 ዝውውሮች ሥስቱን ቀዋሚ አሰላለፍ ላይ የተጠቀሙት አሰልጣኙ በነገው ጨዋታ ላይም በርካት ለውጦችን ሊያደርጉ እንደሚችሉ ይገመታል።

አይናለም ሀይሉ፣ሳሙኤል ዮሐንስ ፤ ካርሎስ ዳምጠው እና ፍቃዱ ደነቀ በጉዳት አዲስ ፈራሚው ሀይማኖት ወርቁ በግል ጉዳይ ምክንያት በነገው ጨዋታ ለቢጫ ለባሾቹ ግልጋሎት ማይሰጡ ሲሆን ሌላኛው አዲስ ፈራሚ ዮናስ በርታም በጉዳት ምክንያት የመግባቱ ነገር አጠራጣሪ ነው።

Hatricksport website writer

Twitter

ዳዊት ብርሀነ

Hatricksport website writer