የጨዋታ ቅድመ ዕይታ | ኢትዮጵያ ቡና ከ ስሑል ሽረ

የሁለተኛው ዙር የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ በነገው ዕለት በሚካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች ሲካሄድ ኢትዮጵያ ቡናን ከ ስሑል ሽረ ጋር የሚያገናኘው የ 10፡00 ሰዓት መርሀ ግብር ዋነኛው ነው ፡፡

ይህን ተጠባቂ ጨዋታ ኢንተ. አርቢትር በላይ ታደሰ በመሀል ዳኘነት እንደሚመሩት ይጠበቃል ፡፡

ኢትዮጵያ ቡናዎች በዝውውር መስኮቱ እየተሳተፉ ከማይገኙ ክለቦች ዋነኛው ሲሆኑ በሁለተኛው ዙር ወደ ሜዳ ይዘው የሚመጡት ነገር በስፖርት ቤተሰቡ የሚጠበቅ ይሆናል ፡፡ ኢትዮጵያ ቡና በመጀመሪያው ዙር ሲያሳዩ ከነበሩት ድክመቶች አንፃር በሁለተኛው የውድድር አጋማሽ ላይ ተሻሽለው እንደሚቀርቡ ይጠበቃል ፡፡
በዋነኛነት ቡድኑ ጨዋታወን ከኃላ መስርቶ መውጣት ሲፈልግ ይህም በታጋጣሚ ቡድኖች ውስጥ ጫና ውስጥ እንዲገቡ ሲዳርገው ለጎሎች መቆጠር መንስዔም ሲሆነ ታይቷል ፡፡ ይሁን እና ቡድኑ ወደ መጨረሻዎቹ የሊጉ ጨዋታዎች ላይ በተለይም ለአቡበክር ናስሩ በሚጣሉ ረጃጅም ኳሶች ከተለመደው የጨዋታ ዘይቤ ውጪ ሲጫወቱ ለመመልከት ተችሏል ፡፡

ኢትዮጵያ ቡና በተለይም የታፈሰ ሰለሞን ሙሉ ለሙሉ ከጉዳቱ አለማገገም ቡድኑ ላይ የማጥቃት እንቅሳቃሴው ላይ ተፅዕኖ ሲያሳድርበት ለመመልከት ቢቻልም ከጨዋታ ጨዋታ ግን መሻሻሎችን በማሳየት ላይ ይገኛል ፡፡
ኢትዮጰያ ቡና ለመጨረሻ ጊዜ በአዲስ አበባ ስታዲየም ባደረጋቸው ሶስት ጨዋታዎች ላይ ሽንፈትን አላስተናገዱም ፡፡ ወላይታ ዲቻን ሲያሸንፊ ከሰበታ ከተማ እና ወልቂጤ ከተማ ጋር በአቻ ውጤት መለያየት ችለዋል ፡፡ ኢትዮጵያ ቡና በመበመጀመሪያው የውድድር አጋማሽ ላይ ሀያ ጎሎችን ብቻ በጀመሪያው አጋማሽ ላይ ዘጠኝ ጎሎችን ሲያስቆጥሩ በሁለተኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ላይ አስራ አንድ ጎሎችን ማስቆጠር ችለዋል ፡፡ ፡፡

ስሑል ሽረ በአሰልጣኝ ሳምሶን አየለ እየተመሩ ጥሩ እንቅስቃሴን ማድረግ ቢችሉም የኋላ ኋላ ነጥብ በመጣል ከመሪዎቹ ክለቦች ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት እያሰፉ ሄደዋል ፡፡ ስሑል ሽረዎች ከአጥቂያቸው ሳሊፎ ፎፎና ጋር መለያየታቸውን ተከትሎ በአጥቂ ክፍሉ ላይ ክፍተት ሊፈጠርባቸው እንደሚችል ይጠበቃል ፡፡ ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው ዙር ሲገናኙ በባለሜዳው ስሑል ሽረ 1 ለ 0 አሸናፊነት መጠናቀቅ ችሏል ፡፡

በተለይም በረመዳን የሱፍ የመስመር ማጥቃት እንቅሳቃሴ በሚነሱ የጨዋታ ሁነት የተጋጣሚ ቡድን ላይ ጫና እንደሚያደረጉ የታዩት ስሑል ሽረዎች በነገው ጨዋታም ቢሆን ከመስመር በሚነሱ ኳሶች ለኢትዮጵያ ቡና የተከላካይ ክፍል ፈተና እንደሚሆኑ ይጠበቃል ፡፡

ስሑል ሽረ ባለፉት የሊጉ ሶስት ከሜዳቸው ውጪ ባደረጓቸው ጨዋታዎች ላይ ማግኘት የቻሉት አንድ ነጥብ ብቻ ሲሆን በሁለቱ ሽንፈት አስተናግደዋል ፡፡ በመጀመሪያው የውድድር አጋማሽ ላይ 13 ጎሎችን ብቻ ሲያስቆጥሩ በጀመሪያው አጋማሽ ላይ አምስት ጎሎችን ማስቆጠር ችለዋል ፡፡

በጨዋታው ባለ ሜዳዎቹ ኢትዮጵያ ቡናዎች ድል ማድረግ የሚችሉ ከሆነ በደረጃ ሰነጠረዡ እስከ ሰባተኛ ደረጃን መያዝ ሲችሉ ከአሰልጣኝ ሳምሶን አየለ ጋር መለያየታቸው የተገለፀው ስሑል ከሜዳቸው ውጪ ድል ካደረጉ በደረጃ ሰንጠረዡ አራተኛ ላይ የሚቆናጠጡበትን ውጤት የሚያስመዘግቡ ይሆናል ፡፡

ቅጣት እና ጉዳት :- በኢትዮጵያ ቡና በኩል የቅጣት እና ጉዳት ዜና ያልተሰማ ሲሆን በስሁል ሽረ በኩል በቅጣት አብዱልለጢፍ መሐመድን በአምስት ቢጫ ካርድ ሲያጡ ዲዲዬ ሌብሪ ከ4 ጨዋታዎች ቅጣት በኃላ ሲመለስ ዮናስ ግርማይና ክፍሎም ገብረህይወት ከደረሰባቸው ጉዳት አገግመው ለነገው ጨዋታ ዝግጁ ሆነዋል።

 

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor