መነሻ ገጽ ባህርዳር ከተማ የጨዋታ ቅድመ-ዕይታ | ባህር ዳር ከነማ ከ አዳማ ከተማ
ባህርዳር ከተማአዳማ ከተማየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ቅድመ-ዕይታ

የጨዋታ ቅድመ-ዕይታ | ባህር ዳር ከነማ ከ አዳማ ከተማ

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ አጋማሽ የሚደረጉ ሲሆን ሰባት ጨዋታዎች ነገ (ረቡዕ) ሲደረጉ ቀሪ አንድ ጨዋታ ደግሞ ሀሙስ የሚደረግ ይሆናል። በነገው እለት ከሚደረጉት ጨዋታዎች መካከል ባህር ዳር ከነማ ከ አዳማ ከተማ የሚያደርጉትን ጨዋታ ለእናንተ እንዲስማማ አድርገን እንደሚከተለው ዳሰነዋል። መልካም ንባብ።

ጨዋታ: ባህር ዳር ከነማ ከ አዳማ ከተማ
የጨዋታ ቀን: ረቡዕ ጥር 20/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ኢንተርናሽናል አርቢትር ሊዲያ ታፈሰ
የጨዋታ ቦታ: ባህርዳር አለም አቀፍ ስታዲየም

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት ላይ የደረሰ ሲሆን በሊጉ አጠቃላይ ጉዞ 179 ጎሎእ ተስተናግደዋል ፡፡ በዚህ ሳምንትም በ10ኛው ሳምንት ወደ አዲስ አበባ ስተዲየም አቅንተው በቅዱ ጊዮርጊስ የተሸነፉት ባህርዳር ከነማዎች በሜዳቸው ከተከታታይ ሽንፈቶች በኋላ በሜዳው በማሸነፍ በማገገም ላይ የሚገኘውን አዳማ ከተማን ያስተናግዳሉ።

በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ እየተመሩ አስፈሪ የፊት መስመር ጥምረትን ለመፍጠር የቻሉት ባህርዳር ከተማዎች በሜዳቸው ለአዳማ ከተማ ትልቅ ፈተና እንደሚሆኑ ይጠበቃል ፡፡
ምንም እንኳ በአስረኛው ሳምንት መርሀ ግብር ሽንፈትን ቢያስተናግዱም ቡድኑ በማጥቃት ሽግግር ላይ ፈጣን እንደሆነ ታይቷል ፡፡ ባሀርዳር ከነማዎች በሊጉ ባደረጓቸው አራት ጨዋታዎች ላይ በሁሉም ሶስት ነጥቦችን ማግኘት ከቻሉት ሌሎች ክለቦች መካከል ዋነኞቹ ሲሆን በሜዳቸው ባደረጉት ጨዋታ አስራ ሶስት ጎሎችን ከተጋጣሚ መረብ ላይ ማሳረፍ ችለዋል ፡፡
አዳማ ከተማዎች በበኩላቸው ከተጫዋቾች ደሞዝ እና የተለየዩ የውስጥ ችግሮች ተያይዞ በውስጣዊ ችግሮች ላይ ቢገኙም አዲስ አዳጊውን ሀድያ ሆሳዕናን በማሸነፍ ከወራጅ ቀጠናው ለመውጣት ችለዋል ፡፡
አዳማ ከተማ በሊጉ የአስር ሳምንታት ጉዞ ላይ ከሜዳቸው ውጪ ሶስት ነጥቦችን ማግኘተ ተስኗቸዋል ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከሜዳቸው ውጪ ባደረጓቸው ጨዋታዎች ላይ ማስቆጠር የቻሉት ሁለት ግቦችን ብቻ መሆኑን ከግምት ሲገባ በዚህ ሳምንት የአጥቂው ክፍል ተሻሽሎ እንደሚቀርብ ይጠበቃል ፡፡
ጨዋታውን ተከትሎ ባህርዳር ከነማዎች በደጋፊዎቻቸው ፊት ድል የሚቀናቸው ከሆነ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ እስከ ሶስተኛ ደረጃ መቀመጥ የሚችሉበትን ውጤት ሲያስመዘግቡ አዳማ ከተማዎች በሌላ በኩል ካሸነፉ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ የሌሎች ቡድኖች ውጤቶችን ጠበቀው እሰከ አምስተኛ ደረጃን የሚያሲዛቸውን ውጤት የሚይዙ ይሆናል ፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...